POWr Social Media Icons

Saturday, May 31, 2014

-ለኤክስፖርት የተዘጋጀ ቡና ላይ የኮንትሮባንድ ንግድ ደርቷል
በቡና ንግድ ተሳታፊ ሳይሆኑ የቡና ፈቃድ አውጥተው ለዓመታት የተቀመጡና ምናልባትም አጭበርባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ 37 ግለሰቦችን ፈቃድ መሰረዙን የንግድ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡
የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ሲያቀርቡ፣ የቡና ንግድ መቀዝቀዙንና ኮንትሮባንድ መስፋፋቱን፣ እንዲሁም ከቡና ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የንግድ ሚኒስቴር ምን እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀዋል፡፡
የቡና ጉዳይ ድሮ በሚኒስቴር ደረጃ ይመራ ከነበረበት ወርዶ በአንድ ተቋም ውስጥ መመሸቁ እንደሚያሳስባቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ከኮንትሮባንድ መስፋፋት በተጨማሪ የቡና ንግድ ሳይኖራቸው የቡና ፈቃድ ያወጡ መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡
በቡና ንግድ ካልተሰማሩ ፈቃዱን ለምን እንደሚፈልጉት መገመት እንደሚቻል የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ዋነኛው መንግሥት ለቡና ንግድ የሚሰጠውን ትኩረትና ጥቅማ ጥቅም ለመቀራመት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
በቡና ንግድ ዘርፍ ለሚሰማሩ መንግሥት ቅድሚያ የባንክ ብድርና የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኙ ስለሚያደረግ፣ እነዚህ በቡና ንግድ ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ያወጡ ነገር ግን ኤክስፖርት አድርገው የማያውቁ ነጋዴዎች ይህንን ጥቅም ለመመዝበር አቅደው ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ሥራ የሚሠሩ የቡና ንግድ ፈቃድ ይዘው የተቀመጡ ነጋዴዎች ፈቃድ ተሰርዟል፤›› ብለዋል፡፡
እነዚህ ነጋዴዎች የሚያገኙትን ብድር ተጠቅመው አራጣ የማበደር ተግባር ውስጥ  ተሰማርተው ሊሆኑ ይችላል የሚሉት አቶ ከበደ፣ የነጋዴዎቹን ማንነት ከመግለጽና ፈቃዳቸውን ከመሰረዝ ባለፈ የሚወሰድ ዕርምጃ ስለመኖሩ አልተናገሩም፡፡ 
የፓርላማው አባላት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቡና ዘርፍ ላይ ያካሄደውን ጥናትና ግኝቱን መረጃ በማድረግም የሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡
ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተመረጡ 15 ቡና ላኪዎች ላይ ባለፉት አምስት ዓመታት  ውስጥ ወደ ውጭ አገር ኤክስፖርት ያደረጉት ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በሕጉ መሠረት ብሔራዊ ባንክ አውቆት ስለመላኩ ለማረጋገጥ ቢሞከርም ማረጋገጫ እንዳልተገኘለት፣ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ ልታጣ እንደምትችል ሪፖርት ማድረጉን በመጠቆም፣ ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ እንዲያስረዱ ሚኒስትሩ ተጠይቀዋል፡፡
ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ችግሩ እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለውን ሚኒስቴሩ እያጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ከበደ፣ በጥናቱ ውጤት መሠረት በሕግ የሚጠየቅ ካለ ይጠየቃል ብለዋል፡፡
‹‹ላኪዎች ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማዕከል ቡና ይገዛሉ፣ ከገዙት ቡና ለሚልኩት የቡና መጠን ኤልሲ ይከፍቱና የብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ያገኛሉ፡፡ የብሔራዊ ባንክን የመላኪያ ፈቃድ ይዘው ሲሄዱ ነው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቡናው እንዲወጣ የሚፈቅደው፤›› በማለት የቡና አላላክ ሥርዓቱን አስረድተዋል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ሦስት ተቋማት መካከል ማለትም በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማዕከል፣ በብሔራዊ ባንክና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መካከል በሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ወቅት ችግር ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል፣ ይህንን ለማጣራት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ አሥር ወራት ውስጥ 206,825 ቶን የቡና ምርት ወደ ውጭ በመላክ 822 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በተያዘው ዕቅድ ላይም ሆነ ባለፈው ዓመት በተላከው መጠን ላይ መድረስ አለመቻሉን ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል፡፡
በሪፖርቱ መሠረት በአሥር ወራት የተላከው የቡና መጠን 136 ሺሕ ቶን ብቻ ሲሆን፣ የተገኘውም 489.3 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በመጠን 8.8 በመቶ ሲቀንስ በገቢ ደግሞ 15.2 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ መዋዥቅ የተነሳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ የኤክስፖርት ቡና በሕገወጥ መንገድ በአገር ውስጥና ወደ ጎረቤት አገሮች እየወጣ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ንግዱን በመከላከል ረገድ የተደረጉ ጥረቶች ውስን መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቡናን ጨምሮ ሌሎች የወጪ ንግድ ምርቶችን ሕገወጥ ንግድ ለመቆጣጠር ከፌደራል እስከ ክልል የሚዘልቅ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ኃይልና ኮማንድ ፖስት መመሥረቱን አስረድተዋል፡፡  

It has finalized a partnership with Japanese firm to import green tea
Aleta Land Coffee, a local coffee firm announced that it would a open trans-border coffee shop in Asia starting next year.
It was made public last Saturday in Hawassa, regional capital of the Southern Nation Nationalities Peoples Regional State (SNNPR). Celebrating the 10th anniversary and inauguration of three factories in the town, Habetamu Silla, general manager of Aleta Land Group told The Reporter that establishing a trans-border coffee shop in Asia and worldwide is being undertaken along with importing green tea seedlings from Japan to send back in the form of soft drinks.
Aleta Land Group was initially established in 2004 with a paid up capital of one million birr, which through years has grown to 62 million Br. “These days, many young Asians have started drinking coffee in addition to their well-known tea tradition,” Habtamu tells why his company is keen on opening coffee shops beside exporting packed coffee. The Company has already secured 500 hectares of land in the Kaffa zone, a globally known spot for forest coffee and owns eight full-fledged coffee processing sites in the Bonga town, Kaffa besides its export-import unit in the capital Addis Ababa. 
Desse Dalke, president, regional government of SNNP acknowledged the relentless efforts made by the company harnessing the immense potential of the region, particularly the coffee sector while inaugurating the three factories planted in the regional capital, Hawassa. “We are hopeful that this company will become more competitive worldwide in utilizing the region’s potential,” he said. 
On the other hand, the group has been discussing green tea production with a Japanese firm to plant the seedlings and distribute it back in the form of bottled drinks. Green tea would easily penetrate the local market because of its healthy values, says the general manager.
The quiet roads, the beautiful scenery, the spectacular lake, comfortable rooms are definitely a gateway from Addis Ababa.
These days, the dusty roads of Addis, the cars honking, the concrete jungle, are becoming too much for people to handle. Due to that people like Natan Ayele can't wait for Friday in order to get out of the city. “Thank God it is Friday,” he says. Usually, his destination is Hawassa, which is located some 270 km south of Addis. Going to the Haile Resort relaxes him and traveling gives him freedom. Whether it is going to a quiet restaurant or staying at home, Addis is the last place he wants to spend his weekends.
Haile Resort is a place where he sits for hours reflecting and reading. He sometimes takes a friend to enjoy the weekend with. 
Usually, when people go out of the city they tend to drink more. However, he opposes the idea of intoxication. Rather, he just sits by the pool and might have a couple of glasses of wine. It is not only Hawassa; he also he likes to go to Kuriftu in Bishoftu.
He plans his trips on Thursdays and selects who he wants to go with. If it is far, he goes there by plane. Otherwise, he drives.
Even though he does not want to reveal how much he spends on his weekends he believes that money is here to serve people. Apart from expensive lodges and resorts he sometimes goes to national parks.
Looking at the booming construction in the city many complain and want to get away from the city to be with nature and find solitude. 
Back in olden days, Addis Ababa was covered with huts and trees. Now the population of Addis Ababa is growing, estimated at more than three million. In the city the scorching sun is felt: and there are shades, parks, open spaces to enjoy the quality of life.
To escape from all that many go to the resorts, lodges that are found outside Addis.  And for travelers there are many resorts such as the Kuriftu Resort and Spa.
Facing a Crater Lake, Kuriftu puts many in a very calm state of mind. Here people can swim, have massage service, view the lake, and be prepared to be overwhelmed with the type and the variety of food the place can offer.
Whether one is a child or not the waitresses actually salute the guests with a respect which is actually given to a senior person, according to Ethiopian culture. Fasil Assefa, 29, just got back from Kuriftu and still feels refreshed. 
His trip was a family getaway. First they stopped at Dukem to eat raw meat and tibis (fried minced meat). After reaching Kuriftu they went to their rooms and went to have a steam bath, Swedish massage and after relaxing they headed to the city to walk. 
After having dinner they chatted for a little bit and slept early. Sunday was reserved for swimming, playing different games and since there were children the game zones made them hype. 
Even though he does this with different family members usually his preference is going out with a group of friends who share his interest. He usually goes out at least once every couple of weeks to Bishoftu or Sullulta and if there is a special occasion such as holidays like Timket he heads to Gondar. 
If they go to Sululta they head to Yaya village to play football. After that the relaxation continues. Their journey usually starts on Saturday, enjoying the landscape and the view of the roadside. 
Sometimes they stop to take pictures. If it is with friends it is always about their interest and adventure and seeing more places. Usually they rent a car and sometimes the price goes up to 1,000 birr per person. If it is Kuriftu they pay USD 92 for a double bed. All in all they pay up to 3000 birr per head, which is a bit stiff for them. So they find what he calls decent pensions with a price up to 300 birr. Since he is an artist, he only goes out after 5pm to enjoy nature for inspiration.
When he is with his friends he drinks but, according to him, this is not excessive, rather only a couple for the sake of passing time. They go out to dance, preferably to the Azmari bets. He enjoys listening to the Azmari's lyrics which features their shrewd sense of humor. For him being around water is what he wants to do; with Hawassa and Bahir Dar being his favorite destinations. 
Many of the city dwellers do not go out of the city. Still there are those who go to Dukem and Sululta to eat raw meat and to drink tej (local wine made of honey). There are even those who actually take public transport and head to Suluta to enjoy tej. Now Sululta is becoming a center for restaurants that serve raw meat and tej.
Most of the resorts are exclusive and charge money even to enter the place. Most of the lakes are surrounded with the resorts which might not be affordable by many people with some charging more than one thousand birr per night to stay. Those who can afford have membership in those places and it is their usual hangout spot. Frehiwot Belay and her family are members of African Vacation Club and she has bought a house in Langano and usually rents it for people. 
Firehiwot, who works for the UN, does not pay entrance money if she goes to Kuriftu. She also has a discount but she only goes there if there are meetings or company retreats. She is not really concerned about going out of town. Rather, she enjoys Addis. 
She goes to Langano every now and then with family and says these are not even real beaches, adding that people have to go to Mombasa, Zanzibar, or Seychelles to know what real beaches are. For many, going to those places is once in a life time opportunity. Nowadays, people save money for their honeymoon and go to some of the resorts located on the coast of the Indian Ocean.
Paradise lodge, which is found in Arba Minch, says they are going to change this with the special package they offer. The place was founded eight years ago and during that time there were not many resorts. 
Their main focus is attracting tourists and also offering a weekend getaway package for anyone who is interested. They offer different types of rooms, including VIP rooms and suites. 
 According to Tesfa Teshome, Paradise Lodge's advisor and Omo Tour and Car Rental tour operation manager, the place is eco-friendly with solar light in the room. Now in the process of expanding and opening other branches in different cities, he says that Ethiopia has a lot to offer. 
The package differs from taking people on a road trip to Butajira, Melka Kuntire, Konso, Abiyata and Shala. Within that there is a boat trip and taking a tour of crocodile farm, fish market and ostrich farm. 
Apart from that, tourists get to interact with local people. Even though he believes the diplomatic community is their main customer, Ethiopians in the diaspora and local customers are also growing in number.  
Apart from other activities, mountain trekking is one that is becoming very popular.  He believes this is a place for those who are looking for a secluded area. 
Even though the cost differs according to the different packages, on average it costs from 3,500-7,000 birr. Especially on the weekends, many people demand flights and more than 80 percent of their rooms are occupied. 
This might be the exotic places for people like Yohannes Desta, 25, who rather prefers to go to Adama, another booming city some 100 km south-east of Addis. Usually, he has friends who drive and on Friday they call each other to hit the road. 
They drive slowly taking a break everywhere while chewing khat. At least it takes them three hours to be in Adama.  After arriving at their destination, they rent a guest house.
Adama is a town known for live music but Yohannes and his friends head to Sefer and beer court to listen to DJ music and hit the booze.
Their Saturdays also pass that way and their Sunday is reserved for eating raw meat at Yilma Butchery. The place is their usual destination. They drink fashko, a.k.a. Turbo (a mix of wine, beer and soda) and laugh while enjoying their weekend. He says it is not expensive, costing them 1,000-1,500 birr per person. On the road back to Addis, he says that all of his friends are “refreshed”, adding that they “can't wait till the next outing comes”.
ምንጭ፦www.fanabc.com
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) 22ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ የተለየዩ ጨዋታዎችይቀጥላል።
መከላከያ ከሀዋሳ ከነማ 9 ሰዓት ላይ ሲጫወቱ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት 11 ሰዓት ከ30 ላይ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገናኛሉ።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድህን 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
በክልል ከተሞች ዳሸን ቢራ ከወላይታ ዲቻ ፣ ሙገር ሲሚንቶ ከመብራት ሃይል ፣ ሀረር ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ፣ አርባ ምንጭ ከነማ ከሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።
“መጓዝ ማወቅ ነው…..!” ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1995 ዓም (ከአስር ዓመት በፊት መሆኑ ነው) በወርሃ መስከረም ላይ በአሁን ሰዓት ላይ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በዋና ከተማነት የምታገለግለውን ሃዋሳ ከተማ ለመጀመርያ ጊዜ ለማየት በቃሁ…..፡፡ በሃይቁ ላይ በነጻነት የሚደንሱ የተለያዩ አሶች፤ደስ በሚለው የማያቃጥለው ሞቃት አየሯ እና ሰማይ ላይ በደስታ የሚንሳፈፉ የተለያዩ አእዋፋት……! ባላቸው አቅም ሁሉ በፍቅር አና በደስታ እንግዶቿን የሚያስተናግዱ ህዝቦቿ ልብ የሚመስጥ ነበር…..፡፡ በዚያን ጊዜ ከተማዋ አቅም እንደሌለው…. ወላጅ  እንደረሳው…. የህጻን ልጅ ቁምጣ እዚም እዛም የተቦጨቀ የአስፋልትና የጠጠር መንገዶች፤በአሁን ሰዓት መሃል ፒያሳ ጎዳናን በኩራት ተኮፍሶ የሚታየውን የገብርኤል ቤተክርስቲያን ጨምሮ በጅምር የቀሩ ጥቂት ህንጻዎች፤የሃዋሳ ሃይቀርን ተከትለው እንደሚታዩት ግዙፍ የሾላ ዋርካ ዛፎች….እድሜ የጠገቡ አብዛኛውን አሮጌ ቤቶችና የቆዩ ትንንሽ ሆቴሎች…..ወዘተ…. የነበራት ሃዋሳ…. ውበትዋ ማርኮኝ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየተመላለስኩ ደስታዬን አጣጥሜያለሁ……!፡፡ እነሆ ዛሬ ከሁለት አመት ቆይ በኋላ ዳግም ተመልሼ እዛው እገኛለሁ ፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ከተማዋ ተለውጣለች… አምራለች…!፡፡ በየጊዜው ለውጥ አለ የተጀመሩ ህንጻዎች አልቀው ሌሎች ተጀምረዋል፡፡በ1960ዎቹ አካባቢ 6ኪሎ ሜትር ብቻ ይሸፍን የነበረው የአስፋከልት መንገድ ዛሬ 56.6 ኪሎ ሜትር ደርሷል፡፡ ትንሽ የነበረው ወስጥ ለውስጥ የተቦዳደሰ መንገዶችዋ ዛሬ በኮብል ድንጋይ 18 ኪሎሜትር ያህል ተነጥፏል፡፡ ከሌሎች መሰል የሃገራችን ከተሞች በአንጻራዊነት ሲታይ በእድሜ ትንሽ ብትሆንም ተፈጥሮም እያገዛት እጅግ በፍጥነት እያደገች….. የሃገር ውስጥ እና የውጪ ቱሪስቶች ፤ ኢንቨስተሮች ቀልብ እየሳበች የመጣች ከተማ ሆናለች ፡፡ ይሄንንም ተከትሎ በህዝቦችዋ እና አካባቢው ሊፈጠር የሚችለውን የተለያዩ አሉታዊ እና አዎንታዊ ገጽታዎች እንዳሉ ሆነው በዚህ አጋጣሚ በጣም የማደንቀው ደራሲ ጋዜጠኛ እና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ ሶስተኛ ጆሮውን እና ሰስተኛ ዐይኑን ከፍቶ የታዘበውን የአሉታዊ ጓዳዋን በተለያዩ ጋዜጣና መጽሄት ላይ እያስነበበን ይገኛል ፡፡ ይሄን ለሱ እንተወውና ከተማዋ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ ተዘዋውሬ ካየሁት ከሰማሁት፤ካነበብኩት በምስል በፎቶ ካስቀረሁት አዎንታዊ ገጽታዋ ለማለት ልሞክር፡፡
•••
ዛሬ የምናወራላት ሀዋሳ የዛሬ መጠርያዋን ከማግኘቷ ሀምሳ ዓመት በፊት “አዳሬ” የሚባል ስፍራ ነበር ትርጓሜውም “የግጦሽ መሬት” ማለት ነው እናም ከተማዋ የከተማ ወግ ስታገኝ ሀዋሳ ተብላ መጠራት ጀመረች ፡፡ ስሙ የተገኘው ከሃይቁ በመኮረጅ ሲሆን ቃሉም ሲዳምኛ ሲሆን “ሰፊ” ወይም “የተንጣለለ” እንደማለት ይሆናል ፡፡ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ እና ከባቢያዊ ሁኔታውን ስንመለከት የዛሬው የሲዳማ ዞን  ወይም በቀድሞው የሲዳማ አውራጃ በስተሰሜን የሚገኝ ቦታ ሲሆን ከሻሸመኔ ከተማ አስተደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች ፡፡ከሀዋሳ በስተምእራብ የሀዋሳ ሃይቅ ተንጣሎ ሲገኝ በስተምስራቅ ደግሞ የወንዶ ገነት ተራራ አዘቅዝቆ ይመለከታታል ፡፡ ቦታው የስምጥ ሸለቆ አካል ሲሆን ልዩ ከሚያደርጉት መገለጫዎች ዋነኛው በዓመት ሁለት ጊዜ የዝናብ ወቅቶች ያለውና ለም መሬት በደን የተሸፈነ አካባቢ መሆኑ ነው፡፡
ይህ የዛሬዋን ሀዋሳ ነባራዊ ሁኔታ የለወጠው ታሪካዊ ክስተት የተፈጠረው በ1949 ዓም ነው ፡፡ ጉዳዩም የተከሰተው አጼ ሃይለስላሴ በ1949 ዓም በያኔው አጠራር የሲዳሞን ጠቅላይ ግዛት ለመጎብኘት በሚጓዙበት ወቅት የሃዋሳን አካባቢ ሲያቋርጡ በተመለከቱት የቦታው አቀማመጥና ተፈጥሮአዊ ጸጋ ተማረኩ፡፡ በወቅቱም የጠቅላይ ግዛቱ ገዢ  ለነበሩት ለደጃዝማጅ (በኋላ ራስ) መንገሻ ስዩም ትእዛዝ አስተላለፉ……“ በዚህ ቦታ ዘመናዊ እርሻ ልማት እንዲከናወን አዲስ ከተማም እንዲሰራ እንዲሁም በሃይቁ ዳር ቤተመንግስት እንዲሰራ…..” የሚል ትእዛዝ ነበር፡፡ በመሆኑም ራስ መንገሻ ስዩም ያስተዳድሩት ከነበረው የአርሲ ጠቅላይ ግዛት ተዛውረው የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛትን እንዲያስተዳድሩ ህዝቡንም እንዲያገለግሉ ሹመት አገኙ፡፡ ያኔ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና ከተማ ይርጋለም ነበር ፡፡ ( በዚህ አጋጣሚ ከሃዋሳ ከተማ 43 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቆ የሚገኘው ይርጋለም ከተማ ብዙ ያልተዘመረለት የገጣሚና የውስጥ ቀዶ ሃኪም አብረሃም ፈለቀ (ቢላዋና ብዕር) የምትል የግጥም መድብል አለው)፤የነ ገጣሚ ደራሲ አብረሃም ረታ ፤የነ ገጣሚና  ጸሃፊ ተውኔት ደበበ ሰይፉ የትውልድ ከተማ ነው፡፡ ሄጄ የማየት እድሉ አጋጥሞኛል….! በተለይ ኪነ ጥበብን በሚያደንቅና  በዙርያው ላይ ላለ ሰው በሚያደንቃቸው የደራሲዎች ሃገር ሲገኙ ምን ያህል ደስታ እንደሚሰማው እኔ ምስክር መሆን እችላለሁ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሁሉም በህይወት የሉም…… ምናልባት ወደፊት በተለይ ብዙ ስላልተዘመረለት ሁለገቡ ባለሙያ ስለ ዶክተር አብረሃም ፈለቀ ካየሁት ከሰማሁት ካነበብኩት ለማካፈል ለመጨዋወት እንሞክራለን) ፡፡
ራስ መንገሻ ይርጋለምን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ከተማዋ ወደፊት ህዝቡ ሲጨምርና የማህበራዊ እኮኖሚያዊ ተቋማት ሲስፋፉ  አብሮ መስፋፋት ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ካጠኑ እና ካስጠኑ በኋላ ለውሳኔ በማቅረብ በ1960 ዓም የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማነት ከይርጋለም ወደ ሀዋሳ መዛወሩ እውን ሆነ…..፡፡ ይህ አጋጣሚ ለሀዋሳ እድገት ትልቅ እድል የፈጠረ ሲሆን ለይርጋለም ከተማ እድገት መጎተት መንስኤ ሊሆኑ ከሚችሉ ምክንያቶች እንደዋንኛው የሚቆጠር ይመስላል፡፡ በዚህም የተነሳ የሀዋሳ ከተማ ታሪክ ወደሌላ ምእራፍ ተሸጋገረ ፡፡
                                      2
         መጓዝ ማወቅ ነው…..! ነበር አይደል ያልነው….!? በስሚ ስሚ በወሬ ከመስማትና አንብቦ ከመረዳት የመለጠ ካሉበት ቄዬ ርቀው በመጓዝ ተፈጥሮን በማድነቅ ፤ የህብረተሰቡን ማህበራዊ አኗኗር ፤ባህል አስተሳሰብ ፤የአበላል ፤የአለባበስ፤ሃይማኖታዊ ስርዓት መረዳት ወዘተ….እቦታው ድረስ በመሆን አምስቱንም የስሜት ህዋሳት ከማሰራት ባሻገር ሀገሬ ብለህ የምትጠራት ሃገርህ ከመውደድ በዘለለ በእውቀት የተሞላ መረጃ እንዲኖርህ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ገጽታውን ለይተህና ቀምረህ ለውጪው አለም እና ሀገር ውስጥ መረጃ እና ምስክር የሚሆን ካንተ በላይ ማን ያለ ይመስልሃል ? ማንም….!፡፡ እርግጥ ነው ሃገርህ ላይ በሚኖር መልካም አስተዳደር እጦት እሱን ተከትሎ በሚከሰት ሰው ሰራሽ ድህነት እንኳንስ ከሃገር ሃገር….መጓዝ ቀርቶ እንጀራ ፍለጋ ከቤት ወደ ስራ ቦታ መንቀሳቀስ አዳጋች የሆነበት ጊዜ ደርሰናል ፡፡ በዚህ በኩል በአንጻራዊነት ሲታይ የደርግ ዘመነ መንግስት የተሻለ መሰለኝ ቢያንስ በግዳጅም ቢሆን (ሀገርህን እወቅ) በሚል በየመስርያ ቤቱ በየትምህርት ቤቱ የሚቋቋም ክበብ እንደነበር…… እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው……ከፍተኛ ድጋፍም እንዳለው የሃገር ፍቅር ስሜት እንዲያድርብህ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው……! ብዙ ታሪካዊ ቦታዎች ይጎበኙ ነበር እኔም ባለቀ ሰአትም ቢሆን የዚህ ፕሮግራም ተቋዳሽ ነበርኩ በርካታ ፓርኮችን ተፈጥሮአዊ መዝናኛዎችን ያየሁት ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ ነው…..፡፡ አሁንም የለም ለማለት ባልደፍርም… ብዙ አልተሰራም ኧረ እንደውም አልተነካም….እርግጠኛ ነኝ ከሃገርህን እወቅና ጉዞ የበለጠ ሃይማኖታዊ ጉዞ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም…. ያውም እንደዚህ አለም አንድ በሆነችበት ወቅት መረጃ እንደፈለገ ባስፈላጊው ሰዓት እየተገኘ ለምን እንዳልተሰራ ሁሉም ሊያስብበት…….፤ የሚመለከተው ክፍል ሊመልስ ይገባል ፡፡ ይልቅ ከደርዛችን ሳንወጣ ወደ ወጋችን እንመለስ….፡፡ መጓዝ ከአንድ ቦታ መንቀሳቀስ ትልቅ የውቀት ባህር ውሰጥ እንደመግባት ነው፡፡ በተለይ ለኪነጥበብ ሰው ይሄ አይነገርም……አንድ አጋጣሚ ላጫውታችሁ የሙዚቃ ደራሲ ገጣሚና ድምጻዊ ንዋይ ደበበ በአንድ ወቅት ከምኖርናት ከተማ ተገናኝተን በኪነጥነብ ዙርያ ሰፊ ጊዜ አሳልፈን ነበር ፡፡ ሃገር ውስጥ መጓዝ ተፈጥሮን ማድነቅ ታሪካዊ ቦታዎችን ማየት ይወዳል መውደድ ብቻ አይደለም በአንድ ወቅት ያጋጠመውን እንዲህ ሲል አጫወጠኝ…….፡፡
ከግቤ ባሻገር አለች እረ አንዲት ሰው
በፍቅር በናፍቆት ልቤን የምትወዘውዘው
አቦል ጀባ ብላ ቡናዋን ብቀምሰው
ልቤ ወደ ጂማ ሱስ አመላለሰው
ቤትሽ ጅማ ነው ወይ…….
ጅማ እንውረድ……… እያለ የአባ ጅፋርን ሃገር እያወደሰ የሚያቀነቅነውን ዘመን ተሸጋሪ የማይሰለች ዜማና ግጥም የደረሰው ከሃያ አንድ ዓመት በፊት ለኪነጥበብ ሙዚቃ ስራ በሄደበት አጋጣሚ በጉዞ ወቀት የጊቤ በረሃን አቋርጦ ጅማ ደርሶ ባለው ባየው ነገር ተገርሞ ተደምሞ…! ከዛም አልፎ ጅማ ድረስ ትርኢቱን ሊያሳዩ የሄዱትን የስራ ባልደረቦች ጨምሮ አንድ ታዋቂ የጅማ ሰው ቤት የእንኳን በደህና መጣችሁ የቡና ስነስርዓት በሚደረግበት ወቅት ቡናውን የምታፈላው የጅማ ቆንጆ ልጅ ውቧቷ ትህትናዋ ፤መስተንግዶዋ ስቦት እሷን ዋና ገጸ ባህሪ አድርጎ ጅማና አካባቢዋን የገለጸበትን ድርሰት እዛው ጽፎ እንደመጣ አጫውቶኛል፡፡ለዚህም ይመስለኛል በተለይ ተፈጥሮ….! ሃገርን እያወደሰ በስሜት  እያነሳ የጻፋቸው የሙዚቃ ግጥም ድርሰቶቹ ቀላልና የማይሰለቹ የሆኑት ወይም እውነት እውነት የሚሸቱት  እቦታው ከስሜት ሆኖ ስለሚጽፋቸው ይመስለኛል፡፡ ነውም ደግሞ…….እስቲ ልብ ብላችሁ አድምጧቸው፡፡
የነገር ዳርረዳርታዬ ወዲህ ነው ሃዋሳ ለዚህም ትመቻለች እውነት ትመቻለች….የነገ ሰው ይበለንና አጋጣሚዎችን እናነሳለን…….. 
                                          3
          ከምድር ወገብ 070 05' ሰሜን ላቲቲዩድ በ 3835' ምስራቅ ሎንግቲዩድ በ1697 ሜትር የባህር ወለል አማካኝ ከፍታ ላይ 47.66 ካሬ ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ይዛ የምተገኘው የሃዋሳ ከተማ አመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠኗ 945 ሚሜ አማካኝ የሙቀት መጠን 19.50 ሴንቲ ግሬድ አንጻራዊ የእርጥበት መጠኗ በዝናባማ ወቅት ከ70 እስከ 80 ፕርሰንት እንዲሁም በደረቅ ጊዜ ከ 40 እስከ 60 ፐርሰንት የሆነ ወይና ደጋ የአየር ንብረት ያላት ውብ ከተማ በአሁን ሰአት የህዝብ ብዛትዋ ወደ 300'000 ( ሶስት ሞቶ ሺ) እንደሚጠጋ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሃገራችን ካሉ መሰል ከተሞች በህዝብ ብዛት በ6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡
ቀደም ሲል እንዳወራነው ሃዋሳ……. በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአርቲስቶችን ቀልብ እየሳበች የመጣች ሃገር ሆናለች…..ሮጠው ማረፊያቸው እዛ ነው….. እውነት አላቸው…….   ከሁሉ በፊት ግን የሃዋሳ ውበት ያጣጣሟት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ናቸው ጊዜውም በ1963ዓም አካባቢ ከአንድ ጄነራል ጓደኛቸው ጋር ደቡብን ጎብኝተው ማምሻውን ሃዋሳ ደረሱ… ፡፡ እጅግ በጣም እንደተማረኩ ከሌሎች ቦታዎች ጸጥታው የሀዋሳ ሃይቅ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ለስእል ስራቸው እጅግ አመቺ በመሆኑ ቀደም ሲል ሃገራቸው ላይ በየክፍለሃገሩ የስእል ስቱዲዮ የመክፈት ሀሳብ ስለነበራቸው ደቡብ ላይ ሀዋሳ ሀይቅ አካባቢ ቪላ አልፋ የመጀመርያ የስዕል ቤታቸውንም ገነቡ አርቲስቱ እጅግ በጣም የሚታወቁበትን ስዕል (ውቢት ሲዳማ) ደቡብን ብሎም ሃዋሳን የገለጹበት ስዕል እዚሁ ሃይቁ ዳር ሆነው እንደሰሩት ይነገራል (በዚህ አጋጣሚ ከ35 ዓመት በላይ ያስቆጠረው ቪላ አልፋ ቤታቸው አንዴ ሲወረስ አንዴ  ሲመለስላቸው ቆይቶ አሁን በሄድኩበት ጊዜ በህይወት ከማለፋቸው ጋር ተያይዞ እንደሆነም….. እንጃ…. ወይም በሌላ የቀድሞ ቤቱ እንደተሸጠ…. ፈርሶ…… ከፍተኛ ግንባታ እየተደረገበት መሆኑን አይቻለሁ… ሰምቻለሁ፡፡ ማን ሸጠው……?  እንዴት ተሸጠ….? ምናልባት ውስጡ የነበሩ ስዕሎች ካሉስ ማን ወሰዳቸው…..?፡፡ አዲስ አበባ ያለውን ለህዝብ እንደተናዘዙ አይተናል ይሄስ? ) ፡፡
          ይሄን ለአንባቢ እንተው እና ወደ ጨዋታችን እንመለስ፡፡
               የሃዋሳ ሃይቅ ልዩ ምትሃት አለው ጸጥታው የአእዋፋት ዝማሬ አሶች ዳንስ….. ልስልስ እያለ ከሀይቁ እየተነሳ የሚነፍስ ሙቅ አየር በቃ ምን ልበላችሁ ልዩ ነው..፡፡ ከሃዋሳ ከተማ በስተ ምዕራብ በ1680 ሜትር የባህር ወለል ከፍታ ላይ 94 ካሬ ሜትር የቆዳ ስፋት ይዞ የሚገኝ ሶሆን 8ኪሎ ሜትር አግድመት 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት ዞርያው 49 ኪ.ሜትር አለው፡፡ ይህንን ተከትሎ በቀዳሚነት ለቱሪስት መስህብ በሚያመች መልኩ የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ቁጥር አንድ እና ሁለት በማለት መገንባት የተጀመረ ሲሆን በአሁን አዓት አለም አቀፍ ስታንደርዱን የጠበቁ የሃይሌ እና ሌዊ እንዲሁም ሌሎች ሪዞርቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሠጡ ይገኛሉ…፡፡ ሀይቁ 1363 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ሲኖረው ከፍተኛ ጥልቀቱ 13.5 ሜትር የሆነና ዓመታዊ አማካኝ የትነት መጠኑ 1736ሚ.ሜትር እንደሆነ ይገመታል፡፡ የሃዋሳ ሃይቅ በእትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ከሚገኙ ሃይቆች በመጠን አነስተኛ ነገር ግን በጣም ምርታማ የሆነ ነው፡፡ ሃይቁ በውስጡ ለሚገኙት ስድስት አይነት የዐሳ ዝርያዎች በምግብነት የሚውሉ ፓይቶ ፕላንክተን(100 ዓይነት ዝርያ)እና ዙ ፕላንተን የተባሉ ተክሎችን የያዘ ሲሆን በሃይቁ ላይ በዓለም በጣም አነስተኛ የሆነውን ባለ አበባ ተክል (ወልፊያ አሪዛ) ጨምሮ ብዛት ያላቸው የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ ሀይቁ ሁለት በእትዮጵያ ብቻ ሚገኙና ሰባት በአፍሪካ ከፍታማ ስፍራዎች ላይ ብቻ ያሉ የአእዋፍ ዝርያዎችን አካቶ ብዛት ላላቸው አእዋፋት የመራቢያ የምግብ ምንጭና መጠለያ በመሆን በሃገራን ውስጥ ከሚገኙ 31 ከፍተኛ የአእዋፋት ክምችት ካላቸው ቦታዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በተጨማሪም ሳነብ እንዳገኘሁት መረጃ ከአቢጃታ ሃይቅ መድረቅና ቀውስ ነተያያዘ በተከሰተው የአሳዎች መጥፋት ሳቢያ ብዛት ያላቸው የወፍ ዝርያዎች በመፍለስ የሃዋሳ ሃይቅን መጠግያ አድርገውታል፡፡ለዚህም ነው እኔንም ጨምሮ በርካታ ቱሪስቶችን፤ አርቲስቶችን ለመሳብ የቻለው ሃዋሳ በርካታ ጊዜ መመላለሴን አወራን አይደል…? አዎ አንድ ምሽት ሃይቁ ዳር ቆጭ ብዬ የቀኗ ጸሀይ የቀን ውሎዋን አጠናቃ ጠልቃ ከመሰወሯ በፊት ወቃማ ብርኃኗን እየሰጠችኝ በልዩ ፍቅር እያስታወስኩ የጻፍኳትን ግጥም ጀባ ልበል…….
                  
አዋሳ
አንቺ አዋሳ
ውበት ስምሽን ሳነሳ
በፍቅር ሐይቅ ላይ በቅዳሜ
አጀብ ጉድ እያልኩኝ ተደምሜ
ካሞራ ገደል ስር እጆቼን ዘርግቼ
ለጥሜ እርካታ ውብ አየርሽን ግቼ
ሀሳብ ጭንቄን ላንቺ ትቼ
ቆይቼ ………ቆይቼ
ድንገት ውልብ ቢለኝ
የወፎችሽ ዜማ ቀስቅሶኝ
ሲያሽካኩ በደስታ አሶች ሲደንሱ
ከሀይቅሽ መንደር ላይ ሲፈሱ
ጦጣና ጉሬዛ
ጉሬዛና አባኮዳ
ፍቅር ሰርተው እንደዋዛ
የወግ ጨዋታቸው ለዛ
የደስታዬን እርካብ ላይዘሉ
ቢደክሙ
ከዋርካሽ ጥላ ስር አርፌ
ጭ…….ልጥ ብዬ በሐሳብ ከንፌ
ታቦር ተራራሽ ከሩቁ
ቆሞ ከነግርማ ሞገሱ
‘ና………ወዲህ’ እያለኝ
ሚስጥርሽን ሊያወጋኝ
ብወጣ ካናቱ
ከዙፋኑ
ደስታው አሰከረኝ
እልፍ መንደርሺን ጀባ ቢለኝ፡፡
ሐዋሳ
    መሀል ከተማሽ ከፒያሳ
ዘር ቀለም ሀይማኖት ሳይነሳ
ካ‘ረብ ሰፈር ከደመቀው
  ዙርያ ገባ ከቀለጠው
ቼ……..ብዬ ስሜቴን ጋልቤ
ጋልቤ ጋልቤ ፈረሴን ኮርኩሬ
 በምሽት ጨረቃ "በሌንቦ" ጨፍሬ
ነፍሴን ወድያ ማዶ በደስታ አጥሬ
እንዳልቀር በዛው ለከርሞዬ
ገብርኤል ከመቅደሱ ተሳልሜ
ውቅሮና ኮረም
ሰፈረ ሰላም ከዳር ስሩ
    ተከብቤ ከመንደሩ
የቱን ትቼ የቱን ላንሳሽ አለሜ
  ቃላት ጠፋብኝ እኮ ላ‘ቅሜ፡፡
እንዲህ ነሽ እንግዲህ አንቺ
እንደኔ ፍቅሩን ለቀመሰ ስትመቺ
እንመጣለን ደግሞ ባ‘መቱ
እንደ ባህር አድማስሽ ሰፍቶ
ውበትሽ እንዳ‘በባ ፈክቶ
"ዳኤ ቡሹ" ልትይን በፍቅርሽ
የተስፋን አንቀልባ ተሸክመሽ፡፡
* * *
ሐምሌ 18/1999 ዓም
ሐዋሳ ሐይቅ ዳር
“በልማት ሰበብ አፈና የሚፈፀምበት መዋቅር ነው” - መኢአድ
“1ለ5 አደረጃጀት ለምርጫው ስጋት አይሆንም”  - አንድነት
“ፓርቲያችን፤ ህዝቡ የመዋቅሩ ሰለባ እንዳይሆን የማጋለጥ ሥራ ያከናውናል”  - መድረክ
“ተቃዋሚዎችም እንደ ኢህአዴግ የፈለጉትን አደረጃጀት መፍጠር ይችላሉ”  - መኢአብ
“ኢህአዴግ አፋኝ ሚሊሻ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው” - ኢዴፓ
“አደረጃጀቱን ለምርጫ ይጠቀማል የተባለው የሃሰት ውንጀላ ነው”  - ኢህአዴግ

ምንጭ፦www.addisadmassnews.com
መንግስት 1 ለ 5 የተሰኘውን አደረጃጀት ለፈጣን ልማታዊ እድገት እየተጠቀመበት እንደሆነ ይናገራል፡፡ በገጠር ይሄንኑ አደረጃጀት ለጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተጠቅሞበት ባስገኘው ውጤት፣ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ አገራት ምሳሌ ለመሆን መብቃቱንም በኩራት ይጠቅሳል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ አደረጃጀቱ ፖለቲካዊ ግብን ያነገበ የስለላ መዋቅር ነው፣ የገዥው ፓርቲ የምርጫ ማስፈፀሚያና መቆጣጠሪያ መዋቅር ነው ሲሉ ይተቻሉ፡፡ 
ኢህአዴግ በ1 ለ 5  አደረጃጀት በመላው ሃገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን ረገድ ስኬታማ እየሆንኩ ነው ቢልም ተቃዋሚዎች ግን ለአፈና እየተጠቀመበት ነው ይላሉ፡፡ “ከክልል ክልል፣ ከወረዳ ወረዳ ተዘዋውረን ህዝብን በአላማችን ስር ማሰለፍና ማደራጀት ቸግሮናል፣ አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን እስራትና ድብደባን ጨምሮ ለብዙ እንግልት እየተዳረጉ ነው፣ እንኳንስ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት ያለው አደረጃጀት ልንፈጥር በአንድ ወረዳ ውስጥ እንኳን  ፅ/ቤት መክፈት አቅቶናል፣ ከአዲስ አበባ ህዝብ የማደራጀት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተሸኙ አመራሮች፣ የወረዳ ሹማምንት ሰለባ ይሆናሉ” የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ገበሬው 1 ለ 5 ካልተጠረነፈ፣ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የመሳሰሉ የግብርና ግብአቶችን ማግኘት አይችልም ሲሉ ችግሮችን ይዘረዝራሉ፡፡ 
ኢህአዴግ 1ለ5 አደረጃጀትን ከምንም በላይ ለምርጫ ማስፈፀሚያነት ነው የሚፈልገው ሲሉ የሚከራከሩት ተቃዋሚዎች፤ በምሳሌነትም ያለፉትን ሁለት ምርጫዎች ይጠቅሳሉ፡፡ በ2002 ዓ.ም አገራዊ ምርጫ “ሊግ” እና “ፎረም” ኢህአዴግን በማስመረጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚሉት ተቃዋሚዎች፤ በ2005 ዓ.ም የአካባቢና ማሟያ ምርጫ ደግሞ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ የጤና ኤክስቴንሽንና የግብርና ባለሙያዎችን ጨምሮ በ1 ለ 5 አደረጃጀት በሚገባ ተጠቅሞባቸዋል ይላሉ፡፡ 12 ወራት ብቻ ለቀሩት ቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫም ገዥው ፓርቲ እነዚህን የመንግስት መዋቅሮችና የህዝብ አደረጃጀቶች እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ የአደረጃጀት ስልቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ እና ድጋፍ ማሰባሰቢያ መጠቀሙ ፈጽሞ አያጠራጥርም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊትም አድርጐታል በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ - ተቃዋሚዎች፡፡ 
“የገዥው ፓርቲ የጨዋታ ህግ 1 ለ 5፣ 1 ለ 40 እና 1 ለ 100 መሆኑን ደርሰንበታል” ያሉት የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሃሪ፤ “በልማት ሰበብ አፈና የሚፈፀምበት መዋቅር ነው” በማለት 1ለ5 አደረጃጀትን ይከሳሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደሚለው ለልማት ብቻ ቢሆን ኖሮ፤ ተማሪዎች በ1 ለ5 ባልተደራጁ ነበር የሚሉት ሊቀመንበሩ፤ መዋቅሩ ገበሬውንና ነዋሪውን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኛውን ከገዥው ፓርቲ አስተሳሰብ ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ የሚያስር እንደሆነ ጠቅሰው፤ በመዋቅር ወደታች ከሚወርደው አስተሳሰብ ያፈነገጠም ቅጣት ይጣልበታል ብለዋል፡፡ “በገጠር የ1 ለ 5 አደረጃጀት አባል ያልሆነ ገበሬ፤  ማዳበሪያና የግብርና ግብአቶች እንዳያገኝ ከመከልከሉም ባሻገር ከሌላው የህብረተሰብ ክፍልም እንዲገለል ይደረጋል፡፡ መንግስት ይህን በማድረጉ አፈናውን አጠናክሮ መቀጠል ይችል ይሆናል፤ የህዝብ ተወዳጅነትንና ቅቡልነት ማግኘት ግን አይችልም፡፡” እንዲህ ዓይነቱ ሴራ ኢህአዴግን በ2007 ምርጫ ከመሸነፍ አይታደገውም የሚሉት አቶ አበባው፤ ይሁን እንጂ አደረጃጀቱ በመራጩ ህዝብ ላይ በነፃነት የፈለገውን እንዳይመርጥ ስጋት ማሳደሩ አይቀርም ባይ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ኢህአዴግ በአፉ ግልጽና ፍትሃዊ ምርጫ እንደሚካሄድ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገር ቢደመጥም፤ ይሄ አደረጃጀት ግን ትክክለኛ ምርጫ እንዳይካሄድ የአፈና መዋቅር መዘርጋቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፤ አቶ አበባው፡፡ ይህን አስጊ መዋቅር ለመበጣጠስና ለማክሸፍ መፍትሄው በምርጫው ተሳታፊ የሆኑ ፓርቲዎች ሁሉ ህብረት ፈጥረው በጋራ መቆማቸው ነው ያሉት አቶ አበባው፤ መኢአድ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ለፍትህ ሚኒስቴር እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የአቤቱታ ደብዳቤ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡ 
የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው እስካሁን ህዝብን ለማደራጀት ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በርካታ የአፈና ተግባራት እንደተፈፀሙበት ጠቅሰው፤ የ1 ለ 5 አደረጃጀት በምርጫው ላይ የሚፈጥረው ስጋት እምብዛም ነው ሲሉ ያቃልሉታል - መንግስትን መቀየር የፈለገ ህዝብ፣ የአፈና መዋቅር ሊገድበው እንደማይችል በመግለፅ፡፡ በአሁን ወቅት ፓርቲያቸው ከ34 በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ ዞኖች ቢሮዎችን በማደራጀት፣ ወደ ወረዳዎች ወርዶ  ለህዝቡ ተደራሽ ለመሆን እየጣረ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ በነዚህ ሂደቶች ውስጥ የወረዳ ሹማምንት የሚፈፅሙት ወከባና እንግልት ከአቅም በላይ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በአዲስ አበባ አዳዲስ አባላት ፎርም ሞልተው ከፓርቲው ጽ/ቤት ሲወጡ ፀጉረ ልውጥ ግለሰቦች ክትትል ያደርጉባቸዋል የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ይሄም የአፈና መዋቅሩ ይበልጥ መጠናከሩን ይጠቁማል ባይ ናቸው፡፡  እንዲያም ሆኖ ግን ይህ ለፓርቲያችን ፈታኝ ጉዳይ ተብሎ ሊጠቀስ አይችልም ያሉት ኃላፊው፤ ህዝቡ ጋ ቁርጠኝነት መኖሩን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለተረዳን፣ ገዥው ፓርቲ 1 ለ 5ን ጨምሮ የተለያዩ መዋቅሮችን ዘርግቶ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎችን ለመገደብ እየሞከረ ቢሆንም፣ በምርጫው ለማሸነፍ የሚደረገውን ትግል አጠናክረን ከመቀጠል ወደ ኋላ አንልም ብለዋል፡፡ 
ኢህአዴግ ኃላፊነት የሚሰማውና ለመድብለ ፓርቲ መጐልበት የሚጨነቅ ፓርቲ አይደለም ሲሉ የተቹት አቶ ዳንኤል፤ ሁሌም ምርጫን ህገወጥ በሆኑ አደረጃጀቶች ለማሸነፍ ሲታትር ነው የሚታየው ብለዋል፡፡ የ1 ለ 5 አደረጃጀት፤ በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ላይ ነኝ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ኢ-ዲሞክራሲያዊ የሆነ አደረጃጀት ነው ያሉት ሃላፊው፤ ይሄም ሳያንሰው በገጠሩ የሃገሪቱ ክፍል ሴፍቲኔት፣ ጤና ኤክስቴንሽንና የግብርና ኤክስቴንሽን የመሳሰሉ የመንግስት መዋቅሮችን ፓርቲው ለግል ጥቅሙ ያውላል ሲሉ ይከሳሉ፡፡ አሁን ደግሞ “የህዝብ ክንፍ” በሚባል አደረጃጀት እድሮችን፣ እቁቦችንና የመሳሰሉ ማህበራዊ ተቋማትን ለመቆጣጠር እየተሞከረ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ ፓርቲያቸው እነዚህን መዋቅሮችና አደረጃጀቶች ለመስበር የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የፓርቲው አባላት በአደረጃጀቱ ውስጥ ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ መንግስት ለልማት በሚል የዘረጋውን መዋቅር፣ ለፖለቲካ አላማ እንዳያውል ቁጥጥር መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ተልዕኦ አባላቶቻቸው ውጤታማ የሆነ ተግባር እያከናወኑ እንደሆነ አቶ ዳንኤል አክለው ገልፀዋል፡፡ 
ምርጫ የገዥም የተቃዋሚ ፓርቲም አይደለም፤ ህዝብ የራሱን ውሳኔና አቅሙን የሚያሳይበት ነው የሚሉት የአንድነት ሃላፊ፤ “በሃገሪቱ ካለው ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ አንፃር ገዥው ፓርቲ ያደራጀውን መዋቅር ፈርቶ ህዝቡ የምርጫ ካርዱን የማይገባ ቦታ አይጥልም” ሲሉ ይሟገታሉ፡፡ አቶ ዳንኤል ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉም፤ ፓርቲያቸው በተለያዩ የንቅናቄ መንገዶች ህብረተሰቡን ለማንቃት እየተጋ በመሆኑ፣ የ1 ለ 5 አደረጃጀት ለምርጫው ስጋት አይሆንም ብለዋል፡፡ 
“ገዥው ፓርቲ በተጨባጭ በ2002 ምርጫ  የ1 ለ 5 አደረጃጀትን ‘የምርጫ ሰራዊት’ ብሎ ለምርጫ አላማ እንደተጠቀመበት እናውቃለን” የሚሉት ደግሞ የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጥላሁን እንደሻው ናቸው፡፡ መድረክ እነዚህ አደረጃጀቶች በምርጫ ሂደት ውስጥ እንዳይገቡ በሚል እንደመደራደሪያ ያቀረበው ጥያቄ እስከዛሬ መልስ አለማግኘቱን የጠቆሙት አቶ ጥላሁን፤  በቀጣዩ ምርጫም የ1 ለ 5 አደረጃጀት ተፅዕኖ ላለማድረጉ ምንም ዋስትና የለም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ “በአደረጃጀቱ ውስጥ ጠርናፊ የሆነው ግለሰብ፣ ዋና ተግባሩ ሌሎች በስሩ ያሉ ግለሰቦችን እንቅስቃሴ መከታተል ነው” ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ድርጊቱ የግለሰቦችን ነፃነት የሚፃረርና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው ሲሉ ይነቅፋሉ፡፡ 
መዋቅሩ በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ እንደሆነ የተናገሩት የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ አባል፤ ፓርቲያቸው አሰራሩን በጥብቅ እየተቃወመ፣ ህብረተሰቡ የመዋቅሩ ሰለባ እንዳይሆን በተለያዩ መንገዶች የማጋለጥ ስራ ያከናውናል ብለዋል፡፡ 
አረና ትግራይ ለሉአላዊነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ በበኩላቸው፤ የ1 ለ 5 አደረጃጀት ለምርጫው እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው፡፡ “ፍትሐዊና ሚዛናዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚባል ከሆነ፣ የምርጫ ቦርድም ሆነ ገዥው ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ሊያደርጉ ይገባል” ባይ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኖ ለመቀጠል እነዚህን መዋቅሮች እየተጠቀመ ነው የሚሉት አቶ ጎይቶም፤ በልማት ስም የተዋቀረውን አደረጃጀት ለፖለቲካ አላማ ሊጠቀምበት እንደሚችል ጠቅሰው፤ አደረጃጀቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት  እንዳይኖረው ማስገንዘብ ከፓርቲዎች ይጠበቃል ይላሉ፡፡ 
ኢህአዴግን ጨምሮ የተወሰኑ ተቃዋሚዎች የተካተቱበት የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆነው የመላው ኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ንቅናቄ (መኢአብ) ሊቀመንበር አቶ መሳፍንት ሽፈራው ግን የሌሎቹን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃሳብና ስጋት አይጋሩም፡፡ እንደውም ተቃዋሚዎቹን ይወቅሳሉ፡፡ የማደራጀት መብት ለኢህዴግ ብቻ አልተሰጠም ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህን መብት የመጠቀም የቤት ስራቸውን በአግባቡ ስላልተወጡ ነው የተበለጡት ይላሉ፡፡ ተቃዋሚዎችም እንደ ኢህአዴግ የፈለጉትን አደረጃጀት መፍጠር ይችላሉ የሚሉት አቶ መሳፍንት፤ የ1 ለ 5 አደረጃጀት ችግር ሊፈጥር የሚችለው ለልማት ተብሎ የተቀየሰው መዋቅር ለፖለቲካ አላማ ከዋለ ነው ሲሉ ወደ ተቃዋሚዎች ሃሳብ ይመለሳሉ፡፡ ፓርቲያቸው ጉዳዩን ለመገምገም እየተዘጋጀ መሆኑን በመጠቆምም ከግምገማው በኋላ መግለጫ እንደሚሰጡበት ተናግረዋል - ሊቀመንበሩ፡፡ 
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሊቀመንር አቶ ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤ ጉዳዩን ቁጭ ብለው እንደገመገሙት  ይናገራሉ፡፡ “መንግስት የልማት ቡድን ነው ይላል፤ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ስርአት በዚህች ሃገር እንዳይሰፍን የአፈና ሚሊሻ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው በሚል ነው በግምገማችን የፈረጅናቸው” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ መዋቅሩ በቀጣይ ምርጫ ችግር ፈጣሪ እንቅፋት ይሆናል የሚል ስጋት አለን ይላሉ፡፡ የማደራጀት መብት የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ነው የሚለው አባባል አያስማማንም የሚሉት አቶ ጫኔ፤ እንኳንስ በህዝቡ ውስጥ ዘልቆ አጀንዳን ለማስረፅ ይቅርና ሦስትና አራት ሆኖ የተሰበሰበም በጥርጣሬ የሚታይበት ሃገር ላይ ነው ያለነው ሲሉ ችግሩን ያስረዳሉ፡፡ ኢዴፓ አፈናውን ለመቋቋም ሚስጥራዊ አደረጃጀቶችን ይጠቀማል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ መዋቅሩን ፓርቲያቸው እንደማይቀበለውና ድርጊቱንም “አፋኝ ሚሊሻዎችን እንደማደራጀት” እንደሚቆጥረው ተናግረዋል፡፡ 
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፖለቲካ ምሁር እንደሚሉት፤ ገና ከአሁኑ የተነሳው ውዝግብ በምርጫ ማግስት ለሚከሰቱ ቅራኔዎችና አለመግባባቶች ትልቅ ሰበብ ሊሆን ስለሚችል፣ ኢህአዴግን ጨምሮ ፓርቲዎቹ ሁሉ በጉዳዩ ላይ በሰለጠነ መንገድ ተወያይተው መግባባት ላይ መድረስ አለባቸው፡፡ 
በአንድ ክልል ከተማ ስለ 1ለ5 አደረጃጀት ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተበተነ ሠነድ፣ አደረጃጀቱ በኢኮኖሚ ከበለፀገችው የጃፓን መንግስት የሚጠቀመው እንደሆነና ከዚያም እንደተኮረጀ ይጠቁማል፡፡ አላማውም የልማት ሠራዊት በመገንባት ዜጐችን በየተሠማሩበት ዘርፍ ብቁና ውጤታማ ለማድረግ እንደሆነ  ሰነዱ ያብራራል፡፡ 
በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበ ስለ አደረጃጀቶች የሚተነትን ሌላ ሰነድ ደግሞ ተማሪዎችን 1ለ5 ማደራጀት፣ ተማሪዎች በየትምህርታቸው ውጤታማ ሆነው እንዲጨርሱና የትምህርት ብክነትን ለመቀነስ ዋነኛ መፍትሔ መሆኑን ይገልፃል፡፡ የየቡድኑ ሃላፊነት እና ተግባርም የክፍሉ ተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ተቀራራቢ ደረጃ እንዲደርስ፣ የተሻሉ ተማሪዎች ሌሎችን እንዲረዱ፣ የተማሪዎች የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህል እንዲዳብር፣ ያለአግባብ የትምህርት ክፍለጊዜ እንዳይባክን ማድረግና ሌሎችንም ይዘረዝራል፡፡ 
ያነጋገርናቸው የ1ለ5 አደረጃጀት ተሣታፊዎች በበኩላቸው፤ የስለላ አይነት መዋቅር ነው በማለት የተቃዋሚ  ፓርቲ መሪዎችን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሠራተኛ እንደሚሉት፤ የአደረጃጀቱ አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያሉ የሥራ ክፍሎች፣ በየዘርፋቸው ውጤታማ እንዲሆኑ  ምክክርና ውይይቶች የሚካሄድበት ቢሆንም የውይይቱ ፍሬ ሃሳብ ለበላይ አደረጃጀቶች ሪፖርት ሲደረግ፣ ተቃራኒ ሃሳብ ያንፀባረቁትን ግለሰቦች ለፖለቲካዊ ጥቃት ይዳርጋል፡፡ በመስሪያ ቤታቸው ውስጥ ያሉት አደረጃጀቶች በሙሉ በኢህአዴግ አባልነታቸው በሚታሙ ግለሰቦች እንደሚመሩ የገለፁት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ብዙውን ጊዜ በውይይትና በምክክር ወቅት ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲና ስለልማት ትልሞቹ ገቢራዊነት በስፋት ይደመጣል ይላሉ፡፡ ይህም አደረጃጀቱ ከፖለቲካ ነፃ አለመሆኑን ያሳያል ባይ ናቸው አስተያየት ሠጪው፡፡ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከሚከተለው ርዕዮተ አለም ውጪም ሌላ ሃሳብ ማራመድ እንደማይቻል አክለው ገልፀዋል፡፡ 
በዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ ያለው የ1 ለ5 አደረጃጀት ተዋረዳዊ ሲሆን ከስር ያለው የ1 ለ 5 አደረጃጀት መሪ ከሌሎች አደረጃጀቶች መሪዎች ጋር እንደገና 1ለ5 ይደራጃል፤ እንደዚያ እያለ እስከ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ይደርሳል፡፡ ከላይ የሚቀመጠው ደግሞ የመንግስት ሹመኛ የሆነ ግለሰብ ነው ብሏል፡፡ 
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የህዝብ ተሣትፎና አደረጃጀት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ደስታ ተስፋው፤ መንግስት ስለዘረጋው 1 ለ5 አደረጃጀት ሲያብራሩ፤ “አደረጃጀቱን በርካታ የእስያ ሃገሮችን ጨምሮ በአፍሪካ ውስጥም ታንዛንያን የመሳሰሉ ሀገሮች እየተጠቀሙበት ውጤታማ እየሆኑ ነው፤አደረጃጀቱ ህዝብን ለልማትና ለመልካም አስተዳደር አደራጅቶ ተግባራዊ ለማድረግ የተፈጠረ ነው፡፡ የህዝብን ጉልበት አስተባብሮ፣ በጋራ ተደራጅቶ ያሉበትን የአፈፃፀም ችግሮች በጋራ ቀርፎ እቅድ ላይም ተወያይቶ በጋራ የሚሠራበት አደረጃጀት ነው” ይላሉ፡፡ በዚህ ሂደትም ግቦቹ ሲሳኩ ተጠቃሚ የሚሆነው ራሱ ህብረተሰቡ ነው ይላሉ፤ አቶ ደስታው፡፡ 
ከላይ ጀምሮ እስከታች ያለው አደረጃጀት ዋና አላማው፣ በልማት ሠራዊት ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ነው የሚሉት ሃላፊው፤ የልማት ሠራዊት ሲባልም የተመጣጠነ ክህሎትና አስተሳሰብ በመፍጠር፣ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ማዋል ነው፣ በዚህ መንገድም የልማት ሠራዊቱ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው ባይ ናቸው፡፡ በማስረጃነትም በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በመስኖ ልማት የመጡትን ለውጦች ይጠቅሳሉ፡፡ እነዚህ ለውጦች ዝም ብለው የመጡ ሳይሆን ህዝቡና የመንግስት አደረጃጀቶች ተቀናጅተው ያመጧቸው እንደሆኑ በአጽንኦት የሚገልፁት ሃላፊው፤ በ1 ለ5 አደረጃጀት ውስጥ የሚሳተፍ ሁሉ የኢህአዴግ አባል ነው ማለት አይደለም ይላሉ፡፡  “የኢህአዴግ አደረጃጀት የተለየ ነው፡፡ ከላይ ጀምሮ መሠረታዊ ድርጅት፣ ህዋስ እያለ እስከታች ይወርዳል፡፡ ይሄኛው ግን የተቃዋሚ ደጋፊና አባል ጭምር የሚሳተፍበት የመላው ህዝብ አደረጃጀት ነው፡፡ የተቃዋሚ አባል በመሆኑ በአደረጃጀቱ አትገባም አይባልም” የሚሉት አቶ ደስታ፤ የኢህአዴግ አባል የሆኑትም  ከድርጅቱ መዋቅር ባሻገር በዚህ አደረጃጀት ውስጥም መሳተፍ ይችላሉ ብለዋል፡፡ 
የ1 ለ5 አደረጃጀት የኢህአዴግ አባላት ብቻ የተደራጁበት ነው ተብሎ የሚገለፀው ስህተት ነው ያሉት አቶ ደስታ፤ ለልማት ህዝቡ ቢደራጅ ምንድን ነው ክፋቱ ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ኢህአዴግ አደረጃጀቱን ለምርጫ ይጠቀማል የተባለውም የሃሰት ውንጀላ ነው የሚሉት ሃላፊው፤ ”ምርጫ የህዝብ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን ምርጫው ሠላማዊና ፍትሐዊ እንዲሆን፣ ለምርጫ ምዝገባና ተሳትፎ ህዝብ እንዲወጣ ለማድረግ ተመሳሳይ አደረጃጀቶችን መጠቀም ሃጢያት አይደለም፣ ህዝብ የሚመርጠው ግን የሚቀርብለትን የፖሊሲ አማራጭ መሠረት አድርጐ ነው” ብለዋል፡፡ 

Fair trade monitoring process questioned in wake of findings in Ethiopia and Uganda

A new study of plantations in Ethiopia and Uganda found casual workers who pick the coffee may be paid less on Fair Trade-dominated farms than on larger plantations or areas without a Fair Trade designation. (Kent Gilbert/Associated Press)

The Fair Trade certification movement asks consumers of coffee, tea, sugar and chocolate to pay a little more for the product to help the people who grow and pick the coffee to a better life.
But a new report by an economist from the University of London finds the Fair Trade certification movement may not be living up to its billing.
Christopher Cramer co-author of Fairtrade, Employment and Poverty Reduction in Ethiopia and Uganda studied 12 sites in Ethiopia in Uganda, comparing the wages of hired labour in areas with large plantations, areas with small farmers dominated by a fair trade organization and areas without such an organization.
“What we found was that the wages on average in the area dominated by a fair trade organization weren’t just the same, they were worse, they were lower than the other sites,” Cramer told CBC's The Current.
He also discovered use of child labour and very uneven working conditions, though stories about conditions varied widely from one area to the next.
“Modern toilets...in one tea plantation were for the exclusive use of senior management,” Cramer said.

Working conditions uneven

“We found people who were or had been workers at a certified tea-producing organization in Uganda who weren’t allowed to use the health clinic or they’d have to pay quite a lot for it, so they’d have to go a much further distance to get a government clinic that was free,” he added.
He also found a community where fair trade money had been used to build houses for teachers.
The study raised the question of who has benefited from Fair Trade certifications, Cramer said.
“The sales through the cooperative are dominated by a minority of rather large, so-called smallholders so if there is a little bit extra for the price, the people who dominate the sales are bound to benefit most,” he said.
Harriet Lamb, CEO of Fairtrade International, one of the largest fair trade certification groups, said she welcomed the study as there is little or no research on casual labourers in Uganda and Ethiopia.
But she urged consumers not to give up the Fair Trade certification.

A 'work in progress'

“I think it is worrying, that’s why I would urge everybody to understand fair trade is about step-by-step tackling the really deep-rooted poverty in global trade,” she said.
Lamb said she sees fair trade as a “work in progress.”
“What we see about this study and we welcome it, is the spotlight on the position of very poor workers – casual country workers, many of them women, many of them divorced or widowed, working on smallholder farms for very small amounts of time every year,” she said.
She said the findings should get governments, unions and everyone interested in fairness “thinking about how can we enable those very poor workers to get a better deal.”
Lamb pointed out that the economics of smallholder farmers has been improved as many of these farmers are extremely poor themselves. 
She told of meeting a coffee farmer in Ethiopia who said the biggest benefit of fair trade was that he was able to build a lean-to for his cattle, so he and his family no longer had to share his one-room house with the cattle.
Lamb said Fairtrade International does ask large plantations to pay workers more than the minimum wage, but moving pay scales higher will take a further effort.
Cramer urged more effective monitoring by the organization and said there is a need for further research into labour markets in areas where chocolate, sugar, coffee and tea are grown.
“I really do hope the money that goes to fair trade really goes to fair trade,” said Doron Levy at Trees Organic coffee in Vancouver, who adopted Fair Trade coffee a few years ago when customers began to demand it.
“The philosophy is that you are good to the farmers who produce the good coffee that I like --  It was appealing to me and it was appealing also to many Canadians.”
http://www.cbc.ca/news/business/fair-trade-not-helping-workers-who-pick-crops-study-shows-1.2660028

Friday, May 30, 2014


የአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን  የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን መሠራትን አስመልክቶ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተወሰኑ
ዩኒቨርሲቲዎች ባደረጉት ሰላማዊ ሠልፍ ላይ በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦችና ንብረታቸው ለወደመባቸው ባለሀብቶች፣ መንግሥት ካሳ መክፈል እንዳለበት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ጠየቀ፡፡ 
መድረክ ‹‹ለሰላማዊ ተቃውሞ ጥይት ምላሽ ሊሆን አይገባም›› በሚል መሪ ቃል ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. መነሻውን ከግንፍሌ ወንዝ ድልድይ አድርጐ በቤልኤር ሆቴል፣ በህንድ ኤምባሲ፣ በአዋሬ አደባባይና በአድዋ ድልድይ በማድረግ በድንበሯ እናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሜዳ ላይ ባጠናቀቀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሐሳቦችን አቅርቧል፡፡
የመድረክ አባልና የፓርላማ ተመራጭ የነበሩት አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም መድረክ ለምን ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ እንደተገደደ ሲናገሩ፣ ‹‹ኢሕአዴግ ራሱ ላወጣው ሕገ መንግሥት ባለመገዛት ኢሕገ መንግሥታዊነቱን አረጋግጧል፡፡ ትግላችን ኢዲሞክራሲያዊ ሒደቶች እንዲታረሙ ነው፡፡ በአገሪቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ችግር የዲሞክራሲና የሕገ መንግሥታዊ አስተዳደር እጦት ነው፤›› ብለዋል፡፡ 
ሕገ መንግሥቱ ሲጣስ ‹‹መብቴ ተጥሷል›› ማለት ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን የገለጹት አቶ ገብሩ፣ የአዲስ አበባንና የልዩ ዞኖቹን የጋራ ልማት ትስስር ሽፋን፣ ሕዝብ ያልተወያየበትንና ያልተስማማበትን ለመተግበር መነሳት ኢሕገ መንግሥታዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሕዝቡና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን የገዢው መንግሥት ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ጭምር ያረጋገጡት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ገብሩ፣ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያቀርቡለት የተለያዩ ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ ሰጥቶባቸው ቢሆን ኖሮ፣ የጠፋው የሰው ሕይወትና የወደመው ንብረት ሊተርፍ ይችል እንደነበር ተናግረዋል፡፡
መንግሥት በ‹‹ጆሮ ዳባ ልበስ›› ያለፋቸውና በቀላሉ መፍትሔ ሊያገኙ በሚገባቸው ጉዳዮች ምክንያት፣ ሕይወታቸው ላለፈው ዜጐች ቤተሰቦችና ንብረታቸው ለወደመባቸው ባለሀብቶች ካሳ መክፈል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ የተፈጠረውን አለመግባባት ወይም ግጭት በተለያዩ ዘዴዎች ማክሸፍ እየተቻለ አልሞ በመተኮስ ሕይወት ያጠፉትን ለፍርድ እንዲያቀርብም አክለዋል፡፡ ገለልተኛ አካል (አጣሪ ኮሚሽን) ተቋቁሞ ጉዳዩን በመመርመር ለሕዝብ እንዲያሳውቅም አቶ ገብሩ አሳስበዋል፡፡ 
ሰላማዊ ሠልፉን የታደሙ የመድረክ አባላትና ደጋፊዎች ‹‹አፈና ይቁም፣ ጥይትና እስራት እኛን ከዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሊያግደን አይችልም፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡትን የሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደታችንን እናካሂዳለን፣ በሕገወጥ መንገድ የሚደረጉ አፈናዎች ይቁሙ፣ አንከፋፈልም፣ ከፋፋዮችን እናወግዛለን….›› የሚሉና በእንግሊዝኛና በቁቤ የተጻፉ መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል፡፡ 
በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ከተገኙት የመድረክ አባል የፖለቲካ ድርጅቶች የአረና ትግራይ ፓርቲ እንዲሁም የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተወካይ አቶ ጐይቶም ፀጋዬ፣ ‹‹መንግሥት ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው የተለያዩ ሴራዎችን ከመሥራት ቦዝኖ አያውቅም፤›› ብለው፣ ይህ ተግባሩ የተነቃበት በመሆኑም ኢሕአዴግ በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣኑ እንዲወርድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
‹‹መሪዎች ጥሩ ሲሠሩና ሲያሠሩ የተወለዱበትን አካባቢና ቤተሰቦቸውን ጨምሮ ሁሉንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይወክላሉ፤›› ያሉት አቶ ጐይቶም፣ መጥፎ ሥራ ሲሠሩ ግን ከራሳቸው በስተቀር ማንንም እንደማይወክሉ ተናግረዋል፡፡ ኢሕአዴግም ይህንን ሊያውቀው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በሕዝብ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣ መንግሥት አለመኖሩንና ሕዝብ እንዲከበር ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ ከፓርቲ ይልቅ ሕዝብ ሊከበር እንደሚገባ ኢሕአዴግ ማወቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሌላው ሰላማዊ ሠልፈኞቹ ያነሱት ነጥብና በአቶ ገብረ ማርያም የተነገረው ጉዳይ፣ በሕገ መንግሥቱ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ መሆኑን የሚደነግገውን ድንጋጌ ኢሕአዴግ በመደፍጠጥ ያለበቂ የካሳ ክፍያና ከመኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎችን እያፈናቀለ መሆኑን ነው፡፡ መንግሥት በዝቅተኛ የካሳ ክፍያ በቂ ያልሆነ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎችን አፈናቅሎ፣ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ እየቸበቸበ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ገብሩ ሕገ መንግሥቱን ባልጣሰ፣ ከሙስና በፀዳ ሁኔታና ባለድርሻን ባሳተፈ ሁኔታ ነዋሪዎች ተገቢ የሆነ ክፍያና በቂ የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የመንገድ፣ የስልክና የተጋነኑ  የዋጋ ጭማሪዎች ላይ፣ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦትን መንግሥት በአስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ 
የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ያላግባብ የታሰሩትም ካሳ እንዲከፈላቸው አቶ ገብሩ ጠይቀዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ ሃይማኖትና መንግሥት አንዱ ባንዱ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ መደንገጉን የጠቀሱት አቶ ገብሩ፣ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል መንግሥት እንዲቆም እንዲያደርግና በቅርቡ ወጥተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙት አፋኝ ሕጐች እንዲታረሙ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹የደኅንነትና የፀጥታ ኃይሎች፣ መከላከያና ፖሊስ ሠራዊት ሉዓላዊነታችንን ጠባቂዎች፣ ታማኝነታቸው ለአገሪቱ ሕገ መንግሥት ብቻ መሆን አለበት፤›› በማለት አቶ ገብሩ ተናግረዋል፡፡ በሰላማዊ ሠልፉ ላይ የኦፌዴን መሥራችና ለረዥም ዓመታት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳም ተገኝተዋል፡፡ ሰላማዊ ሠልፉም ያለምንም ችግር ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት በሰላም ተጠናቋል፡፡   

Thursday, May 29, 2014


የዜናው ምንጭ፦ www.ena.gov.et
አዲስ አበባ ግንቦት 20/2006 ኢትዮጵያ በሁለት አሥርት ዓመታት ውስጥ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሷን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተከበረው 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 20 ዓመታት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመሆናቸው ስኬታማ ውጤት ተመዝግቧል።
ከሦስት ዓመታት በፊት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አገሮች ባለፉት ስድስት አሥርታት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በድርቅ ክፉኛ ተመተው እንደነበር አስታውሰው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ያለአንዳች መሰናክል ችግሩን ማለፏን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከ23 ዓመታት አገሪቱ ከነበረችበት ከፍተኛ ተመጽዋችነት በመውጣት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዓመት ከ250 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማምረቷንም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ገቢ ወደሚያስገኙ ምርቶች መሸጋገሩንና በቀጣይም ጠንካራ አገር በቀል ባለሃብቶችን በማፍራት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል።
ለሁለት አስርት ዓመታት በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግልም አገሪቱ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ትታወቅበት ከነበረው ረሃብና ጉስቁልና በመውጣት ከኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ-ቃላትም የረሃብተኝነት ምሳሌ መሆኗ እንዲፋቅ መደረጉን ተናግረዋል።ይህም ለኢትዮጵያውያን ታላቅ እመርታ መሆኑን ጠቅሰዋል። 
በቀጣይም ኢትዮጵያ ከሚፈለገው ምርታማነትና የብልፅግና ደረጃ ለመድረስና ግሎባላይዜሽን የደቀነውን የውድድር ፈተና በብቃት ለማለፍ  ዜጎች ከመንግስት ጎን በመቆም  አስተዋጽኦቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በዘመነ ደርግ በግለሰብ ደረጀ ከ500 ሺህ ብር ካፒታል በላይ ማንቀሳቀስ የማይቻልበት ወቅት እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፣ ከግንቦት 20 ድል በኋላ በከተማም ሆነ በገጠር ብዙ ሚሊዮነር ባለሃብቶችን ማፍራት እንደተቻለም ተናግረዋል።
በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በማስወገድ ወጣቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣በፈጠራ በእውቀትና ክህሎት የታነጹና ችግር ፈቺ እንዲሆኑ ማድረግ ዋነኛው የመንግስት ትኩረት ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ህዳሴ ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት፣መገናኛ ብዙኃን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ሌሎች ተቋማት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
በ23 ዓመታት ውስጥ የተገኙ ስኬቶችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን፣ በመንግሥት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታትም ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም አቶ ኃይለማርያም አመልክተዋል።
መንግስት በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ፣ነጻና ፍትሐዊ ሆኖ ለማጠናቀቅ   ርብርብ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ ለመመለስ ከ1983 ወዲህ የምታደርገውን ግስጋሴ በርካታ አገሮች አድናቆት እየቸሩት መሆኑን አመልክተዋል።
መንግስት ኅብረተሰቡ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች እንዲስተካከሉ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ህዝባዊ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የተጠናከረ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተዘጋጀው 23ኛው የግንቦት 20 ማጠቃለያ ልዩ ስነ-ስርዓት ላይ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ  አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ  የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Overview
Big changes are underway in Ethiopia, WFP's largest country of operations. A fast-growing economy is reducing the number of people living in extreme poverty (from 38 percent to 29 percent over the last decade). The government has made strides in expanding its health networks and combating HIV/AIDS, and hundreds of thousands of new pupils enter Ethiopian schools every year. 
Despite these positive advances, Ethiopia remains one of the world's most food-insecure countries, where approximately one in three people live below the poverty line. The 2014 Humanitarian Requirement Document (HRD) released in January by the Government of Ethiopia and the humanitarian community, estimates that 2.7 million Ethiopians will need food assistance in 2014 due to droughts and other short-term shocks. 
WFP is working with the government and our partners to strengthen the resilience of Ethiopians and to chart a more prosperous and sustainable future for the next generation. In 2014, WFP Ethiopia plans to assist nearly 6.5 million vulnerable people with food and special nutritional assistance, including school children, farmers, people living with HIV/AIDS, mothers and infants, refugees and many others. 
Ethiopia faces new challenges, with the arrival of tens of thousands of South Sudanese refugees who fled the fighting that erupted in their country in mid-December. By the end of this year, humanitarian agencies forecast Ethiopia could be hosting roughly 150,000 or more South Sudanese refugees.   WFP is responding by offering food assistance in camps and at border points. In addition, we are meeting the needs of nearly 400,000 other refugees, including those from Somalia and Eritrea. 
WFP also works to help prevent hunger in the future. We do this through programmes that use food as a means to build assets, spread knowledge and nurture stronger, more dynamic communities. This helps communities become more food secure.
Under the Ethiopian government’s MERET programme, WFP aims to provide food assistance in 2014 to nearly 650,000 people participating in environmentally friendly public work projects such as sustainable land and water management. WFP also plans to offer similar assistance this year to 1.2 million Ethiopians involved in public works projects like building roads and schools as part of the next phase of the government’s Productive Safety Net Programme (PSNP)
Our Purchase for Progress Programme (P4P) aims to strengthen the management and marketing capacities of smallholder farmers. This year WFP plans to purchase 40,000 tons of maize and haricot beans from P4P farmers - double our 2013 purchases. WFP will use that food for our various programmes, cutting the cost of importing food while boosting the local economy. For example food grown by P4P farmers is used in the Home Grown School Feeding initiative which provides a daily hot meal to some 40,000 children.  This is part of the WFP’s school feeding programme benefitting 670,000 children from food-insecure families.  
WFP also offers special nutritional supplements to the most vulnerable Ethiopians - including pregnant women, nursing mothers, children under 5 and those living with HIV/AIDS. And we continue to find new and innovative ways of delivering our assistance, such as through cash and voucher pilots for our relief and refugee operations. 
WFP's Vulnerability and Analysis Mapping (VAM) unit has developed a variety of early warning tools to strengthen Ethiopia's fight against food insecurity - and assist the government's shift towards proactive disaster risk management. Our operations also serve the broader humanitarian community, notably through the construction of a new logistics hub in Djibouti, scheduled for completion in 2015, and by operating the UN Humanitarian Air Service (UNHAS), that serves UN agencies along with hundreds of other humanitarian organisations.
ምንጭ፦www.wfp.org