ሲኣን የዛሬ 12 ኣመት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በኣደባባይ በግፍ የተገደሉት ንጽሃን ሲዳማውያን በሰላማዊ ስልፍ ለማሰብ ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበሉ የሲዳማ ዞን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ኣስታወቁ

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በኣዲስቷ ሲዳማ ታሪክ ልዩ ቦታ ያለውን የሎቄ ሰማዕታት ቀን በሃዋሳ ከተማ ግንቦት ቀን16 በሰላማዊ ስልፍ እና በሌሎች በተለያዩ ዝግጅቶች ኣስቦ ለመዋል የዝግጅት ኮሚቴ ኣቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የዝግጅቱ ኣንድ ኣካል የሆነው እና በሃዋሳ ከተማ ለማድረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በከተማው ኣስተዳደር ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ላይካሄድ ይችላል ተብሏል።

የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደርን የኣገሪቱ ወቅታዊ እና መሰረታዊ ችግሮች በሰላማዊ እና ዴምክራሲያዊ ኣግባብ እንዲፈታ መንግስትን በሰላማዊ ስልፍ ለመጠየቅ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በጽሁፍ ያቀረበለትን ጥያቄ የጸጥታ ኃይል እጥረት ኣለብኝ በምል ምክንያት እንደማይቀበለው ለሲኣን በጻፈው ደብዳቤ ኣስታውቋል።


ለተጨማሪ መረጃ የከተማ ኣስተዳደሩን እና የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር  የደብዳቤ ምላሽ ከታች ያንቡ
 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር