የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለብ በዞኑ መንግስት ትኩረት ተነፍጓል ተባለ

ከሲዳማ ዞን መንግስት ትኩረት የተነፈገው የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለቡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር ያለ ውጤት ጉዞውን ቀጥሏል።

ሲዳማን በወከል በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ካሉት የእግር ኳስ ክለቦች መካከል የይርጋዓለም ከተማ ተወካይ የሆነው ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሽንፈትን ማስተናገዱን ቀጥሏል።

እስከኣሁን ደረስ ካደረጋቸው ኣስር ጫዋታዎች መካከል ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል ጋር የደረገውን  ጫዋታ ከማሸነፉ ሌላ በተቀሩት በስድስት ጫዋታዎች በመሸነፍ እና በሁለቱ ብቻ ነጥብ በመጋራት በደረጃ ሰንጠረ ኣስራ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ይገል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን የክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞ  የሲዳማ ዞን መንግስትን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኣካላት ትኩረት መነፈጉ የተነሳ መሆኑን ኣንዳንድ የክለቡ ደጋፊዎች ተናግረዋል

በጉዳዩ  ዙሪያ ሪፖርተራችን ቱንስሳ ጂሎ በይርጋኣለም ከተማ ያናገራቸው የክለቡ ደጋፊዎች እንደምሉከሆነ፤ የሲዳማ ክለቦች ያልሆኑትን እንደወላይታ ዲቻ ያሉትን በቅርብ በፕሪሜዬር ሊግ ውድድር የገቡ ክለቦችን በገንዘብ እና በሰው ኃይል ለማጠናከር በሲዳማ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲረዱ ለሲዳማ ክቦች ግን መሰል ዝግጅቶችን ኣልተደረጉም

ክለቡ ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም እና በፋይናስ ኣቅሙን በማጠናከር ውጤታማ ለማድረግ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ስለሌሉ ክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞውን ለመቀጠል ተገዷል ብለዋል።

ኣክለውም፤ ክለቡ ያሉበትን የብቃት ችግሮች ኣስተካክሎ በቀጣይ ውድድሮች ማሸነፍ ካልቻለ ከፕሪሜዬር ሊግ ውድድር መውረዱ ስለማይቀር የሚመለከታቸው ኣካላት ክለቡን በሰው እና ፋይናንስ ኃይል የማጠናከር ስራ ብሰሩ መልካም ነው።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር