POWr Social Media Icons

Monday, July 8, 2013

የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ ሃላፊነታቸው እንደተነሱ ተገለፀ፡፡

ተጠሪነቱ ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሆነው የቤቶች ኤጀንሲ ከትላንት በስቲያ ሶስቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከሥራ ሃላፊነታቸው ያነሳው በተለያየ ደረጃ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከአንድ ዓመት በላይ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የጠቀሱ ምንጮች፤ ሃላፊዎቹ በኪራይ ሰብሳቢነትና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ተገምግመው ነው ከሥራ ሃላፊነታቸው የተነሱት ብለዋል።
http://dezetube.com/article_read.php?a=451