በሃዋሳ ከተማ የትምህርት ቤቶች የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች አውደ ረኢ ተከፈተ

ሀዋሳ የካቲት 20/2006 ትምህርት ቤቶች የነገዎቹን ተመራማሪዎች፣ ሳይንቲስቶችና የልማት አርበኞች ማፍሪያ ስፍራዎች መሆናቸውን በተግባር እያሳዩ እንደሚገኙ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ገለጹ፡፡
ሁለተኛ ዙር የሃዋሰ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች አውደ ረኢ "ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ማዕከላት ይሆናሉ በሚል መሪ ቃል ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተከፍቷል፡፡
መንግስት ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች የሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራን ለማሳደግ  ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑን የአውደ ረኢው ተሳታፊና የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎች ገልፀዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር  ምክትል ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አስተዳደሩ ለትምህርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት አገልግሎቱን ለሁሉም ዜጎች በፍትሃዊነት ከማዳረስ አኳያ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በዚህም በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከልማዳዊ አሰራር ተላቀው በተደራጀ መንገድ ሁሉንም  ባለድርሻ አካላት በተልዕኮ ዙሪያ በማሰለፍ የተማሪ ውጤትን ለመቀየር በሚያስችል የውድድር ሂደት ውስጥ  ተገብቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በከተማው ትምህርት ቤቶች የሚታዩት ሰፋፊ የፈጠራ ስራዎች የትምህርት ፖሊሲውና ፓኬጅ ትግበራ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቁመው እነዚህ አበረታች ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በተማሪዎች እየተሰሩና  ለህብረተሰቡ በአነስተኛ ዋጋ በጥራት የሚቀርቡ የፈጠራ ስራ ውጤቶች ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለመድረስ ያስቀመጠችውን ግብ ማሳካት እንደሚትችል በተግባር እያሳየ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዬ ቢሊሶ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ትምህርት ቤቶችም ለሳይንስ ፣ለሂሳብና
ለፈጠራ ስራዎች መጎልበት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በከተማው ጠንካራ የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት የትምህርት ጥራትንና ብቃትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በርካታ ሞዴል ትምህርት ቤቶች ማፍራት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ከአውደ ረኢው ተሳታፊዎች መካከል ተማሪ ተስፋማርማይ ገብሬ ፣ዳዊት ዮሴፍና ይዲድያ ይሄይስ በሰጡት አስተያየት ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግስት ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች የሰጠው ልዩ ትኩረት ለፈጠራ ስራዎች ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ቤቶቹ የሳይንስና ፈጠራ ማዕከላት መቋቋም ፣ፍላጎትና ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲበረታቱ ማድረጉን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
አውደ ረኢ ተዘጋጂቶ ስራዎቻቸው ለህብረተሰቡ እንዲታይ በመደረጉ ለፈጠራ ስራ ያላቸው ዝንባሌ እንደሚያሳድገው አስረድተዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ረኢ ላይ 26 የመንግስትና 19 የግል ትምህርት ቤቶች ተሳትፈዋል፡፡
ለአራት ቀናት በሚቆየው በዚሁ አውደ ረኢ ላይ በተማሪዎችና በመምህራን የተዘጋጁ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ለህዝብ ክፍት ሆነው ቀርቧል፡:

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር