ከአዲስ አበባ በሃዋሳ ኣድርጎ እስከ ሞምባሳ የሚዘረጋውን መንገድ ኢትዮጵያና ኬንያ እያፋጠኑ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) አፍሪካን እርስ በእርስ የሚያገናኘው መስመር አካል የሆነው መንገድ ከኬፕታውን እስከ ግብጽ ሲደርስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራትን  ያቋርጣል፡፡
የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም የዚህ የአፍሪካ ሀገራትን  በመንገድ እርስ በእርስ የማስተሳሰር ዓላማ አንድ አካል ነው፡፡
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን ኬንያ ከሞምባሳ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ እንዲሁም ኢትዮጵያ ደግሞ ከሞያሌ ድንበር  እስከ ዋና ከተማዋ እየሰሩ ነው፡፡
500 ኪሎ ሜትር ለሚረዝመው መንገድ የሚያስፈልገው 5.3 ቢሊዮን ብር በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እንደሚለው የዚህ መንገድ ሲቪል ስራዎች በቅርቡ እንደሚጀመር ነው የገለጸው፡፡
የሞምባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ከፍተኛ መንገድ ሲጠናቀቅ በሁለቱ ሐገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ በጎርጎሮሳውያኑ 2017 በ200 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኢሬቴድ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር