የይርጋለም ከተማ የንጽህ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት መቼ ይሁን የምጠናቀቀው?

ኣንድ ሚሊዮን ለምጠጉ ይርጋለም ከተማ እና ለኣከባቢዋ የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች ኣገልግሎት ይሰጣል ተብሎ፤ 50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው የውሃ ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች ከሚጠበቀው በላይ ተጓቷል።

ይህ የውሃ ፕሮጀክት 60 ሊትር በሰከንድ ወይም ሺ 142 ሜትር ኪዩብ በቀን የመስጠት አቅም ያለው እና እስከ 2012.ም ድረስ ለ898 ሺ ያህል የከተማዋ ሕዝብ አገልግሎት ለመሥጠት ያስችላል መባሉ ይታወሳል

እንደ ኣዲስዘመን ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ፤ የውሃ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ከቧንቧ መገጣጠሚያ አካል (ፊቲንግአቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ መጓተቱን የሥራ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡

አምስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ካሉት ፕሮጀክት መካከል ሁለቱ በጄነሬተር ሥራ ቢያስጀምሩም ሌሎቹ ግን ውሃ መስጠት አልቻሉም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ውሃ መግፋት የሚያስችል በቂ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት ነው።

 «ትራንስፎርመር ለማስተከል ክፍያ የፈፀምነው በ2003 .ም ቢሆንም እስካሁን ከአንዱ በቀር ምላሽ አልተሰጠንም» የሚሉት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች፤ በዚህ ምክንያት ህብረተሰቡ በቂ ውሃ ማግኘት አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ትራንስፎርመር ቢተከልም በሶስት ቀን ውስጥ እንደፈነዳና አገልግሎት እንዳቆመ ይናገራሉ፡፡ የፈነዳውን ለማስለወጥ ያደረጉት ጥረት ምላሽ አለማግኘቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

እንደጋዜጣው ዘገባ፤ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ የገበያና ሽያጭ ኃላፊ አቶ ታደሰ መርጋ፤ ከፍላጎት መጨመር ጋር ተያይዞ ወረፋ መኖሩን ገልፀው፤ «ፈነዳ» ስለተባለው ትራንስፎርመር ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው፤ መስሪያ ቤቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ የውሃ አገልግሎት መሆኑን ያመለክታሉ፤ የሚቀርቡት የትራንስፎርመር ጥያቄዎች በርካታ በመሆናቸው ሊዘገይ እንደሚችል ይጠቁማሉ። በመሆኑም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የትራንስፎርመር ምርት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኩል እየቀረበ መሆኑን ያስረዳሉ። «ችግሩ ሙሉ ለሙሉ መቼ ይቃለላል?» ለሚለው ጥያቄ ግን «በተቻለ መጠን ከሌሎች ጥያቄዎች ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ብለን ቁርጥ ያለ ቀጠሮ መስጠት አንችልም፡፡ በመሆኑም በትዕግስት ይጠብቁን» ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ የውሃ ፕሮጀክት መገንባት በተለይ በዳሌ እና በሃንጣጤ ወረዳዎች ውስጥ ለምገኙት የውሃ እጥረት ያለባቸው ቀበሌያት ነዋሪዎችን መልካም ዜና ቢሆንም መጓተቱ ደግሞ ነዋሪዎችን ኣሳስቧቸዋል።



Comments

  1. Well the priority of the regime in power isn't satisfying the interests of Sidama people and others inhabit this town. What must the way forward has to be for the people to have their interests are met at least to the acceptable level??

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር