ይታሰብበት!

ከዘረፋ ያልዳነው ሀዋሳ ከተማና እና እድለኛ ያልሆነው የሲዳማ ቡና ክለብ

ከማህበራዊ መረብ ከ ላይ የተገኘ



ስለሀዋሳ ስነሳ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ውበት ብቻ አይደለም የሚነሳው፡፡ ተፈጥሮ የለገሰቻትን ውበት ምክንያት በማድረግ በህጋዊ መንገድ ወደ ከተማይቱ ከምተመው ኢትዮጵያዊ ህዝብ በላቄ መልኩ በህገ ወጥ መንገድ ሾልኮ በመግባት ከተማይቱንና የአካባቢውን ህብረተሰብ እረፍት የሚነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እያሻቀበ መተዋል፡፡ ለዚህ የመንግሥት አካላት በተለይም የከተማው ማዘጋጃ ጽ/ቤት እና ከንቲባው ጽ/ቤት ይህ ነው የሚባል የማስተካከል እርምጃ ስወስዱ አይታዩም፡፡ ይልቁንም ከሌቦች ጋር በመተባበር የከተማውን ወረራ ያፋጥናሉ እንጂ፡፡ 

አሁን ደግሞ በያዝነው ሳምንት ተመሳሳይ የዘረፋ ተግባር በሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና እሱን ከላይ ሆኖ ከሚቆጣጠሩት እራሳቸውን መርጦ ባለሥልጣን የሆኑ አካላት የከተማይቱን የዘረፋ ሂደት እየተፋፋሜ ነው የሚል ነገር በስፋት ይነገራል፡፡ የከተማሞችን ”አዲሱ ሊዝ አዋጅ” ህብረተሰቡን ለወጉ እንኳን ሳያወያይ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ የንግድና የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የማግኘት እድል መካከለኛ ገቢ ላለው ማኅበረሰብ ክፍል በተለይም ለጭቁኑ መንግስት ሰራተኛ ዝግ በማድረግ እየተሻረከና እየነገደ ያለው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ34 ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ተጫዋቾች በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ቦታ ጀባ ማለቱ ተሰምተዋል፡፡ 

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ደረጃ ለሚገኙ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ተጫዋቾች መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ተወስኖ የነበረ ቢሆንም የከተማ አስተዳደር ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ብሩ ወልደ ለወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ የቦታ ካርታ ካስረከቡ በኋላ በአስቸኳይ ከሀገር እንደምወጡም እየተነገረ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለገሠ ወልደ(የብሩ ታላቅ ወንድም) በከተማው ማዘጋጃ ጽ/ቤት ኃላፍነት በምሰሩበት ጊዜ የሲደማን ህዝብ ከማፈናቀልም አልፎ በማንቋሸሽና በማስለቀስ የሚታውቅ ነበር፡፡ ስለዚህ አቶ ለገሠ ወልደ የእናት ጡት ከሚነክሱ ቡድኖች አንዱ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር