POWr Social Media Icons

Sunday, December 8, 2013

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ክልልች የሚገኙ 499  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሊያደርግ ነው።
በሚኒስቴሩ የትምህርት አይሲቲ ማእከል ሃላፊው ዶክተር ገበየሁ ወርቅነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ ሚኒስቴሩ 422 አዳዲስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ደግሞ የፕላዝማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከኢትዮቴሌኮም ጋር በጋራ እየሰራ ነው ብለዋል።
የኢንተርኔት አገልግሎቱ  ፕላዝማው  የመቋረጥ እድል ቢያጋጥመው እንኳን  ተማሪዎቹ ከትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ማእከል የሚተላለፈውን ትምህርት በአማራጭነት እንዲከታተሉበት ታሳቢ ያደረገ ነው።
ኢትዮ ቴሌ ኮም በክልሎች የሚሸፈን ቢሆንም ለፕላዝማዎቹ 78 ሚሊየን እንዲሁም ለኢንተርኔት አገልግሎቱ ደግሞ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር  ውለታ ገብቷል።
በኢትዮቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ የፕላዝማውም ይሁን የኢንተርኔት አገልግሎቱ  ከግማሽ በላይ መከናወኑን ነው የተናገሩት።