የካንሰር ህክምና ማዕከል በሃዋሳ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9 ፣ 2006(ኤፍቢሲ)በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ስድስት የካንሰር ህክምና ማዕከላት ሊከፈቱ ነው።
የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ማዕከላቱ አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶላቸው  በመጪው መስከርም ወር ስራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።
በአሁኑ ውቅትም ከ12 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ ለማዕከላቱ የህክምና ቁሳቁስ ግዥ ለመፈፀም ሂደቱ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላቱ በጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ሀዋሳ እና በሀሮማያ የሚከፈቱ ሲሆን፥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደግሞ  ማዕከሉን የማስፋፋት ስራ እየተካሄደ ይገኛል ።
የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላቱ  መስፋፋት በመስኩ የሚሰተዋለውን የህክምና አገልግሎት እጥረት በመቀረፍ እና የካንሰር ህሙማን እንግልትን በመቀነስ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ያሰችላል ብለዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር