የቀጣዩ ዓመት 5ኛው ምርጫ ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል አሉ


አዲስ አበባ መጋቢት 24/2006 አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ህጋዊ፤ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ  የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።

ኢዜአ ካነጋገራቸው  ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ሰማያዊ ፓርቲ፣ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ይገኙበታል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲው በምርጫው የህዝቡን ይሁንታ ለማግኘት ግልጽ ፖሊሲና ስትራቴጂ  በመከተል ሰላማዊ ትግሉን መቀላቀሉን ገልጸዋል።
 
የምርጫ ዝግጅት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን የሚጠይቅና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ ዋነኛ መሳሪያ በመሆኑ ፓርቲው አባላትን በማፍራትና እጩዎች በመመልመል ላይ ይገኛል።

ምርጫው ፍትሃዊና ህጋዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ፓርቲው የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።                     

የቅንጅት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳሳሁልህ ከበደ በበኩላቸው የፓርቲው አባላት የድርጅቱን ህግንና ደንብ መሰረት በማድረግ ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ያደርጋል።

በቀጣዩ አመት በሚካሄደው ምርጫ ፓርቲው ብቁና ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ከወዲሁ በአባላት ምልምላና የስነ-ምግባር ደንብ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

አቶ ሳሳሁልህ እንዳሉት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አለም አቀፍ ድርጅቶች በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል በሚል የሚያነሱትን ስሞታ ድርጅታቸው አይቀበለውም።

በአገራና ወቅታዊ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ  በፓርቲዎች መካከል ተቀራርቦ  የመወያዬት ባህሉ
ዝቅትኛ መሆኑን ተናግረዋል።                   

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሐሪ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ፓርቲያቸው የገዥው ፓርቲ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ  ገልጸዋል።

መኢአድ በአገሪቱ አብዛኞቹ  አካባቢዎች ጽህፈት ቤቶችን በመክፈትና አዳዲስ አባላትን ለማፍራት ከወዲሁ  እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግረዋል።
                        
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ፓርቲው ራሱን  በአዲስ መልክ በማደራጀትና በማጠናከር ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ክልሎች፤ወረዳዎችና ቀበሌዎች ስለ ድርጅቱ ፖሊሲና አላማ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።    
            
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ቦርዱ ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ስኬታማ  እንዲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ 78 ክልላዊና አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቦርዱ ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የተቋቋሙ ይገኛሉ።

ቀጣዩ ምርጫ በመራጮችና በተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ከፍተኛ ለውጥ ይታይበታል ተብሎ እንደሚጠበቅም  ጠቁመዋል።
            
ባለፉት አመታት በተካሄዱት ሁለት ምርጫዎች  የነበሩ ጉድለቶች እንዳይደገሙ ቦርዱ በርካታ ማሻሻያዎችን ማድረጉንም አስድረድተዋል።

ለአብነትም የምርጫው ሂደት ግልጽና አሳታፊ እንዲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመራጮች የስነ-ምግባር ደንብ ማሻሻያን አንስተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር