POWr Social Media Icons

Saturday, August 17, 2013

የአንድ ማኅበረሰብ መገለጫና መለያ ከሆኑት እሴቶች አንዱና ዋነኛው ባህል እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡
የአንድ ማኅበረሰብ የኑሮ ዘይቤ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መርሕ እምነትና አስተሳሰብ የጥበብ፣ የአስተዳደር፣ የአለባበስና አመጋገብ ሥርዓት፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችና መገልገያዎች የባህል መገለጫዎች ሲሆኑ በዋናነት በሁለት የሚከፈሉት ቁሳዊና መንፈሳዊ ተብለው ነው፡፡ ቁሳዊ ባህል ታሪካዊ ቅርሶች በጽሑፍ የተቀመጡ ሕትመቶችና ሰነዶች ሕንፃዎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች የምርትና አገልግሎት መሳሪያዎችንና ሌሎች ተያያዥ ውጤቶችን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊ ባህል በሌላ በኩል የሃይማት (እምነት)፣ ፍልስፍና፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች (ክብረ በዓላት) እና አመለካከቶችን ያካትታል፡፡ 
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፈቼና አዲሱ ዓመት ክብረ በዓል መንፈሳዊ (ኢንታንጀብል) ባህል ከሆኑት አንዱ ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫ እንደሆኑ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዓመታዊ መጽሔት ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሲዳማ የራሱ የሆኑ የቀን አቆጣጠር ያለው ሲሆን የአሮጌው ዓመት ማለቂያ እና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ  ትክክለኛ ዕለት የብሔሩ  ሊቃውንት (አያንቶ) ተወስኖ ይታወጃል፡፡ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በዓለም መንፈሳዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ቅድመ ምዝገባ የመጀመሪያ ዙር መረጃ የማሰበሰብ ሥራ መጠናቀቁን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ስለ ፊቼ እና ጫምባላላ መንፈሳዊ ባህል ምንነትና መገለጫዎቹን የክብረ በዓሉ ድባብ፣ የዘመን አቆጣጠር ምስጢራትንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚከተለው ተቀኝቷል፡፡ 
•የፊቼ እና ጫምባላላ ምንነትና አመጣጥ 
በሲዳማ ፍቼና ጫምባላላ የማይነጣጠሉ የበዓሉ ሁነቶች ናቸው፡፡ ፊቼ የአሮጌው ዘመን መጠናቀቅ (ዋዜማ) ጫምባላላ የአዲሱ ዘመን (መባቻ) ብስራቶች ናቸው፡፡ ‹‹ፊቼ›› መጽሔት በ2006 ዓ.ም. ዕትሙ፣ ፊቼና ጫምባላ ታሪካዊ  አጀማመር መቼ እንደሆነ በውል ባይታወቅም በዞኑ በሀቤላ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከነበሩት ፊጦራ የሚባሉ ሰውዬ ሴት ልጃቸው ፊቾ አማካይነት መጀመሩን ለቅድመ ምዝገባ ጥናት የተሰበሰበው መረጃ ያመለክታል፡፡ 
ፊቾ የምትባለው የአቶ ፈጠራ ልጅ ለአቅመ ሔዋን ደርሳ ባል ስታገባ የሞቀ ትዳር፣ የተትረፈረፈ ሀብት ስታገኝ በብሔሩ ባህል መሠረት እናት አባቷን ቅቤ፣ የተሠራ ቆጮና የረጋ ወተት ይዛ እየመጣች በየዓመቱ ‹‹ቀባዶ›› ተብሎ በሚጠራው ቀን  ትጠይቃቸው ነበር፡፡ ያመጣችውን ምግብ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤቶች ከበሉ በኋላ ከአባቷ ጋር ምርቃትና አድናቆታቸውን ይገልጹላታል፡፡ በእርግጥ በሲዳማ ባህል ልጆች የሚመገቡት ትላልቆቹና አዋቂዎቹ ከበሉ በኋላ ስለሆነ  የቀረውን የቤተሰብና የጎረቤት ልጆች አንድ ላይ ተሰብስበው ይመገቡና ደስታቸውን ጫምባላላ (የዚህ አይነት ጥጋብ ዞሮ ይምጣ) እያሉ በዘፈን ይግልጻሉ፡፡ መሰል የፊቾ ጥየቃ በዘላቂነት መታወስ እንዳለበት በመግለጽ አባቷ አቶ ፌጦራ በየዓመቱ ደስታና ፋሲካ የምትፈጥረው ልጃቸው የምትመጣበት ቀን የሲዳማ ፌቼ ተብሎ እንዲከበር ከአካባቢው ኅብረተሰብ ተቀባይነት አግኝቶ በጎሳ መሪዎች የዘመን መለወጫ እንዲሆን መወሰኑን የጥናቱ መረጃ ያስረዳል፡፡ ይሁን እንጂ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼና የቀን አቆጣጠር ከፊቾ ታሪክ ጋር ስለመያያዙ ከአፈታሪክ መረጃ በስተቀር ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል በዘመናት ደት የብሔሩ ሊቃውንት የየዓመቱን ዙር መሠረት አድርገው የቀን፣ የወርና የዓመት አቆጣጠር ዘዴን በመቀመር ፊቼ የሲዳማ የዘመን መለወጫ በዓል እንዲሆን መወሰናቸውን ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ተብራርቷል፡፡ ፊቼ ትርጉሙም የዘመን መለወጫ ድልድይ አዲሱ ዓመት የበረከት የደስታና ፍሥሐ ይሁንልን እንደማለት ነው፡፡ ከዋዜማ ቀጥሎ ያለው ቀን አዲስ ዓመት ወይም ጫምባላላ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስለአለፈው ዓመት ለፈጣሪ ምስጋና፣ ስለቀጣዩ ደግሞ የመልካም ምኞት የሚገለጽበት የደስታና ፍንደቃ ዕለት ይሆናል፡፡ 
•የፊቼና ጫምባላ መንፈሳዊ ባህል መግለጫ አጀቦች
 ፊቼ የአሮጌው ዓመት መጨረሻ የአዲሱ ዋዜማ እንደመሆኑ የብሔሩ ሊቃውንት የጨረቃና ኮከብ አቅጣጫና ቁጥር ተመልክተው የዘመን መለወጫ ትክክለኛ  ወሩንና ቀኑን ከወሰኑ በኋላ ለሕዝቡ ከአንድ ሳምንት በፊት በገበያ ይታወጃል፡፡ ይህም ላላዋ ይባላል፡፡
የዘመን መለወጫ ቀኑ ከታወጀ በኋላ የብሔሩ ባህላዊ መሪዎች (ዎማች) ለፊቼ ሳምንት ሲቀረው ከአንድ ወር በፊት የጀመሩት ጾምና የሱባኤ (የንስሐ) ጸሎታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡ በተጓዳኝ ሴቶች ለበዓሉ ማመቂያ ቅቤ፣ ቆጮ፣ ወተትና ቅመማቅመም ያዘጋጃሉ፡፡ ወጣት ወንዶች እንጨት ወጣት ሴቶች ለእናታቸውና ረዳት ለሌላቸው ጎረቤቶች የሚያቀርቡበትና የሚረዱበት ጊዜ ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ ዋዜማን ከደረሱ በኋላ በእርጥብ ቅጠል የተዘጋጀ መሽሎኪያ (ሁሉቃ) ፀሐይ ስታዘቀዝቅ የቤተሰቡ አባላትና ከብቶች በዚያ ሾልከው እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡ ይህም ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ በሰላም ተሸጋግረን ማለት ይሆናል፡፡ መሰል ትዕይንት በዞኑ ሁሉም አከባቢዎች በየደጁ የሚከናወን ሲሆን፣ በሐዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ የሁሉም ጎሳ መሪዎችና አባቶች በተገኙበትም ይከናወናል፡፡ ከዚያም የበዓሉ ማድመቂያ ርችት ይሎኮስና በድምፅና ሕብርቀለማት ደስታ ይገለፃል፡፡ ባለፈው ሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. የተደረገው ይኸው ዓመታዊ ትዕይንት ነው፡፡ በእርግጥ የፊቼ ክበረ በዓል አጀቦች ከላይ ከተገለጹት በተጨማሪ በየአካባቢው ታላቅ ሽማግሌ ቤት ማታ ቆጮ በቅቤ በባህላዊ መመገቢያ ቀርቦ በዎማች ተመርቆ አንድ ላይ ተሰብስበው በመብላት ደስታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ሌላው ገጽታ ደግሞ ፊቼ በዕለት ከብት አለመታረዱ ነው፡፡ ቀድሞ የነበረ ሥጋ ካለ ከቤት ውጭ በእንስሳት ጉያ ያሳድሩታል፡፡ ይህም በፊቼ ክብረ በዓል የሲዳማ ብሔር ለከብት ያለውን ትልቅ ፍቅር የሚያሳይበት በመሆኑ የእንስሳትም ደስታ እንደሆነ ያሳስባል፡፡ 
•ጫምባላላ
ጫምባላላ (ዞሮ መምጣት ማለት ነው) አዲሱ ዓመት የሚጀመርበት ልጆች ምንም ሥራ የማይሠሩበትና እየዞሩ የሚመገቡበት፣ ከብቶች ለዚህ ቀን ተከልሎ በቆየ ጥብቅ ውስጥ ተለቀው የሚግጡበት ቀን ነው፡፡ ልጆቹ ‹‹አይዴ ጫምባላላ›› (ዞረን መጣን) እያሉ ተስብስበው በየአካባቢው ሲዞሩ እናቶች ‹‹እሌ...እሌ..››፣ ወይም ‹‹ድረሱ....ድረሱ›› በማለት በቅቤ የተዘጋጀውን ቆጮ (ቡሪሳሜ) ያቀርቡላቸውና ይበላሉ፡፡ እስከ ጠዋቱ ሦስት ሰዓት መብላት መጠጣቱ ከቀጠለ በኋላ በየሕዝብ መሰብሰቢያ (ጉዱማሌ) ወጥተው የበዓሉን ስሜት ይገልጻሉ፡፡ ባለፈው ሐምሌ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ሐዋሳ ከተማ ከጧቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ከሲዳማ ዞን 19 ወረዳዎችና  ሁለት የከተማ አስተዳደሮች በእግር በፈረስና በመኪና ሐይቅ ዳር ወደሚገኘው ጉዱማሌ የሕዝብ መሰብሰቢያ በሚተሙ እድምተኞች ጡሩምባና ዘፈን በአንድ እግሯ ቆማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ በፈረስ የታጀቡ ከተለያዩ አከባዎች የመጡ አረጋውያንና ጎልማሶች በዜማ የታጀበ ዘፈን እየዘፈኑ በጭፈራ (ቄጣለላ ወጣት ሴትና ወንዶች፣ ፋሮ ያላገቡ ሴቶች ሆሬ በተባሉ ባህላዊ ጭፈራዎች) የአዲሱን ዓመት አቀባበል አድምቀውታል፡፡     
•የፊቼ በዓልና የቀን አቆጣጣር ምስጢራት
የፊቼ በዓል በየትኛው ቀንና ወር እንደሚውል የብሔሩ ባህላዊ ሊቃውንት ወይም አዋቂዎች /አያንቶ/ በጨረቃ ምልክትና ኮከብ ቆጠራ ስሌት ትክክለኛውን ዕለት ይወስናሉ፡፡ በሲዳማ ዞን በየወረዳዎቹና ከተማ አስተዳደሮች ሉዋ ተብሎ የሚጠራው አስተዳደራዊ መዋቅር ሥልጣን ያላቸው ማለትም ዎማ፣ ጋሮ፣ ሞቴ፣ ጋኔ፣ አማካይነት በአያንቶዎች የተገኘው የኮከብ ቆጠራና ጨረቃ ምልከታ ውጤት ይነገራቸዋል፡፡ በብሔሩ አስራ አራቱ ጎሳዎች ያሉት አያንቶዎች ለየአካባቢው ዎማዎች ይነግራሉ፤ እነሱም በተራቸው ለጎሳ መሪዎች (ሞቴ) በአጭር ጊዜ ውስጥ መልዕክቱን በማስተላለፍ የፊቼ በዓል የሚውልበት ቀን የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡ በዘንድሮው በዓል በባህላዊ ጭፈራ (ቄጣላ) የፊቼ ጫምበላላን ክብረ በዓል ከፊት ሆነው ሲመሩ ከነበሩት አያንቶዎች አንዱ የሆኑትን አቶ ጋዱዳ ጋቢሶን ስለ ኮከብ ቆጠራና ጨረቃ ምልከታ በሪፖርተር ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገው የሚከተሉትን ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
•የጨረቃ ምልከታ ኮከብ ቆጠራ
እንደ አቶ ጋዱዳ ማብራርያ፣ በሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ከመድረሱ አንድ ወር አካባቢ ሲቀረው በየጎሳዎቹ የሚገኙት እሳቸውን ጨምሮ ታላላቅ አባቶች (ጪሜሳ) ስብሰባ ይቀመጣሉ፡፡ በዚያ ስብሰባ በዓመቱ ካሉት አስራ ሁለት ወራት በአሥራ አንደኛው ከእንግዲህ ጪሜሳዎች ወደ ዳስ በመግባት ለቀጣይ ተግባር ፊቼ ለመድረስ አንድ ሳምንት እስከ ሚቀረው ድርስ የንሥሐ ጸሎት ይደረጋል፡፡ በነዚህ ሠላሳ ቀናት መጪው ዓመት የሰላም፣ የበረከት፣ ከብቶች የሚረቡበትና ወተት የሚሞላበት ለሕዝቡ የደስታና የጤና እንዲሆን እንዲሁም አዝመራና የአየር ንብረቱ ተስማሚ እንዲሆን ይጸልያሉ፡፡ አቶ ጋዱዳ እንዳስረዱት በንሥሐ ጸሎት ጊዜ የትኛውም ጪሜሳ ሴት በፍጹም አትጠጋውም እነሱም እንደዚያው ርቀው ይቆያሉ፡፡ ምግብ የሚያቀርቡት ትናንሽ ልጆች ናቸው፡፡ ይህ መሰሉ እሳቤም ከኃጢአት እንዲርቁና ፈጣሪም ጸሎታቸውን እንዲሰማ ተብሎ  ነው፡፡
ስለ ኮከብ አቆጣጠሩና ጨረቃ ምልከታ አቶ ጋደዳ የሚከተለው ይላሉ፡፡ ‹‹በእርግጥ የኮከብ ምልክት ከታሪክ  አንፃር ካየነው  በጥንት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስም በኮከቦች እንቅስቃሴ ይመራ ነበር፡፡ በእኛ በሲዳማ ኮከብና የቀን አቆጣጠር አሥራ ሁለት ወራትን በመቁጠር የሚከናውን ሲሆን፣ ፊቼ ሳምንት ሲቀረው  የምልከታ ቀን (ላኦ) በየዓመቱ የምናወቃቸው ሃያ ሰባት ኮከቦች አሉ፡፡ እነዚያ ኮከቦች የሚታዩት በየወሩ በሃያ ሰባተኛው ቀን ሲሆን የተመለከትንበትን ቀን ከቆጠርን በሃያ ስምንተኛው ቀን  ይታያሉ ማለት ነው፡፡ 
በሲዳማ አንድ ወር ማለት አሥራ አምስት የጨለማና አስራ አምስት የጨረቃ ቀኖች ተቆጥረው ነው፡፡ ዓመቱ ከተጀመረ ዕለት ጀምሮ 12ኛ ወር ማለቂያ አካባቢ የፊቼ በዓል ጨለማው ከማለቁ በ11ኛ ወይም በ13ኛው ቀን ቀባዶ በዕለት እንዲውል ይደረጋል፡፡ እዚህ ላይ በሲዳማ ቀኖች ሁሉ ጥሩ ባለመሆናቸው ኮከቦቹን ከጨረቃ አንፃር ያሉበት አቅጣጫ በማየት ሁለት ወይም ሦስት ቀኖች ወደፊት ወደኋላ በማድረግ የግዴታ በቃባዶ ቀን እንዲሆን እንወስናለን፤ ቀባዶ ቀን እንዲውል የተፈለገበት ምክንያት ቀኑ ታሪካዊ በመሆኑና የሳምንቱ የተቀደሰ የመጀመሪያ ዕለት ስለሆነም ነው፤›› ይላሉ፡፡ እንደ አቶ ጋዱዳ ፊቼ የሚውልበትን ትክክለኛ ቀን ብቻ ሳይሆን በየወሩ ኮከብ ቆጠራና ጨረቃ ምልከታ ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም አዲስ ቤት ለመሥራት፣ ሴት ልጅ ለማጨት፣ ጦርነት ካለ ለመዝመት፣ ስለአዝመራ ወቅቶችና ሌሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድርጊቶችን ለመከወን ትክክለኛ ቀንና ዕለት ይወሰናል፡፡
•የሲዳማ ፊቼ - ጫምባላላ ከሙስሊም ጾም ጋር ይመሳሰል ይሆን?
ለዚህ ጥያቄ የሲዳማ አያንቶ የአቶ ጋዱዳ ምላሽ አውንታዊ ነው፡፡ ሆኖም አንድ አይነት ነው ማለት እንዳልሆነ ያሰምሩበታል፡፡ የሚመሳሰልውም ሲዳማም ሆነ የሙስሊሙ ጾምና ፍቺ በጨረቃና  ክዋከብት ሥርዓት (Lunar system) ጋር የተገናኙ በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ሁልጊዜ የሙስሊም ጾም የእኛን ፊቼ በዓል አንድ ወይም ሁለት ቀን ዘግይቶ ይውላል፡፡ አልፎ አልፎ በእኛ ቀን ጫምባላላ ቀን ሊውል ይችላል፤›› በማለት ካብራሩ በኋላ አንድ የሙስሊም ወዳጄ የጫምበላላ ማግስት ባነጋገርኩበት ቀን ‹‹ ለምሳሌ እኔ ባለኝ ተሞክሮና ምልከታዬ ጾማቸው ነገ (ሐሙስ) ሊፈታ እአንደሚችል ነግሬዋለሁ›› በማለት ስለዕውቀታቸው ገልፀዋል፡፡
•የሲዳማ የቀን መቁጠሪያ እንዴት ይዘጋጃል?
የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ በየዓመቱ ከመደበኛው የኢትዮጵያ አቆጣጠር ጋር አያይዞ የዘመን መቁጠሪያ (ካሌንደር) ያሳትማል፡፡ እንዴት እንደሚያዘጋጅ የመምሪያ ኃላፊውን ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ፍላቴ ጠይቀን የፊቼ ጫምባላላ በዓል በየዓመቱ የሚውለው በተለያዩ ቀናትና ወር በመሆኑ የሚወሰነው በአያንቶዎች ጨረቃ ምልከታና ኮከብ ቆጠራ ነው ብለውናል፡፡ 
ነገር ግን አያንቶዎች ባላቸው የኮከብ ቆጠራ ጥበብና ተስጥኦ በትክክል ፊቼ የሚውልበትን ቀን በማወቅ እንደሚወስኑ ያብራሩት አቶ ወርቅነህ፣ ‹‹ለምሳሌ የ2007 ዓ.ም. መቼ እንደሚሆን መዳረሻ ቀኖችን ከእነርሱ ስላወቅን የቀን መቁጠሪያውን ማዘጋጀት እንችላለን፡፡ ለትክክለኛው ቀን የአያንቶዎችን ውሳኔም እንጠብቃለን፤›› በማለት አክለዋል፡፡ 
ከዚህ ጋር በተገናኘ በ2004 ዓ.ም. የሁላ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሸዋሌ አዱላ የተባሉት ምሁር የ10 ዓመታት የፊቼ በዓል የሚውልበትንና የቀን መቁጠሪያውን አስልተው ማቅረባቸውንም አቶ ወርቅነህ ጠቁመዋል፡፡
•ፊቼ - ጫምባላላን በዩሴስኮ በመንፈሳዊ ቅርስነት የማስመዝገብ እንቅስቃሴ
የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ከፌደራልና ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋራ በመተባበር የፊቼ በዓል ከመስቀል በዓል ቀጥሎ  በመለያ ቁጥር 002 ቅድመ ምዝገባ ተደርጎለት በ2005 ዓ.ም. ከግንቦት እሰከ ሰኔ ለአንድ ወር መረጃ የማስባሰብ ሥራ መሠራቱን የመምሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ገልጸዋል፡፡
ዩኔስኮ ባስቀመጠው ፎርማት (ICH-02) መሠረትም የምዝገባ ጥያቄውን ለመሙላት የሚያስችል ቅድመ ምዝገባ ጥናት መደረጉና በአሁን ወቅት የቀረው የክብረ በዓል አስር የፎቶግራና የቪዲዮ እንዲሁም የጽሑፍ ስነዶች እንዳቀርቡ በመጠየቁ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ሥራም በመስከረም 2006 ዓ.ም. ለክልልና ፌደራል ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ከቀረበ በኋላ በጥር 2006 ዓ.ም. ለዩኔስኮ ተጠናቆ እንደሚቀርብ አስረድተዋል፡፡
በአስፋው ብርሃኑ ልዩ ዘጋቢ ከሐዋሳ
የፍትሕ ተደራሽነትን (Access to justice) የፅንሰ ሐሳብ ትንተናና በአገራችን ያለውን አተገባበር መፈተሽ ለባለድርሻ አካላት (ለሕዝቡ፣ ለመንግሥት የፍትሕ አካላት እንዲሁም በመብት ላይ ለሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ያለው አስተዋጽኦ ሰፊ ነው፡፡
የፍትሕ ተደራሽነት የፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ አካል ተደርጎ የሚወስድ ሲሆን፣ በራሱም የግለሰቦች መብት ነው፡፡

የፍትሕ ተደራሽነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ባለመብት መሆን ትርጉም ያጣል፡፡ በሕግ የተቀመጡ መብትና ግዴታን አለማወቅ (ወይም ለማወቅ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖር)፣ ቢታወቅም የሕግ ባለሙያ ዕርዳታ ባለማግኘት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ያላቸው አካላት ተደራሽነት ባለመረጋገጡ መብትን አለመጠየቅ ወይም ለተጣሰ መብት ሕጋዊ መፍትሔ አለማግኘት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ለመሆኑ በአገራችን ያሉ ሕጐች ለግለሰቦች የፍትሕ ተደራሽነት መብት ዋስትና ይሰጣሉ? የመብቱ አፈጻጸምስ በተግባር ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች በፌዴራል ደረጃ መዳሰስ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡

የፍትሕ ተደራሽነት መብት ትርጉም
በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ የፍትሕ ተደራሽነት መብት የፍትሕ ፈላጊውን ማዕከል በማድረግ ሰፋ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት አንድን አጋጣሚ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ ፍትሕ ፈላጊው መብቱን ለማስከበር ተገቢ የሆነ መፍትሔ ለማግኘት የሚከተለውን ሒደት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ ግለሰቦች በተለይ ለመብት ጥሰት የተጋለጡ ሰዎች የደረሰባቸውን ኢፍትሐዊነት ለማወቅ የሚያስችላቸውና ኢፍትሐዊነቱ የሕግ የበላይነትን ወይም ሕግን መሠረት አድርጐ እንዲታረም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ መፍትሔ የሚያገኙበትን ሒደት የፍትሕ ተደራሽነት መብት ልንለው እንችላለን፡፡

የፍትሕ ተደራሽነት በውስጡ ብዙ መብቶችን የሚያካትት ቢሆንም፣ በዚህ ጽሑፍ ምልከታ የሚደረግበት የሕግ ተደራሽነት (Access to law)፣ በጠበቃ (በሕግ ባለሙያ) የመታገዝ (Access to council) እና የፍርድ ቤት ተደራሽነት (Access to court) መብትን ይሆናል፡፡ የሕግ ተደራሽነት በአገሪቱ የሚወጡትን ሕጎች ኅብረተሰቡ የሚያገኝበትንና መብትና ግዴታውን የሚረዳበትን ሥርዓት ይመለከታል፡፡ ሕግ ተደራሽ ነው የሚባለው ሕጉ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ሊያገኘው የሚችለው ሲሆን፣ በቃላቱና በፅንሰ ሐሳብ አጠቃቀሙ ቀላልና ለመገንዘብ የማያስቸግር ሲሆን ነው፡፡  የሕግ ተደራሽነት በአግባቡ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ግለሰቦች በወጣው ሕግ ግዴታ እንዲፈጽሙ መጠየቅ ተገቢ አይሆንም፡፡ ሕግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም የሚለው የሕግ መርህ መሠረት የሚያደርገው፣ ኅብረተሰቡ በአገሪቱ የወጡትን ሕጎች በሙሉ ለማወቅ የሚችልበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው፡፡

በሕግ ባለሙያ የመታገዝ መብት ደግሞ አንድ ተጠርጣሪ ወይም የፍትሐ ብሔር ወይም የአስተዳደር ሙግት ተሳታፊ የሆነ ግለሰብ ለጉዳዩ የሚረዳውና ብቃት ያለው የሕግ ምክር በክፍያ ወይም ያለክፍያ ለማግኘት የሚችልበት አግባብ ነው፡፡ የሕግ ባለሙያ ምክር የማግኘት መብት በአብዛኛው ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገናኘ መታየቱ የተለመደ ቢሆንም፣ ወንጀል ነክ ባልሆኑ ጉዳዮችም መብቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ምንም እንኳ እንደ ወንጀል ጉዳይ ሕይወትንና ነፃነትን የሚያሳጡ ባይሆንም፣ የንብረት መብትንና ማኅበራዊ ጥቅሞችን አደጋ ውስጥ የመክተት ውጤት ስለሚኖራቸው በፍትሐ ብሔር ጉዳይ የሕግ አማካሪ ዕርዳታ ማግኘት ጠቃሚ መብት መሆኑ ችላ ሊባል አይገባም፡፡ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጎች ውስብስብነትና ጠበቃ መቅጠር ከሚችሉ ተሟጋቾች ጋር ያለውን ሚዛን ማጣት መመልከት የመብቱ አስፈላጊነትን የበለጠ ለመረዳት ያስችላል፡፡

ሌላው የፍትሕ ተደራሽነት መብት አካል የፍርድ ቤት ተደራሽነት ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶች በጂኦግራፊያዊ አወቃቀራቸው፣ በመስተንግዶአቸውና በሚከተሉት አሠራር ሁሉ ለሕዝቡ የቀረቡ እንዲሆኑ የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የፍርድ ቤቶች በየአካባቢው መቋቋም፣ መደበኛ ያልሆኑ የዳኝነት አካላት ውሳኔዎች በፍርድ ቤቶች እንደገና የሚታዩበት ሁኔታ መኖር፣ የዳኝነት ክፍያ አለመጋነን፣ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሲሆን አስተርጓሚዎች የሚመደቡበት ሁኔታ ካለ ወዘተ የፍርድ ቤቶች ተደራሽነት መረጋገጡን አመላካች መስፈርቶች ይሆናሉ፡፡ ፍርድ ቤቶች ለሕዝቡ ተደራሽ ካልሆኑ መደበኛ ያልሆነ የዳኝነት ሥርዓት ስለሚነግስ የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት በዓለም አቀፍ መስፈርት መሠረት ማስከበር አዳጋች ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የፍርድ ቤቶች ተደራሽነት ካልተረጋገጠ ሕዝብ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን መተማመን የሚቀንሰው ይሆናል፡፡

የፍትሕ ተደራሽነት የሕግ መሠረት
የፍትሕ ተደራሽነት መብት በግልጽ ወይም በትርጉም በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ስምምነት፣ በፌዴራሉና በክልሎች ሕግጋተ መንግሥት እንዲሁም በዝርዝር አዋጆችና ደንቦች ላይ ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ በአንቀጽ 10 ‹‹ማንም ሰው በመብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም በተከሰሰበት ማንኛውም ወንጀል ውሳኔ ለማግኘት ሙሉ የእኩልነት መብቱ ተጠብቆ ነፃ በሆነና አድልዎ በሌለበት ፍርድ ቤት ሚዛናዊና ይፋ የሆነ ፍርድ የማግኘት መብት፤›› እንዳለው ይደነግጋል፡፡ ድንጋጌው የፍርድ ቤት ተደራሽነት መብትን በግልጽ የሕግና የሕግ ባለሙያ የማማከር መብትን በአንድምታ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ ሚዛናዊ የፍርድ ሒደት የሚኖረው ግለሰቦች በግልጽ በሚታወቅ ሕግ የተከሰሱበትን ነገር አውቀው በሕግ ባለሙያ እገዛ ከተከራከሩ መሆኑ አከራካሪ አይሆንም፡፡

የዚሁ ሰነድ አንቀጽ 8 ‹‹ማንም ሰው በሕገ መንግሥትም ሆነ በሌላ ሕግ የተሰጡትን መሠረታዊ መብቶች የሚጥስ ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ ሥልጣን ላላቸው የአገሩ ፍርድ ቤቶች አመልክቶ ውጤታማ መፍትሔ የማግኘት መብት አለው፤›› በማለት ለፍትሕ ተደራሽነት መብት ጥበቃ ይሰጣል፡፡ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንም በተመሳሳይ መልኩ በአንቀጽ 14 የፍትሕ ተደራሽነትን በምልዓት የሚያስከብሩ ዘርዘር ያሉ መርሆችን አካቷል፡፡ አንቀጽ 14 (መ) ‹‹…ራሱ በተገኘበት የመዳኘት፣ ራሱን በግል ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል፣ ጠበቃ ከሌለው የሕግ አማካሪ ዕርዳታ የማግኘት መብት እንዳለው የማወቅ ትክክለኛ ዳኝነት የሚጓደል ሆኖ ሲታይና የገንዘብ አቅሙ የማይፈቅድ ሲሆን፣ ሳይከፍል ጠበቃ የማግኘት መብቱ….›› እንዲከበርለት ይደነግጋል፡፡

የፌዴራሉ ሕገ መንግሥት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችን ዕውቅና ከመስጠት ባለፈ በአንቀጽ 37 ‹‹ፍትሕ የማግኘት መብት›› በሚል ርዕስ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው፤›› በማለት ለፍትሕ ተደራሽነት መብት የሕግ መሠረት ይጥላል፡፡ በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 19, 20 እና 21 ላይ ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለተያዙ ሰዎች፣ ለተከሰሱ ሰዎች እንዲሁም በጥበቃ ሥር ላሉ ሰዎች የፍትሕ ተደራሽነት መብትን በማካተት ዘርዘር አድርጎ አስቀምጧል፡፡

አንቀጽ 20 የተከሰሱ ሰዎች ‹‹በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግሥት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው፤›› በማለት ደንግጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት በመንግሥት ወጪ ጠበቃ እንዲቆምለት የሚጠይቀው ሰው ክስ የቀረበበት፣ አቅም የሌለው መሆን ሲገባው በፍርድ ቤቱ እይታ ‹‹ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታም›› ሊያጋጥም ግድ ይላል፡፡ መብቱ ለተከሰሱ ሰዎች ብቻ መሰጠቱ የተያዙ ሰዎችና በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች በመንግሥት ወጪ ጠበቃ እንዲቆምላቸው መጠየቅ የማይችሉ መሆኑን ያመለክታል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥት ግን ፍትሕ የሚጓደል መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ለተያዙም ሆነ በጥበቃ ሥር ላሉና በፍርድ ለታሰሩ ሰዎች በመንግሥት ጠበቃ (Assigned counsel) የመጠቀም መብት ያጎናጽፋል፡፡

የፍርድ ቤቶች ተደራሽነትን በተመለከተ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 78 በፌዴራልና በክልሎች ሦስት እርከን ደረጃ ያላቸው ፍርድ ቤቶች እንደሚቋቋም ከመግለጹ በተጨማሪ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአገሪቱ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሊወሰን ይችላል በማለት ለፍርድ ቤቶች ጂኦግራፊያዊ ተደራሽነት መሠረት የሚጥል ድንጋጌ ይዟል፡፡ ይህ ካልሆነም ክልሎች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትንና የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ሥልጣን በውክልና የተሰጣቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በዚህ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በተወሰኑ ቦታዎች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን፣ የተወሰኑ ክልሎች ደግሞ የፌዴራል ጉዳይን በውክልና በማየት ላይ ይገኛሉ፡፡

 በአዋጅ ቁጥር 322/1995 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፋር፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተቋቋመ ሲሆን፣ በተግባር በአግባቡ እየተሠራበት ስለመሆኑ ጥናት ይፈልጋል፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን በውክልና የተሰጣቸው ክልሎች የፌዴራል ጥናት ጉዳዮችን ሲዳኙ የፍርድ ቤቱ ቋንቋ የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ ይሆናል ወይስ የክልሉ የሥራ ቋንቋ የሚለው ሌላው ሊጠና የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በተቋቋሙበት ቦታ ፍርድ ቤቶች በአግባቡ የማይሠሩ ከሆነና በውክልና መሠረት ጉዳዮችን የሚመለከቱ ፍርድ ቤቶች የሚጠቀሙት የክልሉን የሥራ ቋንቋ በሆነ ጊዜ የፍርድ ቤቶቹ ተደራሽነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡

የክልሎች ሕግጋት መንግሥት የፍትሕ ተደራሽነትን በተመለከተ ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን የያዙ በመሆናቸው በዝርዝር መዳሰሱ አላስፈለገም፡፡ ከሕገ መንግሥት ውጪ ያሉት ሕጎችን ምልከታ እናድርግ፡፡ ከሕገ መንግሥቱ በፊት ሥራ ላይ ለዘመናት የነበሩት የሥነ ሥርዓት ሕጎች የግለሰቦችን በሕግ አማካሪ የመጠቀም መብትን ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 57 አቤት ባዩ ራሱ እንዲቀርብ ፍርድ ቤት ካላዘዘ በቀር በማንኛውም ፍርድ ቤት አቤቱታ ለማቅረብ፣ ለመከራከር፣ ነገሩን ለማስረዳት በነገረፈጅ፣ በተወካይ ወይም በጠበቃ እንዲከራከር መወከል እንደሚችል ደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነቱ ጠበቃ ለመቅጠር በሚቻሉ ሰዎች እንጂ ለማይችሉ ባለመሆኑ የፍትሕ ተደራሽነት ላይ የተወሰነ ገደብ አለው፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉም በአንቀጽ 65 የተያዘ ወይም የታሰረ ወይም በጊዜ ቀጠሮ ያለ ሰው ጠበቃውን የመጥራትና የማማከር መብት እንዳለው ቢደነግግም፣ በመንግሥት ወጪ ሊቆም ስለሚችል ጠበቃ የሚለው ነገር ባለመኖሩ በፍትሕ ተደራሽነት መብት አፈጻጸም ክፍተት አለው፡፡ ምክንያቱም የፍትሕ ተደራሽነት መብት ጠበቃ መቅጠር በሚችል ሰው ሚዛን ከሚለካ ይልቅ መቅጠር ባልቻለውና ሕጉ በፈጠረለት ድጋፍ የሚለካ በመሆኑ ነው፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 57/1992 በአንቀጽ 49 ነፃ የሕግ አገልግሎት ስለመስጠት (Pro Bono Publico Service) ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ማንኛውም ጠበቃ በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ በዓመት ቢያንስ የ50 ሰዓት የሕግ አገልግሎት መስጠት አለበት፡፡ አገልግሎት የሚሰጠውም የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሰዎች፣ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ለሲቪል ድርጅቶች፣ ለማኅበረሰብ ተቋማት ፍርድ ቤት የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለሚጠይቃቸው ሰዎች፣ ሕግን፣ የሕግ ሙያንና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ለሚሠሩ ኮሚቴዎችና ድርጅቶች ነው፡፡
ይህ ድንጋጌ ለፍትሕ ተደራሽነት ያለው ጠቀሜታ ሰፊ ቢሆንም፣ በተግባር ያለውን አፈጻጸም የሚገዛ መመርያ ባለመኖሩ ተፈጻሚነቱን መገምገም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጠበቆች አገልግሎቱን እንደሚሰጡ ጸሐፊው በተሞክሮው ያውቃል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/2000 መሠረት የፍትሕ ሚኒስቴር ከሚሰጣቸው ሦስት ፈቃዶች ውስጥ አንዱ የሆነው ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ለፍትሕ ተዳራሽነት ያለው ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህ ፈቃድ የሚሰጠው የኅብረተሰቡን አጠቃላይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ለሚሟገት፣ በቂ የሕግ ትምህርትና ልምድ ላለው፣ ከደንበኞቹ ምንም ዓይነት ክፍያ የማይቀበል የተመሰከረለት ሥነ ምግባር ላለው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ የጥብቅና ፈቃድ ያለው መስፈርቶቹን ካሟላ ደግሞ ለሚኒስቴሩ በማሳወቅ አገልግሎቱን መስጠት ይችላል፡፡ ይህ ፈቃድ ለተፈጥሮ ሰው እንጂ በሕግ ሰውነት ለተሰጣቸው ተቋማት የሚሰጥ ባለመሆኑ ለመብት ጥሰት የተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጥቅም ለማስከበር የተቋቋሙ ድርጅቶች በዚህ ፈቃድ ሊጠቀሙ የሚችሉበት አግባብ የለም፡፡ ልዩ የጥብቅና ፈቃድ በማውጣት ለኅብረተሰብ ጥቅም ጥብቅና መቆም በብዛት ያልተለመደ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶች አካባቢ ከተለጠፉ ማስታወቂያዎች ለመረዳት እንደተቻለው ፍትሕ ሚኒስቴር ልዩ የጥብቅና ፈቃድ እንዲኖር፣ እንዲስፋፋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ነው፡፡

የተከላካይ ጠበቆች ቢሮ በሙሉ ጊዜ ተቀጣሪ የሕግ ባለሙያዎች ነፃ የሕግ ምክርና ጥብቅና የሚሰጥበት አሠራር ነው፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1996 አንቀጽ 16(2) (በ) የፌዴራል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የተከላካይ ጠበቆች ቢሮን ያደራጃል በሚል ደንግጓል፡፡ በዚህ መሠረት ቢሮው በፌዴራል ፍርድ ቤት የተቋቋመ ሲሆን፣ በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ሊወስዱት ስለሚገባው ዕርምጃ መምከርና በወንጀል ችሎት ተከሳሾችን ወክሎ በመቅረብ ይከራከራል፡፡ ይህ ቢሮ ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ማነስ፣ ጠንከር ያለ የአስተዳደርና የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖር እንዲሁም አገልግሎቱ በከባድ ወንጀል ለተከሰሱ በዳኞች ጥያቄ መሠረት የሚሠራ ብቻ እንጂ በባለጉዳዮቹ ጥያቄ አለመሆኑ የሚሰጠው አገልግሎት የፍትሕ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ረገድ አነስተኛ ሆኗል፡፡

በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የፍትሕ ሥርዓቱን ለመርዳት፣ የግለሰቦች ሰብዓዊ መብት በተለይም የሴቶች፣ የሕፃናትና የአካል ጉዳቶኞች መብት እንዲከበር ለመሥራት እንዲችሉ ተደንግጓል፡፡ ይህ የሕግ ማዕቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የፍትሕ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች (የፓራ ሌጋል ሥልጠናና የሕግ ምክርን ጨምሮ) ላይ እንዲሳተፉ ቢፈቅድም፣ በአዋጁ መሠረት እነዚህ ድርጅቶች የበጀታቸውን 90% (ዘጠና በመቶ) ከአባላት መዋጮና ከአገር ውስጥ ምንጭ ማግኘት ስለሚጠበቅባቸው በበጀት እጥረት ምክንያት አገልግሎቱን ለመስጠት ይቸገራሉ፡፡

አዋጁ ከመወጣቱ በፊት በመብት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአንድነትና በነጠላ በመላው ኢትዮጵያ ነፃ የሕግ ምክር፣ የፓራ ሌጋል ሥልጠናና በፍርድ ቤት የውክልና አገልግሎት ይሰጡ ነበር፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ አክሽን ባለሙያ ማኅበር ለሕዝብ፣ የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፋኩልቲ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ ከአዋጁ መውጣት በኋላ የተወሰኑት አወቃቀራቸውን በመለወጥ የተዋቀሩ በመሆኑ ሌሎች ደግሞ በበጀት እጥረት ምክንያት አገልግሎቱን እንደቀድሞው ለመስጠት አለመቻላቸው፣ በፍትሕ ተደራሽነት ላይ የራሱ አሉታዊ አስተዋጽኦ አሳድሯል፡፡

ለአብነት ያህል የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን ብንወስድ ቀደም ሲል አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ በአምስት ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ባሉት ቅርንጫፎች፣ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ ፈቃደኛ አባላት የፓራ ሌጋል ሥልጠና፣ የሕግ ምክርና በፍርድ ቤት የመወከል ሥራዎችን ይሠራ ነበር፡፡ በተጨማሪም በነፃ የስልክ መስመር 940 ለማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል የሕግ ምክር በመስጠት የፍትሕ ተደራሽነትን ረዘም ያለ መንገድ ወስዶት ነበር፡፡ ከአዋጁ መወጣት በኋላ ግን ከ70 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን በመቀነስ የሚሰጣቸው የሕግ ምክርና የውክልና አገልግሎት በቁጥር የቀነሰ ከመሆኑ ሌላ በነፃ የስልክ መስመር የሚሰጠውን አገልግሎት አቋርጧል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የነፃ ምክር አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም፣ ጥንካሬው የቀድሞውን ያህል አይደለም፡፡

ከነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተወሰኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሕግ ፋኩልቲዎች ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ ነው፡፡ የአገልግሎቱ ስፋት ጥራትና ቀጣይነት ራሱን የቻለ ጥናት የሚፈልግ ቢሆንም፣ ቢያንስ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች አዋጅ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ሥራ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

ከፍትሕ ተደራሽነት መብት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮች
ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው፣ የፍትሕ ተደራሽነትን መብትን የሚያረጋግጡ ሕጎች መኖራቸው መልካም ቢሆንም፣ ሕጎቹ የተወሰነ ክፍተቶች ይታይባቸዋል፡፡ የሥነ ሥርዓት ሕጎቹ የፍትሕ ተደራሽነትን በሕግ አማካሪ መታገዝን በመፍቀድ የሚያረጋግጡ ቢሆንም፣ ሕጎቹ በሕግ ቴክኒካዊ ቃላት (Legal jargons) የተሞሉና ውስብስብ መሆናቸው ለኅብረተሰቡ ተደራሽ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ እንኳን ሙያውን የማያውቀው ሕዝብ ባለሙያዎች እንኳን የሥነ ሥርዓቱን ሕግ በመተርጎም ረገድ ልዩነት ያላቸው መሆኑ፣ ተደራሽነት ማጣትን ሰፊ ያደርገዋል፡፡

ሌሎቹም መሠረታውያን ሕጎች ቢሆን ሕዝቡ ሊረዳቸው በሚያስቸግሩ ቃላት የተሞሉ በመሆኑ መብትና ግዴታን የሕግ ባለሙያ ጠይቆ ካልሆነ በቀር አንብቦ መረዳት ያስቸግራል፡፡ ሕጎቹ ከወጡ በኋላም ቢሆን በበቂ ኮፒ በየቦታው የማይገኙ መሆኑ፣ ሕጉ ለመታተም የሚወስድበት ጊዜ ረዥም በመሆኑና በዚህ ጊዜ ሳይቀር ኅብረተሰቡ ሳያውቀው ተፈጻሚነት ያለው መሆኑ ተደራሽነቱን ይፈታተናል፡፡ የሕጎች የመግዣ ዋጋ ከፍተኛ መሆኑ፣ ኅብረተሰቡ ሕጉን የሚያውቅበትን ሁኔታ የሚፈጥሩ አሠራሮች በመንግሥት አለመሥራታቸው፣ አብዛኛው በገጠር አካባቢ የሚኖር ኅብረተሰብ ማንበብና መጻፍ የማይችል መሆኑ የሚወጡ ሕጎች ተደራሽነት አናሳ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በተግባር እንደምናስተውለው እንኳን ኅብረተሰቡ አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች ዳኞችን ጨምሮ የወጡትን ሕጎች በሙሉ ለማወቅ ይቸገራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሕግ ያህል ውጤት ያላቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ውሳኔዎች በፍጥነት አለመታተማቸው፣ የስርጭታቸው ማነስና የውሳኔዎቹ መብዛት የሕግ ተደራሽነት ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ከሕግ ባለሙያ ተደራሽነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ብዙ ናቸው፡፡ የሕግ ባለሙያ እጥረት መኖሩ በተለይ በገጠራማው የኢትዮጵያ አካባቢ፣ የጠበቆች የክፍያ ዋጋ የኅብረተሰቡን አቅም ያላገናዘበ መሆኑ፣ በአንዳንድ ጠበቆች የሚስተዋሉ የሥነ ምግባር ጉድለቶች መኖራቸው፣ የጠበቆች ነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት የመስጠት ግዴታቸውን አለመወጣታቸው፣ ፍትሕ ሚኒስቴርም ለመቆጠጠር የሚያስችል ሥርዓት አለመዘርጋቱ፣ የተከላካይ ጠበቃ ቢሮ በአግባቡ ተደራጅቶ አለመሥራቱ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሕግ ምክር አገልግሎት መዳከሙ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶች ተደራሽነት በተመለከት በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የተለያየ እርከን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙ ቢሆንም፣ የጂኦግራፊያዊ ተደራሽነቱ እንከን የለውም ለማለት አይቻልም፡፡ ብዙ ርቀት ተጉዘው የክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችን አገልግሎት የሚያገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቀላል አይደሉም፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በውክልና የሚያስችሉ የክልል ፍርድ ቤቶችም በክልሉ ቋንቋ በማስተናገድ የሚፈጠሩ ተደራሽነትን የሚያሳጡ ችግሮች መኖራቸውን ጸሐፊው አስተውሏል፡፡ የፍርድ ቤቶች የችሎት አስተዳደርም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለደንበኞች በተለይም ለሕፃናት ምቹ (Client friendly) አልነበሩም፡፡ ፍርድ ቤት ለመቅረብ በማሰብ የሚጨነቅ፣ ችሎት ቆሞ የሚንቀጠቀጥ፣ ክርክሩን በአግባቡ ለማስተላለፍ የሚቸገር ተሟጋች የሚስተዋለው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡

የፍትሕ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ምን ይደረግ?
የፍትሕ ተደራሽነት (Access to justice) ለብዙ መብቶች መከበር ወሳኝ ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት መብት ካልተከበረ ሰዎች መብትና ግዴታቸውን አያውቁም፤ ቢያውቁም አይጠይቁም፤ ቢጠይቁም አርኪ መፍትሔ አያገኙም፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት መብት ከተረጋገጠ ግን ግለሰቦች መብቶቻቸውን በአግባቡ ያስከብራሉ፤ በፍትሕ ሥርዓቱም ላይ ያላቸው መተማመን ይጨምራል፡፡ ይህን ለማድረግ በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ አካላት (ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ፍርድ ቤት) ሰፊ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ግልጽ ፖሊሲ መቅረፅ፣ የፍትሕ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በሕግ የቀመጡ ግዴታዎችን መፈጸም፣ መመርያዎችን ማውጣት፣ ባለሙያዎችን በስፋት አሠልጥኖ ማሰማራት ይጠበቃል፡፡ ሕዝቡ ሕጉን እንዲያውቅ በቀላሉ እንዲደርሰው ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መንግሥትና የአገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ደግሞ እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ስምምነት (Bi-lateral Agreement) ለፍትሕ ተደራሽነት ፕሮጀክት ገንዘብ ቢያፈላልጉና ቢሠሩ መልካም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ቤቶች ማኅበር ተጀምሮ የተቋረጠው የሕግ ምክር አገልግሎት በነፃ የስልክ መስመር የመስጠት አገልግሎት በፍትሕ ሚኒስቴር ቢቀጥልስ ምን ይለዋል?

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን የሕግ ጠበቃና አማካሪ ሲሆኑ፣ በኢሜይል አድራሻቸው getukow@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

በ40/60 ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ምዝገባ ሒደት በመረጃ ፍሰት መደነቃቀፍ ግራ መጋባት ውስጥ የነበሩ የዳያስፖራ አባላት በሳምንቱ መጨረሻ መረጃቸውን እያስተካከሉ ምዝገባ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡
በሌላ በኩልም ባንኩ ከ500 ሺሕ እስከ 800 ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች በዚህ የ40/60 ፕሮግራም ይመዘገባሉ ብሎ ቅድሚያ ግምት ቢሰጥም፣ ባለፈው ዓርብ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ምዝገባ ያካሄዱ ሰዎች ቁጥር  ከታሰበው እጅግ ያነሰ (81,257) መሆኑ ታውቋል፡፡ 
የ40/60 ቤቶች ምዝገባ ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 116 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችና መገናኛ አካባቢ ከአምቼ ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ተጀምሯል፡፡
ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚካሄደው ምዝገባ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዳያስፖራ) የተመደበ ነው፡፡ በዚህ የምዝገባ ጣቢያ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግንባር ቀርበው ወይም በወኪላቸው አማካይነት ምዝገባ ያካሂዳሉ፡፡
ነገር ግን በተለይ በውጭ አገር ሆነው በግንባር መቅረብ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን ከሌላ ምንጭ የሚሰሙት መረጃና ከወኪላቸው የሚሰሙት መረጃ እየተጣረሰባቸው ግራ ተጋብተው መሰንበታቸውን የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ምዝገባው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት የምዝገባ ፍሰቱ መደነቃቀፉንና በሳምንቱ መጨረሻ ፍሰቱ እየተስተካከለ መምጣቱን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ባንኩ በዳያስፖራዎች ምዝገባ ጣቢያ ገለጻ በመስጠት ያለውን የመረጃ ክፍተት በመሙላት ላይ ሲሆን፣ እስከ ዓርብ ምሽት ድረስ በአጠቃላይ ከተመዘገቡት ውስጥ ሦስት ሺሕ የሚጠጉት ዳያስፖራዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም የቀረቡት ቤቶች ባለአንድ መኝታ 55 ካሬ ሜትር፣ ባለሁለት መኝታ 75 ካሬ ሜትርና ባለሦስት መኝታ ቤት 100 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ የባለአንድ ክፍል የመሸጫ ዋጋ 162,645 ብር ሲሆን፣ የዚህ 40 በመቶ 61,960 ብር ነው፡፡ የባለሁለት ክፍል 250 ሺሕ ብር ሲሆን፣ 40 በመቶው 94,470 ብር ነው፡፡  ባለሦስት ክፍል ደግሞ 386,400 ብር ሲሆን፣ 40 በመቶው 147,200 ብር ነው፡፡ ተመዝጋቢዎች ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህንን 40 በመቶ ቆጥበው የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በቅድሚያ ሙሉ በሙሉ ክፍያ የሚፈጽሙት ቅድሚያ ዕድል ያገኛሉ መባሉ ይታወቃል፡፡
ይህ ዋጋ እንደየወቅቱ የኮንስትራክሽን ዋጋ እንደሚቀያየር ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ እስከ ዓርብ ድረስ አብዛኛዎቹ ተመዝጋቢዎች ባለሁለትና ባለሦስት መኝታ ቤት ለማግኘት ምዝገባ ያካሄዱ ሲሆን፣ ከእነዚህ ተመዝጋቢዎች ውስጥ የተወሰኑት ሙሉ ክፍያና 40 በመቶውን ከፍለዋል፡፡
መንግሥት በድርሻ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለአንድ መኝታ፣ በመቀጠል ባለሁለት መኝታና፣ በሦስተኛ ደረጃ ባለሦስት መኝታ ቤቶችን በየቅደም ተከተላቸው ለመገንባት አቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እየወጡ ባሉ መረጃዎች በተመዝጋቢው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የቤት ግንባታ ማካሄድ ስለሚያስፈልግ የቤቶቹ ዲዛይን ሊከለስ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡  

በ40/60 ምዝገባ ግራ ተጋብተው የነበሩት ዳያስፖራዎች መመዝገብ ጀመሩ
በውድነህ ዘነበ
በ40/60 ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ምዝገባ ሒደት በመረጃ ፍሰት መደነቃቀፍ ግራ መጋባት ውስጥ የነበሩ የዳያስፖራ አባላት በሳምንቱ መጨረሻ መረጃቸውን እያስተካከሉ ምዝገባ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡
በሌላ በኩልም ባንኩ ከ500 ሺሕ እስከ 800 ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች በዚህ የ40/60 ፕሮግራም ይመዘገባሉ ብሎ ቅድሚያ ግምት ቢሰጥም፣ ባለፈው ዓርብ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ምዝገባ ያካሄዱ ሰዎች ቁጥር  ከታሰበው እጅግ ያነሰ (81,257) መሆኑ ታውቋል፡፡ 
የ40/60 ቤቶች ምዝገባ ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 116 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችና መገናኛ አካባቢ ከአምቼ ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ተጀምሯል፡፡
ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚካሄደው ምዝገባ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዳያስፖራ) የተመደበ ነው፡፡ በዚህ የምዝገባ ጣቢያ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግንባር ቀርበው ወይም በወኪላቸው አማካይነት ምዝገባ ያካሂዳሉ፡፡
ነገር ግን በተለይ በውጭ አገር ሆነው በግንባር መቅረብ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን ከሌላ ምንጭ የሚሰሙት መረጃና ከወኪላቸው የሚሰሙት መረጃ እየተጣረሰባቸው ግራ ተጋብተው መሰንበታቸውን የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ምዝገባው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት የምዝገባ ፍሰቱ መደነቃቀፉንና በሳምንቱ መጨረሻ ፍሰቱ እየተስተካከለ መምጣቱን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ባንኩ በዳያስፖራዎች ምዝገባ ጣቢያ ገለጻ በመስጠት ያለውን የመረጃ ክፍተት በመሙላት ላይ ሲሆን፣ እስከ ዓርብ ምሽት ድረስ በአጠቃላይ ከተመዘገቡት ውስጥ ሦስት ሺሕ የሚጠጉት ዳያስፖራዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም የቀረቡት ቤቶች ባለአንድ መኝታ 55 ካሬ ሜትር፣ ባለሁለት መኝታ 75 ካሬ ሜትርና ባለሦስት መኝታ ቤት 100 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ የባለአንድ ክፍል የመሸጫ ዋጋ 162,645 ብር ሲሆን፣ የዚህ 40 በመቶ 61,960 ብር ነው፡፡ የባለሁለት ክፍል 250 ሺሕ ብር ሲሆን፣ 40 በመቶው 94,470 ብር ነው፡፡  ባለሦስት ክፍል ደግሞ 386,400 ብር ሲሆን፣ 40 በመቶው 147,200 ብር ነው፡፡ ተመዝጋቢዎች ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህንን 40 በመቶ ቆጥበው የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በቅድሚያ ሙሉ በሙሉ ክፍያ የሚፈጽሙት ቅድሚያ ዕድል ያገኛሉ መባሉ ይታወቃል፡፡
ይህ ዋጋ እንደየወቅቱ የኮንስትራክሽን ዋጋ እንደሚቀያየር ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ እስከ ዓርብ ድረስ አብዛኛዎቹ ተመዝጋቢዎች ባለሁለትና ባለሦስት መኝታ ቤት ለማግኘት ምዝገባ ያካሄዱ ሲሆን፣ ከእነዚህ ተመዝጋቢዎች ውስጥ የተወሰኑት ሙሉ ክፍያና 40 በመቶውን ከፍለዋል፡፡
መንግሥት በድርሻ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለአንድ መኝታ፣ በመቀጠል ባለሁለት መኝታና፣ በሦስተኛ ደረጃ ባለሦስት መኝታ ቤቶችን በየቅደም ተከተላቸው ለመገንባት አቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እየወጡ ባሉ መረጃዎች በተመዝጋቢው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የቤት ግንባታ ማካሄድ ስለሚያስፈልግ የቤቶቹ ዲዛይን ሊከለስ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡  
አዲስ አበባ ነሐሴ 11/2005 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አሳሰቡ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለ20 ቀናት ሲወስዱ የቆየውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ በይፋ ተጠናቋል። የትምህርት ሚኒስቴር 1 ሺህ 700 የሚሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶች፣ የዩኒቨርስቲ ፋኩልቲ ዲኖችና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ዛሬ በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የተጀመረውን አገራዊ ዕድገት ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠልጥኖ የሚወጣው የሰው ኃይል ብቃቱ የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል። ለኢንዱስትሪ ልማት መፋጠን እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በየአካባቢው ከሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን እንዲቀረፁ በማስቻል ረገድ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም አመልክተዋል። አገሪቱ ከድህነት ለማውጣት በሚደረገው ጥረት ፈጣንና ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ቀጣይነት ያለው ሥራ ለመስራት ግብርናው ወሳኝ ሚና መጫወቱን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የአገሪቱን የግብርና ዘርፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማስቻል እየታዩ ያሉትን ጅምር ዕድገቶች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምርና ስርፀት አስደግፈው ሊሰሩ እንደሚገባቸው አቶ ኃይለማሪያም አስገንዝበዋል። በዚህ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ መንግሥት በተቻለው አቅም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። በመላ አገሪቱ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ምሁራንና የመስኩ ባለሙያዎች አገራዊ ዕድገት ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ካባ ኡርጌሳ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለ20 ቀናት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ሲወስዱ የቆዩትን የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ በይፋ መጠናቀቁን ገልጸዋል። ሥልጠናው ወሳኝ የሆኑ የአገሪቱን ፖሊሲዎች በመምረጥና ለአመራርነት ሊረዳቸው በሚችሉ ነጥቦች ላይ በማተኮር እንዲሰጥ መደረጉን ጠቅሰው በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ አመራርን ለማፍራት እንዲያስችላቸው አቅም የፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል። በዲላ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ በላይነህ ሥልጠናው አመራርን ሊገነባ የሚችል ወሳኝ አቅም እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በሥልጠናው ያገኘቱን ዓቅም ወደ ተግባር በመለወጥ የትምህርት ሰራዊት በመፍጠር ረገድ አገሪቱ በትምህርት ልማት ዘርፍ በአምስት ዓመቱን ዕቅድ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት እንደሚጠሩ አስታውቀዋል።
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=10963
By    KIRUBEL TADESSE, Associated Press
ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) — A European Union parliament delegation on Wednesday called on Ethiopia's government to release jailed journalists and activists, but in a sign the call may not be heeded the delegation was denied from visiting a prison it had been approved to see.
The head of the delegation, Barbara Lochbihler, said Ethiopia is jailing journalists and activists for "exercising their legitimate right to freedoms of expression, association and religion." The group is concerned by reports of misuse of the country's anti-terrorism legislation to stifle dissent, she said.
"Despite the country's excellent constitution, we note flaws in the impartiality of the judicial system," Lochbihler told journalists at a press conference Wednesday.
A spokesman for the Ethiopian Prime Minister said the country doesn't have any political prisoners and that prisoners would not be released "just because some European Union members said so."
According to the Committee to Protect Journalists, the Ethiopian government criminalizes the coverage of any group the government deems to be a terrorist group, a list that includes opposition political parties.
"Among those jailed is Eskinder Nega, an award-winning blogger whose critical commentary on the government's extensive use of anti-terror laws led to his own conviction on terrorism charges," the group said in its latest survey, which placed Ethiopia among the world's top ten worst jailers of journalists.
The EU parliament delegation said certain broadcasters are jammed in Ethiopia and that access to the Internet and social media are "regularly restricted." The practice is at odds with the Ethiopian constitution, the delegation said in a statement.
The four-person delegation, drawn from the parliament's subcommittee on human rights, said the Ethiopian government must guarantee freedom of speech and the right to peaceful assembly at all times in accordance with its constitution and obligations under international law. The delegation met top government officials, activists and leaders of the opposition.
Earlier on Wednesday the delegation was scheduled to visit to the country's Kaliti prison where most activists are believed to be serving their sentence. But the prison director turned the group back on arrival, saying "he didn't have time to work with you," according to a member of the delegation, Jorg Leichtfried.
Leichtfried told a news conference their visit was "overshadowed" by the incident. He described it as an episode he doesn't wish to experience again. All four delegation members spoke about the incident, which appeared to have frustrated them.
The delegation said Ethiopia itself has requested international assistance to improve its detention centers and their visit was to have a firsthand experience of the detention conditions.
Getachew Reda, a spokesman for Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, said he was not aware of any decisions either to grant permission to see the prison or to deny it. Getachew said only family members can visit the prisoners.
"We don't have any single political prisoner in the country. We do have, like any other country, people who were convicted of crimes including terrorism who are currently serving their sentence. They would only be freed when either they complete their sentence or probation on good behavior," Getachew told the Associated Press on Wednesday. "We are not going to do release anyone just because some European Union members said so."
He criticized the delegation's statement, calling it "unhelpful" to relations between Ethiopia and the EU.
The EU is one of Ethiopia's largest donors with millions of dollar spent on development projects across the country.
Hailemariam was scheduled to meet the visiting delegation on Wednesday night.
The European lawmakers also met with African Union officials. Lochbihler criticized Nigeria and the AU for allowing Sudanese President Omar al-Bashir to travel to Abuja earlier this week. The International Criminal Court has an arrest warrant out for Bashir.