POWr Social Media Icons

Friday, July 5, 2013

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ?
መንጌ የነገረኝ ቀልድ ትቅደም፤
መንጌ ማለት አሉኝ ከምላቸው ጓደኞቼ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እሳት የላሰ የአራዳ ልጅ ነው፡፡ “ካራዳ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ፤ ባይበሉም ባይጠጡ ስንቅ ይሆናል ቀልዱ”  የተባለለት ጨዋታ አዋቂ!
አንድ ሙዝ ነጋዴ ነበር አለኝ መንጌ…
እሺ…
ሙዙ ገበያ ሲያጣ ምን ያደርጋል መሰለህ…
እ…
የተሰቀለውን ያወርደዋል፡፡ መሬት የነበረውን መስቀያው ላይ ያንጠለጥለዋል፡፡ እንደርሱ ብቻ አይደለም፤ “ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ…” ሲልም ያበረታታዋል… አለኝ፡፡
እኔ ፋራው የምጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ የሚገርመው… ከዛስ…  አልሸጥ ያለው ሙዝ ይሻጣል….  ወይስ ይንቀሳቀሳል…?
መንጌ ይስቃል… እርስዎም ይሳቁ፡፡
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሙዙ ነጋዴ ናቸው፡፡ የሱቁ ባለቤቶች “እስቲ ደግሞ ለአኬር፤ ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ” ይበሉ … ብለዋችው ይሁን; በራሳቸው ተነሳሽነት እንጃ ሞዛዞቻቸውን ቦታ አቀያይረዋቸዋል፡፡ (ሙዛ ሙዞቻቸውን ማለቴ ነው….)
አቶ ሬድዋን የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር… ተደርገዋል፡፡ የምርም ስለ ኢህአዴግዬ ዋይ ዋይ ለማለት እርሳቸው ሳይሻሏት አይቀሩም፡፡  ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን ቻርጅ እንዳለቃቸው በጣም ያስታውቃሉ፡፡ (ጢን… ጢን.. ማለት ከጀመሩ ቆይተዋል) ስለዚህ ነጋ ጠባ ስለ ድርጅታቸው በየአደባባዩ እየተከሰቱ “በላውድ ስፒከር” ሊጮሁላት አይቻላቸውም፡፡ እናም፤ ባትሪ ፉሉ አቶ ሬድዋን መተካታቸው ለዚህ ቦታ ትክክል ይመስለኛል፡፡
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስቴር… ይሄኛው ያስቃል፡፡  የሰውዬው የስራ ልምድ እኮ አስተኳሽነት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ የስራ ልምዳቸው እንደ ጥይት የሚተኳኮስ የትራንስፖርት ስርዓት ይዘረጉልናል፡፡ ብለን ተስፋ እናድርግ እንዴ…!
በእውነቱ ቀልድ በብዛት የሆነበት ፓርላማ ነውኮ ያለን! ለአስፋልቱ የተሸለ ስርዓት ዝርጋታ “የሰው ያለህ” በሚለው የትራንስፖርት ችግር ላይ፤ የሰው ልጅን አስፋልት ላይ በጥይት ሲዘረጉ የነበሩ ሰውዬ ሲሾሙ አስደናቂ ታሪክ ላይ መመዝገብ ያለበት ታሪክ ነው!
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የማፈናቀል ጥበባቸውን  ለምን እንደተፈለገ እንጃ ይዘውት ወደ ትምህርት ሚኒስቴርነት ከች ብለዋል፡፡ ይቺ ስልጣን ከአቶ ደመቀ በምን ምክንያት “መንጩ” እንደተደረገች እንጃ… አቶ ደመቀ ስራ በዝቶባቸው ይሆናል እንዳንል… እርሳቸው ለራሳቸው አንድ ሶስተኛ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡ እንኳንስ ለአንድ ሶስተኛ ምክትልነት እና ያኔ አቶ ሃይሌ ብቻቸውን ሙሉ ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው እየሰሩ፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነቱንም “ቀጥ” አድርገው ይዘውት ነበር፡፡  ታድያ አንድ ሶስተኛ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነትና የትምህርት ሚኒስቴርነት ምን አላት…
የሆነ ሆኖ የትምህርት ሚኒስቴርነቱን ቦታ አቶ ሃይሌ ለአቶ ሽፈራው ሽጉጤ እነሆ በረከት ብለዋቸዋል፡፡ እኛም እየጠየቅን እንገኛለን፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፈው በክልላቸው ያማረሯቸውን እና ከክልላቸው ያባረሯቸውን ሰዎች እያስታወስን፤
የትምህርት ሚኒስቴርነት ብቃት የሚለካው በማማረር ወይስ በማባረር… ! ? እንላለን፡፡
ችግሩ መንግስታችን የፈለገ ጥያቄ ቢጠየቅ መልስ መስጠት መልስ የመጥራት ያክል ይከብደዋል እና መልሱ “መ” ነው፡፡  መ- መልሱ የለም፡፡
አረ እረስቼያቸው እኒያ ፍትህ ሚኒስቴርም በምን እንደወረዱ ሳይነገረን ሌላ በምን እንደመጡ የማናቃቸው ሰውዬ ተሸሙብን አይደል!
ለማንኛውም ሹመኞቹ ቢቀያየሩም ባይቀያየሩም ዋናው የድርጅታችን ልብ መግዛት ነው እና ድርጅታችን ኢህአዴግ እኛን ቦንድ ግዙ እንደምትለን ሁሉ፤ እኛም እባክሽ ልብ ግዢ እንላታለን! ቦንዱ ለራሳችሁ ብዬ ነው እንደምትለንም ሁሉም፤ እኛም ልብ ግዢ ማለታችን ለራስሽ ብለን ነው እንላታለን!
House of Peoples Representatives today approved the appointment of ten ministers nominated by Prime Minister Hailmeriam Desalegn.
Before announcing his appointments, PM Hailemariam told parliamentarians that Deputy Prime Minister Demeke Mekonnen is relieved of his post as minister of education. Hailemariam appointed Shiferaw Shigute as minister of education.
Shiferaw has been serving as Chief Administrator of Southern Nations, Nationalities and Peoples' Region (SNNPR) since March 2006.
Redwan Hussien, who was public mobilization and participation advisor minister to the PM and head of EPRDF Secretariat, has replaced Bereket Simon as Minister of Government Communications Affairs Office. Bereket and outgoing Addis Ababa City mayor Kuma Demeksa yesterday were appointed as policy and research advisor ministers to the Prime Minister.
Workneh Gebeyehu, who was commissioner of the Federal Police Commission, is appointed as Minister of Transport replacing Diriba Kuma.
Mekonnen Manyazewal, who was minister of Industry, is replaced by Ahmed Abetew, deputy chief administrator of Amhara regional state and head of the region's Trade and Industry Bureau. Mekonnen is appointed as Commissioner of the newly established National Planning Commission.
Roman G. Sellasie, Member of Parliament and government whip, will serve as chief government whip at the house of people's representative, replacing Aster Mamo.
Demitu Hambessa, Speaker of Oromia Regional State Council (Cheffe Oromia), is appointed as the minister for Technology & Science replacing Dessie Dalke.
The vacant Ministerial position at the Ministry of Justice following the dismissal of Berhan Hailu is now filled with the appointment of Getachew Ambaye. Getachew was public relations advisor to the Addis Ababa Mayor with the rank of Deputy Mayor.
Bekir Shale's last month appointment as Director General of Ethiopian Revenues & Customs Authority (ERCA) is now made official by Hailemariam.
The house approved their nomination with one abstinence. Today's ordinary session also saw the approval of the proposed 154 billion birr budget for the 2013/14 budget year.
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የመንግስት ሚኒስትሮችን እና የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በ1 ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
በዚህም መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ - የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ-  የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ - የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ - በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ - የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው - የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ - የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ - የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው - የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙ ሲሆን ፥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።