ሲኣን ከኣባላቱ እና ከደጋፊዎቹ ጋር ልመክር ነው

በመጪው መጋቢት 20 ላይ በምካሄደው ህዝባዊ ጉባኤ፤ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ብሔራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ከሆነው ከመድረክ ጋር ግንባር መፍጠር ያስፈለገበትን ምክንያት ለማብራራት እና ግንባሩን ወደፊት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሰፊው የሲዳማ ህዝብ ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና እንደዘጋበው ለኣንድ ቀን በሚውለው በዚህ ህዝባዊ ጉባኤ ላይ የሲዳማ ኣባቶች በባህሉ መሰረት መርቀው የሚከፍቱ ሲሆን፤ በሲዳማኣፎ ፤ በኣማርኛ እና በኦሮሚፋ ቋንቋዎች እንደየኣስፈላጊነቱ ለመጠቀም ፕሮግራም መያዙ ታውቋል። በተጨማሪም ጉባኤ በተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች ይታጀባል።

ከዚህም ባሻገር በሃዋሳ በሌሎች የሲዳማ ከተሞች በሚገኙ ዋና ዋና መገናኛ ቦታዎች ላይ ስለ ጉባኤው ዓላማ እና ዝግጅት የሚያትቱ ፖስተሮችን እና ማስታወቂያዎች እንደምሰቀሉ ተገልጿል።

በጉባኤው ላይ በድርጅቱ ኣከፋፈል መሰረት በሰባቱ የሲዳማ ክልል ዞኖች ውስጥ ከምገኙ 21 ወረዳዎች እና 502 ቀበሌያት የተጋበዙ የድርጅቱ ኣባላት እና ደጋፊዎች ብሎም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደምገኙ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከሲዳማ ህዝብ ጋር በባህልና በሃይማኖት ከተሳሰሩት እና ተመሳሳይ የፖለቲካ ኣካሄድ ካለቸው ብሄሮች መካከል የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እንደምሆኑ ታውቋል።

ባለፈው ሳምንት በመድረክ ኣዘጋጅነት በሻሾሚኔ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ጉባኤ ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ(ሲኣን) 15 ኣባላቱ የተወከለ ሲሆን፤ ኣባለቱ በሲዳማ ባህላዊ ኣልባሳት ተሽቀርቅረው ወደ ጉባኤው ኣዳራሽ በገቡበት ወቅት የጉባኤው ተሳታፊዎች ከመቀመጫቸው በመነሳት በጭብጨባ ታላቅ ኣቀባበል ማድረጋቸው ይታወሳል።

በወቅቱ የሲዳማ እና የኦሮሞ ሽማግሌዎች የተለያዩ ሰጦታዎችን የተለዋወጡ ሲሆን፤ በሲኣን ኣዘጋጅነት መጋቢት 20 ላይ በምከሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

መድረክን በመወከል የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ካላ በቀለ ገብረሃና እና ሌሎች 6 የድርጅቱ ኮሚቴዎች ይገኛሉ። እንድሁም ከሌሎች ኣጋር የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የደቡብ ህብረት ተወካዮች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉኤው የድርጅቱን ኣባላት ያነቃቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የሲዳማን እና የኦሮሞን ህዝብ ታሪካዊ ግንኙነት እና ኣንድነት ያጠናክራል ተብሎ ይታመናል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር