የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 2ኛውን የኦፕን ዶር(Open-Door) ቀን አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በጋር በመሆን ሁለተኛውን የኦፕን ዶር ቀን በደመቀ ሁኔታ ሚያዝያ 14/2006 ዓ.ም አከበሩ፡፡
Hwu Logo"የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን በመወከል ዶ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ የመክፈቻ ንግግር አድረገዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት ኦፕን ዶር በሀገራችን ብዙም ያተለመደ ነገር ግን የተለያዩ የምርምርና የቴክሎጂ ውጤቶችን የምናስተዋውቅበት ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታዎች አሉት ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍቅሬ አክለውም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እምርታና ለውጥ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲው ከአውሮፓ ከካናዳ እና አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በበኩላቸው እንዳተናገሩት መድረኩ በዩኒቨርሲቲውና እና በኢንስዲስትሪው መካከል ከፍተኛ ትስስር የሚፈጠርበትና ኢንስቲትዩቱ የሚሰራቸውን ስራዎች የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሞልቶት አክለው ይህ ቀን እንዲከበር በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች ዩኒቨርሲቲውን የደገፈው የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮን አመስግነዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ማዕከል በተካሄደው መድረክ በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የትምርት ክፍሎችና ት/ት ቤቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባርና እንቅስቃሴ አስተዋውቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል የመወያያ ሰነድ በዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ ቀርቧል፡፡
ውይይቱንም የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ አለሙ ያወያዩ ሲሆን፤ በውይይቱም ዩኒቨርሲቲው ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጋር፣ ከማኑፈክቸሪንግ ዘርፍ ጋር፣ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋርና ከማህበረሰቡ ጋር አብሮ የመሰራት ውስንነቶች እንዳሉበት ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
አቶ መለሰ አለሙ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስሩ በሚገባ ከተጠናከረ የህዳሴውን መንገድ ለማሳካት ጉልህ ሚና ይጫወታል ካሉ በኋላ ዩኒቨርሲቲው በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በዘርፉ በቂ አቅም እንዳለው ገልፀው ለሌሎችም ይህንን መልካም ተሞክሮ በማጋራት ለሀገር እድገት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
በዕለቱ ከክልሉ ንግድ ኢንዱስትርና ከተማ ልማት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች፣ ከከተማ አስተዳደር፣ የዩነቨርሲቲው የበላይ አመራር አካላት ፣ ኢንዱስትሪያሊስቶች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ የኢንስቲትዩቱ የት/ት ከፍል ሃላፊዎችና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር