በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎችን ለማፈን መንግስት የምወስደውን የኃይል እርምጃ እንድያቆም የሲዳማ መብት ተከራካሪዎች ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው ተባለ፤የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

ፎቶ  ኢንተርኔት 

ሰሞኑን ከሬውተርስ የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የኣሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዋናነት ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትን ማሳደግ በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ ከሀገከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይመክራተብሎ ይጠበቃል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጉብኚት ኣስመልክቶ ሪፖርተራችን ሚሊዮን ማቲያስ ያናገራቸው ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች የሆኑት ምሁራን እንደተናገሩት፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኣገሪቱ ባለው የሰብኣዊ መብት ኣያያዝ ላይ የምመክሩ በመሆኑ በዚህ ኣጋጣም በሲዳማ ያለውን የስብኣዊ መብት ረገጣ የማጋለጥ ስራ መስራት ኣለበት ብለዋል።

ኣክለውም መንግስት በሲዳማ በተለያዩ ጊዚያት የሰብኣዊ መብት ረገጣ መፈጸሙን ኣስታውሰው፤ መንግስት በሲዳማ የምፈጽመውን የሰብኣዊ መብት ተባብሶ መቀጠሉን ኣመልክተዋል።

ለኣብነትም በዚህ ወር ውስጥ በሃዋሳ ከተማ የኣላሙራ እና ታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የሲዳማ ተማሪዎች ከሲዳማ ኣፎ ጋር በተያያዘ ላነሱት የመብት ጥያቄ መንግስት የኃይል ምላሽ መስጠቱን ኣብራርተዋል።

በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጥያቄን ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች መንግስት በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የኃይል እርምጃ መውሰድ መምረጡን እንድያቆም ብሎም ዞኑ የምፈጽመውን የዲሞክራሲ እና ሰብኣዊ መብት ረገጣ ለማስቆም የምታገሉ ህዝባዊ ድርጅቶች ይህንን ኣጋጣሚ በመጠቀም ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው በማለት እኝኑ ምሁራን መክረዋል።

ኬሪ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እና ከኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር የሚገናኙ ሲሆን በቀጠናው የሰላም ማስከበር ጥረትና አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በሚያጠናክሩበት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር