በኣላሙራ እና ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተነሱ ጥያቄዎችን እንደምደግፉ ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ኣስታወቁ፤ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኃይል እርምጃውን ኣለማውገዛቸው እንዳዛዘናቸው ገለጹ


ሪፖርተራችን ሚሊዮን ማቲያስ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው በቱላ ክፍለ ከተማ በንግድ ስራ ላይ የሚተዳደሩ ካላ ማርቆስ ሪብሳ በሰጡት ኣስተያየት መንግስት በተለያዩ ጊዜት የተለያዩ የመብት ጥያቄ ያነሱ ተማሪዎች ላይ የኃይል እርምጃ መውሰዱን ኣስታውሰው፤ በተማሪዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች በኣግባቡ ምላሽ ከመሰጠት ይልቅ የኃይል እርምጃ መውሰድ መልካም ኣስተዳደር እና ዴሞክራሲን ኣሰፍናፈው ከምል መንግስት የምጠበቅ ኣይደልም ብለዋል።
ኣክለውም መንግስት የመብት ጥያቄ በምያነሱት ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ የማይቀለበሰውን የመብት ጥያቄ ለመቀልበስ ከመሞከር ሌላ ሰላማዊ ኣማራጭ መንገዶችን መምረጥ ኣለበት ብለዋል።
በሃዋሳ ከተማ ኣረብ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት እና ስማቸውን እንድጠቀስ ያልፈለጉት ሌላው ኣስተያየት ስጪ በበኩላቸው ሰሞኑን የኣላሙራ እና ታቦር ትምህር ቤቶች የሲዳማ ተማሪዎች ያነሳቸውን ጥያቄዎችን እንደምደግፉ ገልጸው፤ በከተማው በምገኙ ትምህርት ቤቶች ለሲዳምኛ ቋንቋ ትኩረት እንድሰጠው መጠየቅ ስህተት ኣለመሆኑን ኣስረድተዋል።
እኝሁ ኣስተያየት ሰጪ ኣንዳብራሩት፤ የኣገሪቱ ህገ መንግስት ብሄር፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በራሳቸው ቋንቋ መማር መብት ከደነገገበት ወቅት ጅምሮ በመላው ኣገሪቷ ትምህርት በኣከባቢው ቋንቋ በመሰጠት ላይ ሳለ እዚህ ሃዋሳ ከተማ ተግባራዊ ኣለመደረጉ ኣግባቢነት የለውም።
በሃዋሳ ከተማ ሰፈረ ሰላም ያገኛናቸው ሌላዋ ኣስተያየት ሰጪ በበኩላቸው የተማሪዎቹ ጥያቀ የእርሳቸውም ጥያቄ መሆኑን ጠቁመው፤ ሃዋሳ ከተማ በምገኙ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይሆን በግል ትምህርት ቤቶችም ጭምር በሲዳምኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ትኩረት እንድሰጥ እንደምፈልጉ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በኣላሙራ እና ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች በሲዳማ ተማሪዎች ላይ የወሰዱትን የኃይል እርምጃ ኣለማውገዛቸው እንዳዛዘናቸው ኣንዳንድ የሃዋሣ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ሪፖርተራችን ሚሊዮን ማቲያስ በሰሞኑ የሲዳማ የፖለቲካ ትኩሳት ላይ ያናገራቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ የኣገሪቱ ህገ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት በሃዋሳ ከተማ ትምህርት ቤቶች ለሲዳምኛ ቋንቋ ተገቢው ትኩረት ይሰጠው በምል ጥያቄ ባነሱት ተማሪዎች ላይ በመንግስት የተወሰደው እና በመወሰድ ላይ ያለው የኃይል እርምጃ ተገቢነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ በርካታ የኣገር ውስጥ እና ዓለም ኣቀፍ የሰብኣዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች በማውገዝ ላይ ባሉበት በኣሁኑ ወቅት ለሲዳማ መብት መከበር እንታገላለን የምሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ድምጻቸውን ኣለማሰማታቸው ኣዛዝኗቸዋል።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር