ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን ኣሽነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ትናንት በተደረጉ 20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጀመሪያ ጊዜ አቻ ሲለያይ ደደቢት አሸንፏል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 28 ነጥብ ይዞ በሶስተኝነት ደረጃ ላይ ከሚገኘው መከላከያ ጋር ያደረገው ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
ይህን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ ስድስት የፕሪሜየር ሊግ ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮን መሆን የሚያስችለውን ውጤት ማሳካት አልቻለም።
በመጀመሪያው ግማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ የግብ ሙከራ ማድረግ ችሏል።
በሌላ በኩል ደደቢት በዘጠኝ ነጥብ በሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ለ 1 ፣ ሀረር ከተማ ከወላይታ ዲቻ 0 ለ 0 ሲለያዩ  ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 እንዲሁም አርባምንጭ ከነማ መብራት ሃይልን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።
በክልል ትናንት  ጎንደር ላይ ሀዋሳ ከነማን ያስተናገደው ዳሽን ቢራ በ37ኛ ደቂቃ በጣለው ከባድ ዝናብ ጨዋታው ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ዛሬጨዋታው ከቆመበት ቀጥሎ  0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር