ሰበር ዜና : የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን የጠለፈው ረዳት አብራሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ሰኞ ማለዳ (የካቲት 10) ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ሲያመራ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቭ እንዲያርፍ ያስገደደው የአውሮፕላኑ ረዳት አብራሪ በጄኔቭ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
የበረራ ቁጥር ET 702 አውሮፕላን የጠለፈው ረዳት አብራሪ በስም ባይጠቀስም ተገዶ ባረፈው አውሮፕላን ውስጥ የሚገኙት ተሳፋሪዎችም ሆኑ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡
ሮይተርስ ቀደም ብሎ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን አውሮፕላኑ በሱዳን መዲና ካርቱም በኩል ማለፉንና ምናልባትም ጠላፊው ወይም ጠላፊዎቹ ከዚያው ሳይሳፈሩ እንዳልቀረ ተናግረው ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ በተገኘው መረጃ ጠላፊው ረዳት አብራሪው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር