አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ከመድረክ አባልነት በጊዚያዊነት ታገደ፤ የሲዳማ አርነት ንቅናቄን በአዲስ አባልነት ተቀበለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣  2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ትናንት 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ከመድረክ አባል ፓርቲነት በጊዜያዊነት እንዲታገድ ጉባኤው መወሰኑንም የመድረክ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡
የመድረክ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና እንደተናሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የመድረክን መግባቢ ሰነድ በሚጻረር መልኩ የሰጡትን መግለጫ በይፋ እንዲያስተባብሉ ቢጠየቁም ባለማስተካከላቸው አንድነት በጊዜያዊነት ከመድረክ አባል ፓርቲነት ታግዶ እንዲቆይ በጉባኤው ተላልፏል።
የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በበኩላቸው የመድረክ ውሳኔ ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡
አንድነት የሚያስተባብለው ነገር የለም ብለዋል።
እንድም የሰጠነው አስተያየት የለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ እንደ ተቋም መድረክን ገምግመን ሰጥተናል፤  እገዳው ለምን እንደሆነ አልገባንም ብለው ለኢሬቴድ ገልጸዋል።
ጉባኤው የሲዳማ አርነት ንቅናቄን  በአዲስ አባልነት ተቀበሏል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር