በሲዳማ ዞን ሃርቤጎና ወረዳ በ250 ሚሊየን ብር ቀርከሃን ወደ ጣውላ የሚቀይር ፋብሪካ ሊገነባ ነው

  • ኢህኣዴግ ወደ ስልጣና መምጣቱን ተከትሎ በመላው ኣገሪቷ የኢንዱስትሪ ልማት በከፍተኛ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት በመካሄድ ላይ ቢሆንም የሲዳማ ዞን የዚህ እድል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፤

  • መንግስት በተለይ በሲዳማ ዞን እና በሃዋሳ ከተማ በመከተል ላይ ባለው የኣገልግሎት ኢንዱስትሪ የማስፋፋት ፖሊስ የተነሳ  ወደ ዞኑ ብሎም ወደ ከተማዋ የሚፈሰው የኢንቨስትመንት ፍስት በኣገልግሎት ስጪ ድርጅቶች ግንባታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ ዞኑ በሆቴሎች እና ሎጆች እንዲሞላ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ ኣልነበረውም፤

የሲዳማ ዞን በሃዋሳ ከተማ እና በዙሪያዋ በባለሃብቶች ከተገነቡ ጥቂት የመጠጥ እና ምግብ ፋብሪካዎች በስተቀር ለላፉት 20 ኣመታት  በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ የተረሳ ዞን ነው።

በሲዳማ ዞን ውስጥ ኣልፎ  ኣልፎ  በየወረዳዎች ከምታዩት የቡና መፈልፈያ እና ማቀነባበሪያዎች በስተቀር ለዞኑ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለውን ልማት ማስመዝገብ የሚያስችል ኣንድም ፋብሪካ የለም። ሃዋሳ እና በዙሪያዋ ያሉት ጥቂት ፋብሪካዎች ለሲዳማ ኢኮኖሚ ያበረከቱት ኣስተዋጽኦ ይሄ ነው የሚባል ኣይደለም፤ በእነዚህ ፋብሪካዎች ተቀጥረው ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የምደጉሙ ሲዳማውያን በጣት የምቆጠሩ ናቸው። በተቃራኒው መንግስት ለኢንዱስትሪ ልማት በማለት ቤት ንብረታቸውን ኣስነስቶ  መሬቶቻቸውን የነጠቃቸው ሲዳማውያን ቁጥር በርካታ ነው። 

ከዚህም ባሻገር መንግስት በተለይ በሲዳማ ዞን እና በሃዋሳ ከተማ በመከተል ላይ ባለው የኣገልግሎት ኢንዱስትሪ የማስፋፋት ፖሊስ የተነሳ  ወደ ዞኑ ብሎም ወደ ከተማዋ የሚፈሰው የኢንቨስትመንት ፍስት በኣገልግሎት ስጪ ድርጅቶች ግንባታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ ዞኑ በሆቴሎች እና ሎጆች እንዲሞላ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለው።

የሲዳማ ዞን መንግስት ለዞኑ ኢኮኖሚ ግንባታ የኣገልግሎት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለው ፋይዳ እንዳለ ሆኖ፤ የሲዳማ ዞን መንግስት  በኣገልግሎት ኢንዱስትሪ ላይ ብቻ ትኩረት ከመስጠት በሌሎች ኢንዱስትሪ ኣይነቶች ማለትን በማዕድን፤ በግንባታ፤ በኃይል፤ በቴክኖሎጂ እና በመሳሰሉት የኢንዱስትሪ ዘርፎች የዞኑን የተፈጥሮ  ሃብት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ብስራ መልካም ነው።        

ሰሞኑንን በሃርቤ ጎና ወረዳ በ250 ሚሊየን ብር ቀርከሃን ወደ ጣውላ የሚቀይር ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን የመንግስት ዜና ኣውታሮች የዘጋቡ ሲሆን ይህ መልካም ጅምር በመሆኑ ልበረታታ ይገባል።

በሃርቤጎና ወረዳ ልገነባ ነው ስለተባለው ፋብሪካ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከታች ቀርቧል፦
የቀርከሃ ጣውላን ወደ ውጭ በመላክ በዓመት 140 ሚሊየን ብር የሚያስገኝ ነው።
ፋብሪካው በሚገነባበት አካባቢ የሚገኙ አርሶአደሮች ቀርከሃን በዘላቂነት ለማምረት የሚያስችል ስልጠና እንዲያገኙና ምርቱንም ለፋብሪካው እንዲያቀርቡ በማድረግ ፤ በዓመት 30 ሚሊየን ብር የሚያስገኝ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ያደርጋል ተብሏል ።
ለ400 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል የሚፈጥረው ይህው ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት 10 ሄክታር ወስዶ የቀርከሃ ልማት ጀምሯል ።
ምንጭ፦ አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር