የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በወቅታዊ የፖለቲካ ኣካሄዱ ላይ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ




መግቢያ
የሲዳማ ህዝብ የትግል ታሪክ እንደሚያሳየው የሲዳማ ህዝብ እንደማንኛውም ጭቁን ህዝቦች ለነፃነትና ዴሞክራሲ መስፈን ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ አሁን ለሚታየውም አንፃራዊ መረጋጋት አያለ የህዝብ ልጆች ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ አኩሪ የታሪክ አሻራ አስቀምጠው አልፈዋል፡፡ ምንም እንኳን የተከፈለው መስዋዕትነት ከፍተኛ ቢሆንም የሲዳማ ህዝብ እስከ አሁን ድረስ የተሰዋለትን ነፃነት ፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ብሎም አስተዳደራዊ ነፃነት እንደተነጠቀ ዘመናትን አስቆጠረዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላላፈው የነፃነት ትግልም እስከ አሁን ድረስ የቀድሞውን ቁልፍ የህዝብ ጥያቄዎችን በማንገብ የሚነሳውን የአሁኑን ትውልድ ደም እያፈሰሰ፣ የሕይወት ዋጋም እያስከፈለ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክሮ ቀጥለዋል፡፡

ስለዚህ የሚያባሪር ካልቆሜ የሚሸሽ ስለማይቆምም(shorrannohu uurrikkinni xooqannohu diuurranno) እንደምባለው የህዝብን ታሪካዊ አደራ ከዳር ለማድረስና ሰላማዊ ትግል ለማቀጣጠል በየደረጃው የሚገኙ የሲአን አመራርና መላው የሲዳማ ህዝብ ብሎም የትግሉ ደጋፊ የሆኑ የሌላ ብሔር አባላት ከምን ጊዜውም በላይ መጠናከር ወሳኝ ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር የሲአን ከፍተኛ አመራርም የድርጅቱን አላማ አንግቦ ይበልጥ ወደ ህዝብ መድረስ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን አንገብጋቢ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ክፍል አንድ
የትግል ማጠናከሪያ አንኳር ዘዴዎች፡
1.
የውስጥ አደረጃጀት ማጠናከር፣

ከሌሎች ትክክለኛና ተቀራራቢ የትግል ዓላማ ካላቸው ተቃዋም ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተዳደሪያችን ደንብና ፖለቲካ ፕሮግራማችን መሠረት በጋራ መስራት ይገኝበታል፡፡ የውስጥ አደረጃጀትን ማጠናከር አብዘኛው የዓለም ታሪክ እንደሚያሳየው የአንድ ሀገር ነፃነት ዋና አቀጣጣይና የለውጥ መሪ መሆን ያለበት ተጨቋኙና የተገፋው ማሕበረሰብ መሆን እንዳለበት ያሳያል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የትግል መሪ ተጨቋኙ ማሕበረሰብ ካልሆነና በውስጥ ጥንካሬ ያልተደራጀ ትግል መልኩን የለወጠ በደልና ጫና የበዛበት እንደምሆን የኛ የሲዳማ ህዝብ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ በተጨማሪም እኛ፤ በኛ፤ ለራሳችን ከሚንቀዳጀው ነፃነት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ አሰራር ውጪ ማንም፣ መቸም ለሲዳማ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ መስፈን የሚታገልልን እንደለለና ሊኖርም እንደማይችል ሁሉም የሲዳማ ህዝብ ጠንቅቆ እንዲያወቅ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ የሲዳማ ህዝብም ከምንም ጊዜው በላይ በፋይናንስ፣ በአቅም ግንባታና አደረጀጃት የውስጥ ጥንካሬውን ለመጠበቅ ትክክለኛ መረጃ በመስጠትና በመቀበል፤ የመሪነትና የባለቤትነት ስሜት መላበስ፤ የአካባቢና የሀብት ጥበቃ ለማድረግ የነቃና ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ ይህንን ውጤታማ ለማድረግና ህዝባዊ ዓላማ ለማሳለጥ ድርጅታችን የሲዳማን ክልል በሳባት ሰፋፊ ዞኖችን በማደራጀት እየሰራ መገኘቱ የጥረቱ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችን መሪ፣ ባለቤትና የሚገባን ነን!!፡፡

2. ከሌሎች ትክክለኛና ተቀራራቢ የትግል ዓላማ ካላቸው ተቃዋም ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተዳደሪያችን ደንብና ፖለቲካ ፕሮግራማችን መሠረት በጋራ መስራት በፖለቲካ ዓለም እንደሚታየው ድርጅቶች የተለያየ የትግል ዓላማ አንግቦ ለትግል ይነሳሉ፡፡


አንዳንዶች በርዕዮተ-ዓለም አንድነትና ልዩነታቸው መሠረት የትግል ጎራ መርጠው የርዕዮተ-ዓለሙ ተስማሚ የሆነ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካዊና ማህበራዊ ፖሊሲያቸውን መንግሥት ሆነው ለመተግበር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ምክንያታዊ ጎራ ከፍሎ መንቀሳቀስና የሀሳብ የበላይነትን ማረጋገጥ ጤናማ የፖለቲካ አሰራር በመሆኑ ድርጅታችን የራሱን የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ በአዲስ መልክ በመቅረፅ በተጠናከሬ መልኩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ከርዕዮተ-ዓለም በላይ በመሆኑና የነፃነትና የዴሞክራሲ ጉዳይ ቢሆንም የራሳችንን የፖሊሲ አቅጣጫ በመጠቆም ከድርጅታችን ፕሮግራም ጋር የሚቀራረቡ የፖለቲካ ድርጅቶችን በጥልቀት በመፈተሽ በጋራ ተባብሮ መስራትም ጊዜ ሊሰጥ የሚገባ እንዳልሆነ የሀገርቱ ተጨባጭ ሁኔታ ፍንትው አድርገው ያሳያል፡፡ ለአብነት የሲዳማ አርነት ንቅናቄ በግል ባደረገባቸው የትግል ጊዜያት የተጎናፀፋቸው ስኬት እንደተጠበቀ ሆኖ በአንጻሩ ደግሞ ያጋጠሙት በግል የመጋፈጥ ፈተና ተጠቃሽ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት በግል በታገለባቸው የትግል ጊዜያት የታዘባቸውንና ያጋጠሙትን ፈተናዎች ግምት ውስጥ በማስገባት በተለይም የኢህአዴግን የጥፋት ጡንቻን ይበልጥ ለመቋቋምና ለድል ለመብቃት በዓላማ ከሚቀራረቡ ፖለቲካ ድርድቶች ጋር መተባበር አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ባደረገው ጥልቅ ግምገማና ተሞክሮ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡


ከፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚደረጉ የጋራ ስምምነቶች፣ አይነትና ልዩነት ከተሻሻለው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ድንጋጌ መሰረት፡-


ትብብር -የአጭር ጊዜ ለጊዜያዊ ጉዳይ የሚደረግ አንድነት ሆኖ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚሰጥ ማንኛውም እውቅና የለውም፤
ቅንጅት -የአጭር ጊዜ ለጊዜያዊ ጉዳይ(አጀንዳ) የሚደረግ ትብብር ሆኖ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚሰጥ የእውቅና ሰርተፍከት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፤


ግንባር-ግንባር ለመፍጠር የተስማሙ ፖለቲካ ድርጅቶች ህሊውናቸውን ሳይለቁ በዓላማቸው(መለስተኛ ፕሮግርም) መቀራረብ ተቃኝተው ለጋራ አላማ የሚሰሩበት አንድነት ነው፡፡ ወደ ውህደት ለማደግ ካልወሰኑ በስተቀር በግንባር የተሳተፉ ፖለቲካ ፓርቲዎች በግንባሩ አስፈላጊነት ላይ እምነት ካጡ በራሳቸው ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ለቆ መውጣት ይችላሉ፡፡


ውህደት-ለመዋሄድ የተስማሙ ድርጅቶች የነበራቸውን ህሊውናቸውን በማጣት አዲስ በሚፈጥሩት ድርጅትና ፍፁም የጋራ ለሆነ ፕሮግራም የሚመሩበት አንድነት ነው፡፡

በግንባሩ መመስረት አስፈላጊነት ላይ የሲአን አቋምና እርምጃ በአሁን ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ህዝባዊ ስርአት ለማስፈን በሠላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በግል ከመታገል ይልቅ ሀይል በማስተባበር በግንባር ወይም በውህደት የመታገል ስልት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ በመወሰናቸውና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ በተናጠል የሚደረግ ትግል መሄድ የሚገባውን ርቀት ተጎዞ ያጠናቀቀ መሆኑን በመረዳት ጊዜ ወስዶ ሲያደርግ የነበረውን ጥናት በማጠናቁቁ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ካሉ አመራሮቹና አባላቱ ጋር መክሮ የግንባር መመስረት አስፈላጊነትን ያለ ልዩነት ተቀብሏል፡፡


ግንባሩ ለሲአን ትግል ስኬት የሚያስገኘው ጥቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲዳማን እንደ ብሔር እና ሲአን እንደ ሲዳማ መሪ ድርጅት የሚኖረውን ድርሻ ለማስጠበቅ እና የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት በሀገር ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ መድረኮች በማጋለጥ ለመታገል አቅም ይፈጥራል፡፡

በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ለምደግፉት በተለያየ መወዳደሪያ ምልክት ለሚወዳደሩት ፓለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል የምሠጡት የምርጫ ድምጽ በአንድ መወዳደሪያ ምልክት ለአንድ ግንባር ለፈጠር ፓርቲ ስለሚሠጡ የማሸነፍን እድል ያሰፋል፡፡ መድረክ ፓርቲ በምርጫ በማሸነፍ መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር ካገኘ ሲአን ራሱ በመሰረተው መንግስት የመመራት መብትን ያስጠብቅለታል፡፡ ሲዳማ ለዘመናት ሲታገል የኖረውን ክልላዊ መንግስት ይመሰረታል፤ ለሲዳማ በፌዴራል መንግሰት በልመና ሳይሆን በመብቱ የስልጣን ውክልናና የማስተዳደሪ አቅም ይፈጥርለታል፡፡


ማጠቃለያ
በኢትዮጵያ ያለው ስርአት የደረሰበትን ጨቋኝና አፋኝ የአስከፍነትን ደረጃ ግምት ውስጥ በማስገባት የትግል አቅጣጫችንን በጥልቀት መገምገምና መፈተሽ ጊዜ ሊሠጠው የሚገባ ጉዳይ እንዳይደለ ድርጅታችን ጠንቅቆ በማወቅ እየሰራ ይገኛል፡፡ ለዚህም ጠቃምና ወሳኝ የሚባሉትን የውስጥ መጠናከርንና የህዝብ ግኑኝነቶቻችን የበለጠ ከማጉላታችንም በተጨማሪ በፖለቲካ ፕሮግራማችንና መተዳደሪያ ደንባችን መሠረት ተቃኝተው ተቀራራቢ ከሚሆኑ ክልላዊና ሀገራዊ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መስራትም ወሳኝ ተግባር መሆኑን አግኝተዋል፡፡

ስለዚህ ሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከመድረክ ግንባር ጋር ግንባር ፈጥረው ለመስራት ካሰበበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የመተዳደሪያ ደንባችንና ፕሮግራማችን ጋር ያለውን ልዩነትና ተቀራራቢነት በጥልቀት ከፈተሸን በኋላ ከልዩነታችን ይልቅ ተቀራራቢነታችን ማመዘኑን ሊገነዘብ ችለዋል፡፡ የድርጅቱ አመራርም ያለውን አንፃራዊ አስፈላጊነት ለማዕከላዊ ጉባዔ በማቅረብ በጥልቀት ካወያየ በኋላ ማዕከላዊ ጉባዔ ለድርጅታችን ጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ ይሁንታ እንዲያገኝና በአስቸኳይ ወደ ስራ ልገባ እንደሚገባም ጭምር ባሳሰበው መሰረት በ17/05/2006.ም ሊቀርብ ችሏል፡፡

የቀረበውም ይህ ታሪካዊ አጀንዳ በሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲኣን) ጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፈዎች ስለጉዳዩ በስፋት ከተወያዩና ሀሳብ ካንሸራሰሩ በኋላ በሙሉ ድጋፍ አፅድቋል፡፡ በሌላ በኩል በውስጥ አደረጃጀት ስለተነሳው ሀሳብም ጉባዔው በሰፈው ከተወያየ በኋላ በመነሻ ሀሳብ ረቅቂ እንደተገለፀው ምንም እንኳን ከተቀራራቢ ፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል የሚደረግ ህዝብ ግኑኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሚታመንና ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ብሆንም የውስጥ መደራጀትና የየእለት መረጃ የማግኘትና ስለአካባቢያችን ነቅተን መከታተል ለአመራር ብቻ የሚተው ስላይደለ ሁሉም ሴት፣ ወንድ፣ ወጣትና ሽማግሌ ሳይባል ስለሀገሩ መቆርቆርና በከተማና ገጠሩ የሚፈፀመውን ነገር ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት አፅኖዖት ሰጥቶ ተወያይተዋል፡፡

በመጨረሻም ስለሲዳማ ህዝብም ሆነ ስለመልካዓ-ምድራችን ጠንቅቀን ስለምናውቅ ከእናንተ የምንፈለገው ስለሚሆነው ነገር ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ብቻ ነው በማለት ከህዝብ ወደ መድረክ ብሎም ለአመራር ጥብቅ ማሳሰቢያ በመስጠት ጉባዔው በአስደናቂ ሁኔታ ተጠናቀዋል፡፡
ክፍል ሁለት
የሲዳማ ህዝብ ብሎም የሲአን ታሪካዊ ውሳኔ አንደምታ በሥራዐቱ(ኢህአዴግ) ታማኝ አቀንቃኞችና በተቀረው ሲዳማ ህዝብ ብሎም አብሮ ነዋሪው ህዝቦች ዘንድ፤ በሥርዐቱ ታማኝ አቀንቃኞች ዘንድ የሚኖረው አንደምታ፤ በሁሉም የሲዳማ ማኅበረሰብ ብሎም በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በገሐድ እንደሚታወቀው ኢህአዴግ የሀገር ውስጥ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠቀማቸው ለመድበለፓርቲ ስርዓት በኢትዮጵያ እንዳለና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳሰፈነ ለውጭው ዓለም ለመደስኮር እንጂ ጠንክሮና ጎልብቶ ለሀገር ዴሞክራሲና ከዚህም በተጨማሪ ከኢህአዴግ ሥርዓት ውጪ ያለውም ሆነ የሚመጣው ስርዓት ሀገር ውዳሚና አጥፊ መሆኑን ደጋግሞ በመደስኮር ለቀጣይ 45 ዓመታት ያለምንም ተቀናቃኝ ህዝቡን በስጋት ቆፈን ውስጥ ይዘው ለማቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

ለአብነት እንኳን በቅርቡ ከየቀበሌው ተወከሉ የተባሉትን ነገር ግን አስፈራርተው በሰበሰቧቸው ጭቁን ሲዳማ ህዝብ ላይ በኢትዮጵያ የነበረው ሥርዓት ከአፄ ምንልክ ጀምሮ አፋኝ እንደሆነና እነርሱ(ኢህአዴግ) ብቻ የሀገር አለኝታ መሆኑን፤ በአንፃሩ ደግሞ ሌሎች የሀገር አፍራሽና ጠላት መሆናቸውን ደጋግሞ በመናገር ህዝቡ ተስፋ ቆረጦ ኢህአዴግን በግዴታ ውዴታ ተቀብሎ እንዲቀመጥና እንዲገብር የማድረግ ጥረታቸውን መቀጠላቸው ጥሩ ማሳያ ነው፡፡


በሌላ በኩል ተፈላልገው የሚደራጁ ፖለቲካ ፓርቲዎች በልኩ(ኢህአዴግ በሰፋው ቁንጣ ውስጥ ካልገቡ) ካልሆኑና ኢህአዴግ ጥላ ስር ካልሆኑ አሸባሪ፤ የሀገር ጠላት፣ ጠባብ፣ ዘረኛና ወዘተ አድርገው ይፈርጃሉ፡፡ በተጨማሪም እውነተኛ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተባብሮ፣ተቀናጅተው፣ግንባር ፈጥሮ ወይም ተዋህዶ የሚንቀሳቅሱ ከሆነ የስጋት ጥላሼት በመቀባት ከህዝብ ለመለየት የማይፈነቅለው ቋጥኝ የለም፡፡ ስለዚህ "የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጣጣ" እንደሚባለው ሰሞኑን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባዔ ያሳለፈውን ታሪካዊ ውሳኔና የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ውጥረት ያስደነገጠው ገዢው መደብና ተከታዮቻቸው አዋጭ ነው ብሎ የሚያስቡትን የማደናገሪያ ዘዴ ሁሉ እንደምጠቀሙ ይጠበቃል፡፡ ከክፉ ሙገሳ አይጠበቅምና የማጠልሸት ስራቸውን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ እንደሚያናፍሱ አያጠራጠርም (Hamashshu godowinni Caacurre diagadhinanni yaanno sidaamu manni).



ከእነዚህ ከስርአቱ አቀንቃኞች የሲዳማ ህዝብ መረዳት ያለበት(ከማይረዱት ተላላኪዎች በስተቀር) የሚያናፈሱት ፕሮፓጋንዳ ሊሞቱ እየተጣጣሩ መሆኑን ጠቋሚ ምልክት መሆኑን ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም አስተዋይ የሆነው ሲዳማ ህዝብ ያለሙትን እርኩስ ሴራቸውን ቀድሞ በመረዳት ቀዳዳውን ሁሉ በማጥፋት ይበልጥ መፈናፈኛ ማሳጣት ከነፃነት ናፋቂ ሲዳማ ህዘብ የሚጠበቅ አንኳር ቁምነገር ነው፡፡ ይህንን እንደሚያደርግም የድርጅታችን ሲአን እምነት ነው፡፡


በተቀረው ሲዳማ ህዝብ ዘንድ የሚኖረው አንደምታ በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ማዕከላዊነት(Globalization) አይደለም የጋራ ጠላት በተባበረ ክንድ ለመገርሰስ ይቅርና በባህል፣ በገበያ፣ በተለያዩ ኑሮ ዘይቤዎችና በመሳሰሉት ጉዳዮች ወደ አንድነት እየተሳቤ ያለበት ክፈለ-ዘመን ላይ እንገኛልን፡፡ ሲዳማ እንደ ብሔር እና ሲአንም እንደ ሲዳማ ህዝብ ታሪካዊ መሪ ድርጅት እንደመሆኑ ያለበት ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መረገጥ መረሳትና መዘረፍ ችግሩን ከማንኛውም ተባባሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማጋለጥ አግባብና ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ መላው የሲዳማ ህዝብ የሚያረካ እንደሆነና የሲዳማ ማኅበረሰብም በዚህ ዙርያ አቋሙ ፅኑ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

በጋራ መሥራትና የሚገባውን ተደራድሮ ማስጠበቅ የሰለጠነና በራሱ የሚተማመን ግለሰብ ወይም ድርጅት ውሳኔ እንደሆነም የሲደማ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የህዝብ ንቃተ ህሊና የደረሰበት ደረጃ ያልገባቸው አንዳንድ የሥራዓቱ አቀንቃኞች ህብረተሰቡን ለማደናገር ሆን ብሎ ሲአን ከዚህ በኋላ አይኖርም፣ መንግሥት በሀገር ደረጃ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ልቀንስ(ልጨፈልቅ) ነው በማለት መንግሥት የሌለውን አቅም በመካብ ህዝብን የማስጋት ሴራ እየተናፈሰ እንደሆነ የየወረዳ የድርጅታችን ጽ/ቤቶች ሪፖርት ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይንን የተደናገረውን ሥርዓት ይበልጥ ምክንያታዊና ሰላማዊ በሆነ አቀራረብ በማስጨነቅ ውድቀታቸውን እንዲያፋጥን የድርጅታችን እምነቱ የፀና ነው፡፡

ድል ለተበደለው ሲደማ ህዝብ!

ሲዳማ በኛ፤ ለኛ ትለማለች!

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር