ኢትዮጵያና ኬንያን ከሚያገናኘው የሐዋሳ ሞያሌ መንገድ የተወሰነው ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ኬንያን ሚያገናኘው የሐዋሳ ሞያሌ የመንገድ ፕሮጀክት የተወሰነው በመጠናቀቀቅ ላይ ነው።
በአጠቃላይ የአዋሳ ሞያሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በ5 ነጥብ 3 ቢሊዮን የሚገነባ ሲሆን ፥ ስድስት ተቋራጮችም እየተሳተፉበት ይገኛል ።
የሀዋሳ-ሞያሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በየብስ ለማገናኘት እየተገነቡ ካሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው።
ለአብነትም ለመንገዱ አምስተኛ ክፍል የሆነው የያቤሎ ሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ ከሃገረ ማሪያም እስከ ያቤሎ ያለው የመንገዱ አራተኛ ክፍልም በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ሌሎቹ የመንገዱ ክፍሎች በዚህ ዓመት ግንባታቸው የተጀመሩ ሲሆን ፥ በቀጣዩ ዓመት የሚጀመሩም እንዳሉ ነው በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ የሚናገሩት ።
የፕሮጀክቶቹ የጊዜ መራራቅ የተከሰተው በተቋራጮች በቶሎ ወደ ስራ አለመግባት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሳምሶን ፥ 186 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሀዋሳ-ሀገረ ማርያም መንገድም ለሶስት ተቋራጮች ተከፍሎ በዚህ ዓመት ግንባታው መጀመሩን ገልፀዋል ።
ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኘውና  በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የመንገዱ የመጨረሻ ክፍልም በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ግንባታው የሚጀመር ሲሆን ፥ ሙሉ መንገዱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባም የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትስስር ይበልጥ  እንደሚያጠናክረው ሃላፊው ገልፀዋል ።
ኢትዮጵያም ለኬንያ ከምትልካቸው ምርቶቿ የምታገኘው ገቢ ዝቅተኛ የሚባል የነበረና በአንፃሩ ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ያለው አናሳ መሆኑ ነው የሚነገረው ።
ሆኖም ሁለቱ ሀገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የንግድ ትስስራቸውን የማሳደግ ፍላጎታቸው ጨምሯል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኬንያ ለኢንዱስትሪዎቿ የሀይል ፍላጎትን ለማሟላት የምስራቅ አፍሪካ የውሀ ማማ ከሆነችው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ትፈልጋለች ።
የመንገዱ ዝርጋታ የሁለቱ ሃገራትን ኢኮኖሚ እና ልማትን በማፋጠን ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የሚናገሩትም ፥ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የማስታወቂያ እና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አቤልነህ አግደው ናቸው ።
የመንገዱ መዘርጋት በሁለቱ ሃገሮች መካከል የሚኖረው የንግድ ልውውጥ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ካለበት በተሻለ የሚያሳድግ ከመሆኑም በተጨማሪ ከዚህ በፊት ከአውሮፓ እና ከሌሎች ሃገራት ጋር ይደረግ የነበረው የንግድ ልውውጥ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር እርስ በእርስ እንዲጠናከር ያስችላል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር