በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዋሳጥር 21/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት  ከተለያዩ ምንጮች ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ  ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ 
የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱም ተገልጿል፡፡ 
የጽህፈት ቤቱ  የዕቅድ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አክሊሉ እንጀቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ገቢው የተሰበሰበው  ከመደበኛና የማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎትን ጨምሮ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ የታክስ ግብር እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው፡፡
 የተሰበሰበው ገቢ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡ 
በዞኑ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የገቢ ግብር አሟጦ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት  ሌሎች ዝግጅቶችን ጨምሮ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 
ዞኑ ባለፈው የበጀት ዓመትም ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ296 ሚሊዮን  ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ጠቁመው የዞኑን አጠቃላይ ወጪ በሚገኘው ገቢ ለመሸፈን የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ 
በዞኑ 15ሺህ 146 ግብር ከፋዮችና 1 ሺህ 535 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች  እንዳሉም ገልፀዋል፡፡ 
በተያዘው የበጀት ዓመትም 290 ተጨማሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስከአሁን 71 መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢቲቪ እኣኣ 1/29/2014

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር