በሲዳማ ዞን ለባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

ሐዋሳ ጥር 20/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት ከ24 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የኢንቨስትመንት ካፒታል ላስመዘገቡ 12 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ 
በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፋፊያ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ግብርናና ኢንዱስትሪ ይገኙበታል፡፡ 
ባለሃብቶቹ ለ279 ቋሚና 788 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል ማግኘታቸውን ገልፀው ባለፈው ዓመት በተጀመረ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴም ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ 
መምሪያው ለ41 ባለሃብቶች የፍቃድ እድሳትና ተጨማሪ የማስፋፊያ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችን ድጋፍ  በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሂደት ለማመቻቸት ባደረገው ጥረት 320 ፕሮጀክቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ 
አዲስ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ከገቡ ባለሃብቶች መካከል አንዳንዶቹ ልማታዊው መንግስት እያደረገላቸው ድጋፍ በርካታ ባለሃብቶች በሃገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረግ ሌላ በድህነት ላይ በሚደረገው ዘመቻ ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ 
በሲዳማ ዞን ባለፉት 15 ዓመታት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ770 በላይ ባለሃብቶች በኢንቨሰትመንት መሰክ በመሰማራት ከ56 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠራቸውን አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜኣ 1/28/2014

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር