የሃዋሳ ኤርፖርት የግንባታ ቦታ ለውጥ እና መዘዙ


  • የኤርፖርቱ ግንባታ ቦታ ለውጡን ተከትሎ የሞሮቾ ሾንዶላና ቀበሌ እና የኣከባቢው ቀበሌያት ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል።


የሃዋሳ ከተማ በተለይ ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ ከፍተኛ ሁለ ገብ እድገት በማስመዝገብ የነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን የኣገር ውስጥ እና የውጭ ኣገር ዜጎችን መሳብ መጀመሯ የምታወቅ ነው። ከተማይቱ ከኣዲስ ኣበባ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ እና ምቹ የምድር ትራንስፖርት ፍሰት ያላት መሆኑ ኤርፖርት ሳይኖራት እንድትቆይ ምክንያት ሆኗል።

የሆነ ሆኖ ሰሞኑን የመንግስት ዜና ኣውታሮች ለዘመናት ያለ ኤርፖርት የቆየችው ይችው የሲዳማ መዲና ሃዋሳ፤ የኤርፖርት ባለበት እንድትሆን ኤርፖርት ልገነባላት መሆኑን ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ የሃዋሳ ነዋርዎች እንድሁም ኣጠቃላይ ሲዳማውያን ደስታቸው በተለያየ መንገድ ስገልጹ ከርመዋል።

በኣሁኑ ጊዜ በሲዳማ የኤርፖርቱ ግንባታ ቁጥር ኣንድ የመወያያ ኣርዕስት ሲሆን፤ በተለይ የቦታ መረጣው የብዙዎቹን ቀልብ የሳበ ጉዳይ ሆኗል።

ለሃዋሳው ኤርፖርት ግንባታ ከዚህ በፊት በሸቤዲኖ ወረዳ ውስጥ ሞሮቾ ሾንዶላና ቀበሌ እና በኣከባቢው ያለው ቀበሌ ተመርጦ የነበረ ቢሆንም፤ በኣሁኑ ጊዜ ቦታው ተቀይሮ በሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ኡዶ ዎጣጤና ሳማ ኤጀርሳ ቀበሌ እንዲዛዎር ተደርጓል።

እንደሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘጋባ መሰረት የቦታ ለውጡ የተደረገው ከሞሮቾ ሾንዶላ ቀበሌ እና ከሌሎች በኣከባቢው ካሉ ቀበሌያት ለኤርፖርት ግንባታ ሲባል የምነሱ ሰዎች ቁጥር ብዙ በመሆኑ ለምነሱ ሰዎች እና ለመሬት ይዞታ ብሎም ለንብረት የምከፈለው ካሳ ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ለካሳ የምከፍለውን ገንዘብ ለማስቀረት ሌላ ኣማራጭ ቦታ መፈለግ የግድ ሰላሆነበት መሆኑ ታውቋል።

የጥቻ ወራና ዘጋባ ኣክሎ እንደምያመለክተው ከሆነ፤ ይህ ኣሁን ለኤርፖርት መስሪያነት የተመረጠው ቦታ በኣብዛኛው በግለሰቦች ያልተያዘ ባዶ መሬት መሆኑ ተመራጭ ኣድርጎታል ተብሏል። ከዚህም ባሻገር መንግስት ለንብረት ካሳ መክፈያነት ልያውለው የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለግንባታው እንድጠቀም ይረዳዋል ተብሏል።

የኤርፖርቱ ግንባታ ቦታ ለውጡን ተከትሎ የሞሮቾ ሾንዶላና ቀበሌ ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸው ተሰሞቷል።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከቀበሌያቱ ያሰባሰበው መረጃ እንደምያመለክተው፦በሞሮቾ እና የኣከባቢው ቀበሌያት ነዋር የሆኑ ግለሰቦች ኣከባቢው ለኤርፖርት ግንባታ መመረጡን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመሬት ይዞታቸው በምነሱበት ጊዜ መንግስት ንብረታቸውን ገምቶ የካሳ ገንዘብ እንደምሰጣቸው በማሰብ በርካታዎቹ ገንዘብ የተበደሩ ሲሆን፤ የተበደሩትን ገንዘብ ለተለያዩ ጉዳዮች በማዋላቸው የኤርፖርቱ ግንባታ ቦታ ለውጥ እዳ ውስጥ ከቷቸዋል።


እነዚህም ባሻገር ከኤርፖርቱ ግንባታ ጋር ተያይዞ ኣካባቢው የንግድ ማዕከል ይሆናል በሚል ኣያሌ ባለሃብቶች ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ በኣከባቢው ቀበሌያት ለንግድ ስራ የሚሆን መሬት በመግዛታ ለክሳራ ተዳርገዋል። በዚህም የተነሳ የኤርፖርቱ ግንባታ ቦታ ለውጥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ መፍጠሩ ታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር