በዛሬው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የሲዳማ ክለቦች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 22፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለያዩ  ጨዋታዎች በዛሬው እለት ቀጥሏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች ፥  የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ከመብራት ሀይል በ9 ሰዓት ተገናኝቶ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ረቷል።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና 11 ከ 30 ላይ ተገናኝተው  ፥ ጨዋታው በሲዳማ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ።
በክልል ጨዋታዎች በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከነማ አርባ ምንጭ ከነማን ፣ ቦዲቲ ላይ ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ ቡናን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት  መርታት ችለዋል።
ደደቢት በበኩሉ በአበበ በቂላ ስታዲየም በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘውን ሀረር ከተማን  በ10 ሰዓት አስተናግዶ 1 ለ 1 ተለያይቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር