በሃዋሳ ከተማ የኣንዳንድ መንደሮች ነዋሪዎች በራስ ተነሳሳሽነት መልካምኣስተዳደርን ለማምጣት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የክልሉን መንግስት ትኩረት መሳቡ ተነገረ


በሃዋሳ ከተማ የኣንዳንድ መንደሮች ነዋሪዎች በራስ ተነሳሳሽነት መልካምኣስተዳደርን ለማምጣት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የክልሉን መንግስት ትኩረት መሳቡ ተነገረ

ሪፖርተራችን ቱንስሳ ጂሎ ከሃዋሳ እንደዘገበው፤ በሀዋሳ ከተማ በባህል አዳራሽ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የታረቀኝ፣ የዳንዲ ቦሩ፣ የአረጋውያንና የግራር መንደር ነዋሪዎች በአንድ ለአምስት በመደራጀት ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ የዝርፊያና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም በትምህርት ፣በጤናና በግብር ዙሪያ ሌሎች ቀበሌዎች ኣርኣያ የሆኑ ተግባራትን በማከናውን ላይ ናቸው።

እነዚህ መሃል ከተማ መንደሮች ከዚህ በፊት በጸጥታ እና በሌሎች ችግሮች የሚታወቁ እና የመደሮቹም ነዋሪዎች በዘርፎብዙ ችግሮች ይሰቃዩ የነበሩ ናቸው።


ሰሞኑን በክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር  በኣቶ መለሰ ኣለሙ የተመራ ኣንድ የመንግስት ኣካል የመደራቱን የስራ እንቅስቃሴ የጎበኘ ሲሆን፤ በስራ ኣፈጻጸማቸው መደሰቱን እና በሃዋሳ ከተማ የሚታዩ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመፍታት ነዋሪው የተለያዩ አደረጃጀቶች በመጠቀም እያከናወነ ያለውን ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት ብለዋል። 
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በበኩላቸው እንዳሉት የአራቱ መንደር ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት በመንደሮቹ ያለውን የመንገድ ችግር ለማቃለል ከመቶ ሺህ በላይ ብር በማዋጣትና ከከተማው አስተዳደር ጋር በመተባበር ጠጠር በማልበስና ሌሎች የልማት ስራዎችን በማከናወን  ከጠባቂነት ለመላቀቀ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። 
መንግስት በከተሞች መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እያከናወነ ያለውን ተግባር ለማገዝ የመንደሮቹ ነዋሪዎች እየሰሩት ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትነ አምልክተዉ ይህን ስራቸውን ለማገዝ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። 
በአራቱ መንደሮች የተመሰረቱ የአንድ ለአምስት ትስስሮች በትምህርት ፣በጤና፣ በግልና አካባቢ ንጽህና፣በጸጥታ በግብርና በሌሎች መስኮች በራሳቸው ተነሳሽነት የተለያዩ ተግባራት እያከናወኑ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት የተጠቆመ ሲሆን መንደሮቹን በሞዴልነት ለማስመረቅ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸዉን ሪፖርተራችን ቱንስሳ ጂሎ ከሃዋሳ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር