ሰሞኑን ኢትዮጵያ የቢ ፕላስ ደረጃን ማግኘቷ ተገጿል ለመሆኑ ስለተቀሩ ኣገራት ምን ያህል ያውቃሉ?

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እድገትና ኢንቨስትመንትን በመሳብ የቢ ፕላስ ደረጃን አገኘች  
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ እድገትና ኢንቨስትመንት መስህብ አለም አቀፍ ደረጃ እንደወጣላት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሶፈያን አህመድ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ አስካሁን ያስመዘገበችው እድገት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ መሆኑ በ3 አለም አቀፍ ገለልተኛ ተቋማት መረጋገጡንም ገልፀዋል ሚንስትሩ ።
ሶስት አለም አቀፍ  ተቋማት በአፍሪካ ደረጃ ከወጣለቸው አራት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያን  በ ቢ ፕላስ ደረጃ አስቀምጠዋታል።
አቶ ሶፊያን ደረጃው ኢትዮጵያ በዕድገት ግስጋሴዋ ያስመዘገበችው ውጤት ተጨባጭ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ይህ ውጤት አገሪቱ ቀደም ሲል ትታወቅበት የነበረው የድህነት ገፅታ መቀየር መቻሉን ያመላከተ ነው ያሉት።
አገሪቱ ይህን ደረጃ ያገኘችው ባለት የኢንቨስትመንት አማራጮች ፣ ምቹነት እንዲሁም ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅም እና በአጠቃላይ በመላ አገሪቱ ያለው የልማት እንቅስቃሴን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑ ነው የተመለከተው።
ስድስት ወራተን በፈጀ ጥናት የተመለከተው የኢኮኖሚ እድገትና ኢንቨስትመንት መስህብ አለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፣ ከአፍሪካም አምስተኛዋ አገር አድርጓታል።
በቀጣይም ተመሳሳይ ደረጃ ለማውጣት ዓመታዊ ምዘና እንደሚካሄድ ተመልክቷል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር