የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በትምህርት ጥራት ላይ እየሰራሁ ነኝ ኣለ

Ethio-American School Hawassa-Yirgalem

በሃዋሳ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተደረገው ጥረት ለውጥ እየመጣ ነው

ሀዋሳ መጋቢት 1/2006 በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና መጠነ ማቋረጥ ለመቀነስ  በተደረገው ጥረት  አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ገለጸ፡፡
በመምሪያው የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ደገፉ እንደገለጹት የትምህርት ጥራት ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ ከወላጆች ቦርድ፣ ከመምህራንና ተማሪዎች ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ ናቸው፡፡
በዚህም በርካታ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራሞች በመጀመራቸው የተማሪዎች ውጤት በየአመቱ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡
ባለፈው አመት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ 8ሺህ 643 ተማሪዎች መካከል 72 በመቶ ወደ ቀጠዩ ደረጃ መሸጋገራቸውንና ይህም ከቀዳሚው አመት ጋር ሲነፃፀር 8 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በተመሳሳይ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከተቀበሉ 5ሺህ 986 ተማሪዎች ከ83 በመቶ በላይ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ጠቁመው  በየአመቱም እድገት ማሳየቱን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
ትምህርታቸውን ጀምረው የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምስት በመቶ በታች ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡
በተለይ የወላጆች ቦርድ፣ መምህራንና የትምህርት ቤት ኮሚቴዎች በየወቅቱ በትምህርት ጥራት ፓኬጅ ዙሪያና በሚከሰቱ ችግሮች  እንዲሁም መፍትሄዎቻቸው ላይ በመወያየት ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የጋራ ጥረትም ከ115 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡
ከከተማው ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን መካከል እንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ባለድርሻ አካላት በተለይም የወላጅ መምህራን ህብረት፣ የቀበሌ ትምህርትና ስልጠና ቦርድ ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ለትምህርት ስራ ተቀናጅቶ የሚያደርጉት ድጋፍ ለዘርፉ እድገት ቁልፍ ድርሻ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡
ከተማሪዎችም መካከል ሙሴ ማቴዎስ ፣ ዮርዳኖስ ሰለሞንና ዳዊት ዮሴፍ ትምህርት ቤቶቻቸው የትምህርት ጥራት ለመጠበቅ እያደረጉት ያለው ጥረት ከበፊቱ የተሻለ ለውጥ እንዳመጣላቸው ተናግረዋል፡፡
በአንድ ለአምስት ቁርኝትና በልማት ቡድን ተደራጅተው በክፍል፣ ከክፍል ውጭና በየሰፈሩ በጋራ ተቀናጅቶ የሚያደረጉት ጥረት እንዲሁም ወላጆች የስራ ጫና በመቀነስና እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ዘውትር በመሄድ የሚሰጣቸው ድጋፍ ውጤታቸውን ለማሻሻል እንደረዳቸው ተማሪዎቹ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦ http://www.ena.gov.et

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር