የመብት ጥያቄ ያነሱት የሲዳማ ተማሪዎች በኣሸባሪነት ልከሰሱ መሆኑ ተሰማ፤ገዥው ፓርቲ ከተማሪዎቹ ንቅናቄ ጀርባ የሲኣን እጅ ኣለበት በማለት ላይ ነው

ባለፈው ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በኣላሙራ እና በታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምማሩ የሲዳማ ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቹ ለሲዳምኛ ቋንቋ ትኩረት ተነፍጎታል በማለት ሲዳምኛ ቋንቋ በትምህርት ቤቶቹ የሰራ ቋንቋ መሆን ኣለበት በምል እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን ኣክለው ድምጻቸውን ባሰሙ ተማሪዎች እና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በማካከል በተፈጠረው ግጭት የታሰሩት ተማሪዎች በኣሽባርነት ለመክሰስ መንግስት እየተዘጋጀ ነው።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ እንደዘጋበው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ እና በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተበታትነው ታስረው ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል 25ቱን በኣሸባሪነት ለመክሰስ ኣቃቤ ህግ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑ ታውቋል።

በጉዳዩ ጋር በተያያዘ የከተማው ኣስተዳደር የተማሪዎቹን ቤተሰቦች ባለፈው ቅዳሜ ለማናገር የሞከረ ሲሆን፤ በሰብሰባው ላይ የተገኙት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች መንግስት በህጻናቱ ላይ የኃይል እርምጃ ከወሰደ በኃላ ልጆቻችሁን ምከሩ የምል መልዕክት ማስተላለፉ የሲዳማን ባህል ያልተከተለ መሆኑን በመግለጽ ቁጣቸውን ኣሰምቷል።

እንደተማሪዎቹ ቤተሰቦች ከሆነ፤ በሲዳማ ባህል መሰረት ልጆች ካጠፉ ለወላጆቻቸው ተነግሮ ወላጆቻቸው እንድመክሯቸው ይደረጋል እንጅ የኃይል እርምጃ በመውሰድ በልጆቹ ላይ ጉዳት ካደረሱ በኃላ ምክሩ ማለት ኣግባብነት የለው ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ከተማሪዎቹ ንቅናቄ ጀርባ የሲኣን/መድረክ እጅ ኣለበት በማለት የገዥው ፓርቲ የተማሪዎቹን ንቅናቄ ፖለቲካዊ ገጽታ በመስጠት ላይ ነው።

እንደሪፖተራችን ጥቻ ወራና ገለጻ ከሆነ፤ ገዥው ፓርቲ የተማሪዎቹን የመብት ጥያቄ በኣግባቡ ከመመለሰ ይልቅ ንቅናቄውን ፖለቲካዊ ገጽታ በማላበስ ሲኣንን የመሳሰሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከጉዳዩ ጋር በማላከክ ለፖለቲካ ለራሱ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በመጠቀም ላይ ነው።

ሲኣን/መድረክ ከተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ በመግለጽ ገዥው ፓርቲ ከስም የማጥፋት ዘማቻው እንድታቀብ በጽሁፍ የከተማውን ኣስተዳደር መጠየቁን ጥቻ ወራና ዘግቧል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር