የደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ 60 አቃቢያነ ህግን በስነምግባር ግድፈት ከስራ አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2006(ኤፍ.ቢ.ሲ.) የደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ 60 አቃቢያነ ህግን በስነምግባር ግድፈት ከስራ አሰናበተ።
ቢሮው ሌሎች 211 የሚሆኑትን ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርስ እርምጃ ወስዶባቸዋል።
በተመሳሳይ የክልሉ ማረሚያ ኮሚሽንም 42 የሰራዊቱ አባላት ላይ ከባድ እርምጃ የወሰደ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 10 የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ከስራቸው የተሰናበቱ ናቸው
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እድማሱ አንጎ እና የማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አዳነ ዲንጋሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ግለሰቦቹ እርምጃው የተወሰደባቸው ጉቦ በመቀበል፣  ፍትህ በማዛባት፣ በወገናዊነት መስራት እና እስረኞች እንዲያመልጡ ማድረግ የመሳሰሉትን ወንጀሎች ፈፅመው በመገኘታቸው ነው።
ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ ነዋሪዎችን ባሳተፈ ሁኔታ የተካሄደው እርምጃ ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑንም የስራ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል።
እርምጃ  ከተወሰደባቸው  ግለሰቦች መካከልም አብዛኛዎቹ  ክስ  ይመሰረትባቸዋል ተብሏል።
http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7153:----60------&catid=102:slide

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር