የ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 19/2006የ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ምድብ ድልድል ይፋ ሆነ።
ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከማሊና አልጄሪያ ጋር ስትደለደል ከማላዊ፣ ቻድ፣ ሳኦቶሜና ቤኒን መካከል አሸናፊው ቡድን ምድቡን የሚቀላቀል ይሆናል።
በምድብ አንድ ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ናይጄሪያ፣ ከደቡብ አፍሪካና ሱዳን ጋር የተደለደለች ሲሆን ናሚቢያ፣ ኮንጎ፣ ሊቢያና ርዋንዳ በሚያደርጉት የእርስ በርስ ጨዋታ አሸናፊው ቡድን ምድቡን ይቀላቀላል።
ቡርኪና ፋሶ፣ አንጎላና ጋቦን በምድብ ሦስት የተደለደሉ ሲሆን ላይቤሪያ፣ ሌሴቶ፣ ኮሞሮስና ኬንያ እርስ በርስ በሚያደረጉት ጨዋታ አሸናፊው ቡድን ይቀላቀላቸዋል።
ምድብ አራት ኮትዲቯር፣ ካሜሩንና፣ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ሲያገናኝ ከስዋዚላንድ፣ ሴራሊዮን፣ ጋምቢያና ሲሸልስ የጨዋታወ አሸናፊ ቡድን የሚቀላቀላቸው ይሆናል።
በምድብ አምስት ጋና፣ ቶጎና ጊኒ በቀጥታ ሲደለደሉ ማዳጋስካር፣ ሞሪታንያ፣ ኢኩአቶሪያል ጊኒና ኡጋንዳ በሚያደረጉት ጨዋታ አሸናፊው ቡድን  ምድቡን ይቀላቀላል።
በምድብ ስድስት ዛምቢያ፣ ኬፕቨርድና ኒጀር በቀጥታ የተደለደሉ ሲሆን የዚምባብዌ፣ ታነዛንያ፣ ሞዛምቢክና ደቡብ ሱዳን አሸናፊ ምድቡን ይቀላቀላል።
ቱኒዚያ፣ ግብጽና ሴኔጋል በምድብ ሰባት ሲደለደሉ ከብሩንዲ፣ ቦትስዋና፣ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ከጊኒ ቢሳዎ መካከል አሸናፊው ቡድን ምድቡን የሚቀላቀል ይሆናል።
የየምድቡ አሸናፊና በሁለተኛ ደረጃ የሚያጠናቅቁ፣ አንድ ምርጥ ሦስተኛ ቡድንና አሰተናጋጇ ሞሮኮን  ጨምሮ በድምሩ 16 ቡድኖች በ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚፋለሙ ይሆናል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር