POWr Social Media Icons

Thursday, November 21, 2013  • የሲዳማ ዞን መንግስት በቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት የልማት ድርጅቶች ላይ በያዘው የተሳሳተ ኣቋም ድርጅቶቹን ኣጠናክሮ ለታለሙለት ኣላማ እንድውሉ እና ስፊውን የሲዳማን ህዝብ እንድጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ ድርጅቶቹን እንደጠላት ንብረት በማየት የሚጠፉበትን እና የሚበተኑበትን ሁኔታዎችን ብቻ በማመቻቸት ላይ የተጠመዷል
  • የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የመንግስት ድጋፍ ያስፈልገዋል
ክፍል ሁለት
የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ተቋም (SMFI) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፋቃድ ኣግኝቶ በራሱ ቦርድ የሚተዳደር የገንዘብ ተቋም ነው።ተቋሙ በከተሞች ኣካባቢ ቤትን እና ሌሎች ንብረቶችን በመያዝ ብድር የመስጠት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን፤ እንደሌሎች መሰል የኣገሪቱ የብድር እና የቁጠባ ተቋማት ሁሉ ሰዎች በቡድን ተደራጅተው ገንዘብ የሚበደሩበትን መንገዶች በማመቻቸት ኣገልግሎት ይሰጣል።
በኣገልግሎቱም እስከ ሃምሳ ሺ ነው የሚያበድር ሲሆን በግለሰብ ደረጃ ግን ከሶስት ሺ ብር በላይ ኣያበድርም። ለነገሩ በኣሁኑ ወቅት በኣገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት ብድሩን የሚወስዱ ሰዎች በሶስት ሺ ብር ምን ኣይነት ኢንቨስትመንት ልያደርጉ እንደምችሉ ግልጽ ባይሆንም ብዙዎቹ በገንዘብ ኣያያዝ ላይ ትምህርት ሳይሰጣቸው የብድሩ ተጠቃሚ ስለምሆኑ የተበደሩትን ገንዘብ ላላለሙለት ጉዳይ ላይ በማዋል እዳ ውስጥ ስገቡ ታይተዋል። ሰዎች የተበረሩትን ገንዘብ በውቅቱ ኣለመመለሳቸው ከብድር እና ቁጠባ ተቋሙ ጋር እንድካሰሱ ምክንያት ሆኗል። ጉዳዮቻቸው በፍርድ ቤቶች እየታየ ያሉ እና ቤት ንብረቶቻቸውን ሽጠው ለመክፈል የተገደዱ ብዙዎች ናቸው። ለማንኛውን ተቋሙ በኣሁኑ ጊዜ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎትን በተዳከመ መልኩ በመስራት ላይ ይገኛል።
ለሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ተቋም መዳከም ምክንያቱ ምንድነው ብለን ስንል በዞኑ መንግስት ትኩረት መነፈጉ እና በሃላፊትን እና በብቃት የምመራውን ኣካል ማጣቱ ብሎም የሰለጠነ የሰው ኃይል እና የፋይናንስ ኣቅም ውስን መሆን እንደምክንያት ይነሳሉ።
የሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘገባ እንደምያመለክተው፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ከብድር እና ቁጠባ ተቋሙ ገንዘብ እንደፈለጉ እንዳይበደሩ በተበደሩት ገንዘብ ላይ ከፍተኛ የሆነና በየትኛውን ኣገር ተሰምቶ የማይታወቅ ኢንተረስት ወይም ወለድ ማለትም 18 ከመቶ እንድከፍሉ ይጠየቃሉ። ይህንን ከፍተኛ ወለድ ላልመክፈል ስሉም ሌላ ኣማራጨ የብድር ኣገልግሎቱ ሰጭ ተቋም እንድመርጡ ኣድርጓቸዋል። በዞኑ ውስጥ ያሉት ገንዝብ የመበደር ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ከሲዳማ ማክሮፋይናንስ ተቋም ከመበደር ይልቅ ከኦሞ ማክሮ ፋይናንስ መበደርን እንደምመርጡ ሆኗል ማለት ነው። ይህም ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ከመሆኑ በላይ በኣገሪቱ ገዥው ፓርቲ በተለይ ወጣቶችን ኣደራጅቶ የራሱን ፖለቲካ ማራመጃነት ለመጠቀም ሲል የሚያመቻቸውን የብድር ኣገልግሎት በኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በኩል እንድሰጥ ስለምደረገ የሲዳማ ማክሮፋይናንስ የገንዘብ ኣቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ መጥቷል። በተጨማሪም የሲዳማ ማክሮፋይናንስ ተቋም በራሱ ብድር ለመስጠት የምጠቀመውን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚበደር በመሆኑ እና ተቋሙ ያበደራቸው ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ በወቅቱ ካለመመለሳቸ ጋር የያይዞ ተቋሙ በራሱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የማግኘት እድል ጠቧል፤ ይህም ተቋሙ ለብድር ፈላጊ ደንበኞቹ ተገቢውን ኣገልግሎት እንዳይሰጥ ኣድርጎታል።
በተቃራኒው የኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በክልል ደረጃ የተቋቋመ ተቋም በመሆኑ በሲዳማ ውስጥ ብሎም በክልሉ ጠንካራ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል። በተለይ በሲዳማ ዞን ውስጥ cash crop ማለትም ቡና፤ ጫት እና እህል ባለባቸው ወረዳዎች በምገኙ በእያንዳንዳቸው ቀበሌያት ውስጥ LOAN OFFICER በመቅጠር የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ይህም የሲዳማ ማክሮፋይናንስ በዞኑ ውስጥ የነበረውን የብድር እና ቁጠባ ገበያ ለኦሞ ማክሮፋይናንስ እንድያጣ ሆኗል።
የክልሉ መንግስትም ብሆን የወጣቶች entrepreneurship ፕሮግራሙ የሚሆን ገንዘብ በኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በኩል እንድገባ እና እንድወጣ ኣድርገዋል።በተጨማሪም ከኦሞ ማክሮፋይናንስ የሚበደሩ ስዎች 10 ከመቶ ብቻ ወለድ እንድከፍሉ ስለምጠየቁ በርካታ የኣገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ኦሞ ማክሮ ፋይናንስን እንድመርጡ ምክንያት ሆኗል። ከዚህም ባለፈ ኦሞ ማክሮፋይናንስ ያበደሩት ገንዘብ በወቅቱ እንድመለስላቸው ለተበዳሪዎች ተገቢ የሆነ የገንዘብ ኣያያዝ ትምህርት ስለምሰጡ ብሎም በየቀበሌያቱ ባሰማሯቸው ባለሙያዎች በኩል በተበዳርዎቹ ላይ ክትትል ስለምያደርጉ የሚያበድሩትን ገንዘብ በወቅቱ በተበዳሪዎች እንዲመለስላቸው ኣቅም ፈጥረዋል። የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እና ካቢኔዎችም ብሆኑ በምንቀሳቀሱባቸው የሲዳማ ቀበሌያት ህዝቡ የኦሞ ማክሮፋይናንስ ኣገልግሎት ተጠቃሚ እንድሆን የመቀስቀስ ስራ ይስራሉ ተብሏል።

ልክ ኣገሪቷም የውጭ የገንዘብ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ በማድረግ ለኣገር ውስጥ የገንዘብ ተቋማት ከሌላ እንደምሰጡት ሁሉ፤የሲዳማ ዞን መንግስት በዞኑ ውስጥ ከኦሞ ማክሮፋይናንስ በፊት ተቋቋሞ ኣገልግሎት ይሰጥ የነበረውን የሲዳማን ማክሮፋይናንስ ተቋም በማጠናከር በዞኑ ውስጥ ሌላ ማይክሮፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ የዞኑ ህዝብ ንብረት የሆነውን የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ተቋም ከማጠናከር ይልቅ በማዳከሙ ላይ በመበረታቱ ለብዙ ሲዳማዎች መለያቸው እና ኩራታቸው የሆነው ተቋም ከስሮ ለመዘጋት እያመራ ነው።የሲዳማ ዞን መንግስት በቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት የልማት ድርጅቶች ላይ በያዘው የተሳሳተ ኣቋም ድርጅቶቹን ኣጠናክሮ ለታለሙለት ኣላማ እንድውሉ እና ስፊውን የሲዳማን ህዝብ እንድጠቅሙ ከማድረግ ድርጅቶቹን እንደጠላት ንብረት በማየት የምጠፉበትን እና የምበተኑበትን ሁኔታዎችን ብቻ በማመቻቸት ላይ የተጠመደ ይመስላል። ነገር ግን ድርጅቶቹ የሰፊው የሲዳማ ህዝብ ንብረት መሆናቸውን በመገንዘብ በሰው ኃይል እና በገንዘብ የምጠከሩበትን መንገድ ቢያመቻች መልካም ነው።
ለሲዳማ ህዝብ ልማት እና ብልጽግና እንዲያመጡ ተብለው የተቋቋሙ የቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን(SDC) እህት የልማት ድርጅቶች በዞኑ መንግስት ትኩረት በመነፈጋቸው የተነሳ ፈርስዋል፤ በመፍረስም ላይ ናቸው
  • የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን(SDC)ሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎች ለመስራት ቀርቶ ድርጅቱ በራሱ በሁለት እግሩ መቆም ኣልቻለም
  • ፉራ ኮሌጅ፦ ከምመለከተው ኣካል ትኩረት በመነፈጉ የተነሳ ባጋጠመው የትምህርት ጥራት ጉድለት ኣብዛኛዎቹን የትምህርት ክፍሎች በመዝጋት ላይ ያለ ኮሌጅ ሆኗል
  • ሬድዮ ሲዳማ፦ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ለመንግስት የፖለቲካ ማካሄጃነት በመዋል ላይ ያለ
  • ጋራምባ ኮንስትራክሽ እና ኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ፦ተበትነው እና ፈርሰው ታሪክ የሆኑ
  • ሲዳማ ማክሮፋይናስ፦ በኦሞ ማክሮፋይናንስ የታፈነ
ክፍል ኣንድ
ኤስዲስ በኣይርሽ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ እና በሲዳማ ውስጥ በርካታ የልማት ተግባራትን ስያከናውን የቆየ ድርጅት ነው። ይሄው ድርጅት በወቅቱ በርካታ እህት ድርጅቶችን በስሩ ኣቋቁሞ ይስራ የነበረ ሲሆን ካቋቋማቸው ድርጅቶች መካከል በኣሁኑ ጊዜ ኣብዛኛዎቹ ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ በማገልግል ላይ ናቸው፤ የቀሩት ደግሞ ፍርስዋል።

እንደ ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘገባ ከሆነ፦ከሲዳማ ልማት ፕሮግራምነት ወደ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽነትን የተቀየረው SDC፤ በወቅቱ የሲዳማ ህዝብ ኩራት ሆኖ ለሲዳማ ህዝብ ልማት የምቆረቆሩ ግለሰቦች እንደንብ የምሯሯጡበት የነበረ ሲሆን፤ በኃላ ላይ በመንግስት ጠልቃ ገቢነት የተነሳ የስራ ኣቅሙ የተመታ እና የላሸቀ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በኣሁኑ ወቅት ስፋፊ የእርሻ መሬት በኮንትራት መልክ በመያዝ በተለይ በቆሎን በመዝራት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። ሆኖም ምርቱንም በመሸጥ የምያገኙውን ገቢ ለሰራተኞቹ ደሞዝ ከመክፈል ውጭ ሌላ ምንም የረባ እና የምታይ የልማት ስራ ሲስራ የማይታይ ድርጅቶ ሆኗል። በምያሳዝን ሁኔታ የተቋቋመበትን ዓላማ በማሳካት ለሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎች ለመስራት ቀርቶ ድርጅቱ በራሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያነስ በመሄድ ላይ ያለ ነው።

ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን ድርጅት የሆነው ፉራ ኮሌጅ ከSDC ጋር በቦርድ የምተዳደር ሲሆን ከዚህ በፊት ለበርካታ ለተቸገሩ የሲዳማ ልጆች የትምህር ድጋፍ ያደርግ የነበረ፤ ብዙ የሲዳማ ምሁራንን እስከ ውጭ ኣገራት በመላክ ሲያስተምር የነበረ ቢሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት በትምህርት ጥራት ላይ በመውስድ ላይ ባለው እርምጃ ተወዳዳር መሆን ያልቻለ እና በኮሌጁ ኣንዳንድ የትምህርት ክፍሎች በትምህርት ጥራት መጓደል የተነሳ ኣብዛኛዎቹ የትምህርት ክፍሎች ተዘግተው በኣሁኑ ጊዜ በሶስት የትምህርት ክፍሎች ብቻ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ነው። ኮሌጁ ከምመለከተው ኣካል ትኩረት በመነፈጉ ልክ እንደሌሎቹ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት ድርጅቶች በመክሰም ላይ ያለ ኮሌጅ ነው።

ሶስተኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሆነው ሬድዮ ሲዳማ በኣሁኑ ጊዜ በሲዳማ ትምህር መምሪያ ስር የምተዳደር ሲሆን፤ ባለቤት በማጣቱ የተነሳ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ መንግስት የራሱን ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ እና ፕሮግራሞች የምያስራጭበት ሬድዮ ጣቢያ ሆኗል።

ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሆነው ጋራምባ ኮንስትራክሽ በበኩሉ፤ በሲዳማ ውስጥ የምካሄዱትን የልማት ስራዎችን በጥራት እና በብቃት እንድሰራ ብሎም ለሲዳማ ልጆች የስራ እድል እና የስራ ልምድ ማካበቻ እንድሆን ተብሎ የተቋቋመ ቢሆንም፤ ሀላፊነት ወስዶ የምመራ ኣካል ባለመኖሩ ከዚህ በፊት ለስራ ተብለው የተገዙ ከባድ ማሽኖች ሳይቀር ተሽጠው ወይም ለሌላ ድርጅቶች ተሰጥተው ስላላቁ በመፍረስ ላይ ያለ ብቻ ሳይሆን የፈረሰ ድርጅት ነው።

ኣምስተኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት ኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ ከስሙ ውጭ ይሄን ስርቷል የምባል ነገር የለውም። ስራ ካለመስራቱ በላይ ለስራ ተብለው የተገዙ ከባድ ማሽኔሪዎች ተሽጠው ስላላቁ ከጋራምባ ኮንስትራክሽ የተለየ እድል ኣልገጠመውም። ለድርጅቱ መዘጋት ሃላፊነት ወስዶ የምመራው ኣካል ማጣቱ እንደምክንያት ይነሳል።ድርጅቱን በተመለከተ ሌላው ኣሳዛኙ ነገር ለኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ የተሰጠው በሃዋሳ ከተማ የምገኘው ቦታ በኣሁኑ ጊዜ Tony printing press ለተባለ ማተሚያ ድርጅት በክራይ ተሰጥቷል።

ስድስተኛውን እና ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሲዳማ ማክሮፋይናስን በተመለከተ በክፍል ሁለት እንመለስበታለን።