በሃዋሳ ከተማ ሰሞኑን የትራንስፖርት ኣገልግሎት እጥረት ተከሰቷል፤ ችግሩ የተፈጠረው በቤንዚን ኣቅርቦት እጥረት ነው ተብሏል

በከተማዋ እና በኣከባቢያዋ የትራንስፖርት ኣገልግሎት የምሰጡት በሺዎች የምቆጠሩት ባለሶስት ጎማ ተሽከርካሪዎች ሰሞኑን እንደተለመደው የትራንስፖርት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ኣይደሉም።

የሃዋሳ ከተማዋ ነዋሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትም የባዳጂ ታክሲዎች ቁጥር ጥቂት በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የእለትተእለት ስራቸውን ተንቀሳቅሰው ለማከናዎን መቸገራቸውን ኣመልክተዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ያናገራቸው የባዳጂ ኣሽከርካሪዎች እንዳስረዱት፤ ለሃዋሳ ከተማ እና ለኣካባቢዋ ነዳጅ የማከፋፈል ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ከምገኙት ከኣስር በላይ የነዳጅ ማዴያዎች መካከል ኣብዛኛዎቹ ቤንዚን ኣይሸጡም።

በኣጠቃላይ ከተማዋ ከሁለት የማይበልጡ ብቻ ቤንዚን በማደል ላይ ሲሆኑ፤ በእነዚህም ነዳጅ ማደያዎች የቤንዚህ ኣገልግሎት ፈላጊው እና ኣቅርቦቱ የተመጣጠነ ባለመሆኑ በርካታ ኣሽከርካሪዎች በረዥም ሰልፈ ጊዜያቸውን በማቃጠል ላይ በመሆናቸውን ተናግረዋል።

የነዳጅ ማደያዎቹ ሰራተኞች በበኩላቸው እንደምሉት ከሆነ፤ ቤንዚን የማደል ኣገልግሎት የማይሰጡት የቤንዚን እጥረት በመፈጠሩ ነው።



ነገር ግን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት ኣስተያየት በኣገሪቱ ውስጥ የነዳጅ እጥረት እንደሌለ እየታወቀ ሳለ በሃዋሳ ከተማ ብቻ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ጉዳዩን በጥርጣሬ እንድመለከቱ እንዳደረጋቸው ጠቁመው፤ የምመለከተው የመንግስት ኣካል መፍትሄ እንድፈልግ ጥሪ ኣቅርበዋል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር