በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት የተደራጁ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት እንደምያሹ መግለጻቸውን ተከትሎ የዞኑ መንግስት ለማህበራቱ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ኣስታወቀ

ከሶስት ሳምንታት በፊት የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘጋብ ሪፖርተር ጥቻ ወራና '''' በምል ሃዋሳን  ጨምሮ  በሲዳማ ዞን ባሉ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት የተደራጁ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ የምቃኝ ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ የዞን መንግስት ለወጣቶቹ የገበያ ትስስር ስራ መስራቱን በመናገር ላይ ነው።

ሪፖርተራችን ያናገራቸው በጥቃቅን እና ኣነስተኛ የልማት ስራዎች የተደራጁ ወጣቶች ዘላቂነት ያለው የሙያ ስልጠና የማግኘት እና ለምርቶቻቸው ደግሞ ገበያ የማፈላለግ ችግሮች እንዳሉባቸው የጠቆሙ ሲሆን፤ የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ በበኩሉ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት በሰጠው መረጃ ኣመልክቷል።

ሁለቱንም ዘጋባዎች ኣያይዘን ኣቅርበናል ከታች ያንቡ፦
    

አዋሳ ጥር 14/2006 በሲዳማ ዞን  ባለፉት ስድስት ወራት ተደራጅተው በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ስራዎች ለተሰማሩ አንቀሳቃሾች ከ85 ሚልዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ 
በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደበበ ተገኝ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የገበያ ትስስሩ የተፈጠረው ከ11ሺህ በላይ ለሚሆኑ አንቀሳቃሾች ነው፡፡ 
በዞኑ ሁለት የከተማ አስተዳደሮችና 19 ወረዳዎች ለሚገኙት ለእነዚሁ አንቀሳቃሾች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበት ሁኔታ በማመቻቸት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ 
በዞኑ ባለፉት 6 ወራት ከ11ሺህ በላይ  ሰዎች ተደራጅተው በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ሲሆን ከመካከላቸውም 4ሺህ የሚጠጉ ሴቶች መሆናቸውንና ከ13 ሚልዮን በላይ ገንዘብ መቆጠባቸዉን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ 
በየተደራጁባቸው የስራ ዘርፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የምክር፣ የንግድ ስራ አመራር ስልጠናና ሌሎችም ድጋፎች እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 
አንቀሳቃሾቹ ከተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች መካከል ማንፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ምግብ ማቀነባበር፣ አገልግሎት ፣ አነስተኛ ንግድ፣ ከተማ ግብርናና  ድንጋይ ንጣፍ  የመንገድ ስራዎች ይገኙበታል፡፡ 
በዚሁ ጊዜም ከ9 ሚልዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ ለአንቀሳቃሾች መሰራጨቱንና በአዲሱ ስትራቴጂ ማዕቀፍ መሰረት ማህበራቱ ለመበደር ከሚፈልጉት ውስጥ 20 በመቶ እንዲቆጥቡ መደረጉንም አስተባባሪው አመልክተዋል፡፡ 
ከአንቀሳቃሹቹ መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በተፈጠረላቸው የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር የገቢ አቅማቸው እያደገ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በሃዋሳ ከተማ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ ስር የታቀፉ የሲዳማ ወጣት ልጆች በቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ መሆናቸውን ሪፖርተራችን ሰሞኑን ከሃዋሳ ከተማ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቷል።
የሲዳማ ወጣቶች በድንጋይ መፍጨት ስራ፤ በኮብል ስቶን ስራ፤ ቢም እና ፕረካስት ስራ የብረታብረት እና የእንጨት ስራ እና በመሳሰሉት የስራ መስኮች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ በማህበር በመደራጀት በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ በራሳቸው ማለትም ብቻቸውን ተደራጅተው ካቋቋሙት ማህበራት በተጨማሪ ከሌሎች ብሄር እና ብሄረሰቦች ልጆች ጋር ተደራጅተው በመስራት ላይ መሆናቸው ተሰሞቷል።
በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ካሉት በተጨማሪ በሁሉም የሲዳማ ከተሞች በመስል መልኩ የማህበራት በመደራጀት በተለያዩ የስራ መስኮች የገንዘብ እና የስልጣና ድጋፎችን ኣግኝተው የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለማሻሻል በመጣር ላይ ናቸው።
ወጣቶቹ በጥቃቂን እና ኣነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ስራ መስራታቸው መልካም ሆኖ ሳለ በምሰሩት ስራ ያሳዩት ወጤት ብዙም ኣጥጋብ ኣይደለም።
በእርግጥ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የወጡትን ጨምሮ ብዙ የተግባር ስራ ልምድ የሌላቸው ጊዜያቸውን ባልቧለ ቦታ ያሳልፉ የነበሩት ወጣቶች ወደ ስራ ገብተው ውጤታማ መሆን መጀመራቸው የምካድ ባይሆንም፤ እያስመዘጋቡ ያሉትን ውጤት ከሌሎች ክልል ማህበራት የስራ ውጤቶች ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ የእትዬ ሌሌ ነው። ከዚህ ባሻገር በስራ ላይ ውጤት በማጣታቸውም የተነሳ እስከ መበተን የደረሱም ኣሉ።
እንደ ጥቻ ወራና ዘጋባ ከሆነ በሃዋሳ ከተማ ሲዳማውያን ብቻ ተደራጅተው ካቋቋሟቸው ማህበራት መካከል ሁለቱ በኣያያዝ ችግር የተነሳ ፈርሰው ከዚህ በፊት ለስራ በከታማዋ ማዘጋጃ የተሰጣቸውን የስራ ቦታ ሊያጡ የግድ ሆኖባቸዋል።
የሲዳማ ወጣቶች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ብሎም ሳይማር ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ለመርዳት እንድያስችላቸው እና በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች ውጤታማ እንድሆኑ የዞኑ መንግስት ኣሁን በማድረግ ላይ ያለው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ማህባራቱ ባለባቸው ድክመቶች ላይ ትኩረት ስጥተው Supportive Monitoring and evaluation ስራዎችን ብሰራ መልካም ነው ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር