የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምደባ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠሩ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚመደቡበት ወቅት የሚደረጉ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠረብን ነው አሉ ዩንቨርስቲዎች።
ዛሬ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪጅስትራር የተውጣጡ ባለሙያዎች ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ፥ የትምህርት ክፍሎች ካላቸው አቅም በላይ እና በታች የተማሪ ቁጥር መመደብ እንደ ክፍተት ተነስቷል ።
ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጓቸው አካል ጉዳተኞች ፤ ሴቶች እና ሌሎችም መረጃን በአግባቡ ባለመሙላትም የሚፈጠሩ ክለሳዎች ፥ ዩንቨርስቲዎችን ለተጨማሪ ስራና የጊዜ ብክነት እየዳረጉ ስለሆነ ሊቀረፍ ይገባል ብለዋል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሪክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሄር በበኩላቸው ፥ የተነሱትን ሀሳቦች በመያዝ ለቀጣይ ምደባ የተሻለ ነገር ለመስራት አልሞ የተዘጋጀ መድረክ በመሆኑ እንደ ግብአት ወስደን የተሻለ ጥራት ያለው ስራ ለመስራት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።
በውይይቱ የተማሪዎች ምደባ አፈፃፀም መመሪያ ማሻሻያ ላይ ውይይት ይደረጋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር