POWr Social Media Icons

Wednesday, March 20, 2013

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁ ሁለት አጥኝዎች ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁት ዊልያም ማርዣክ እና ሞርጋን ማርኪስ-ቧር ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡ 
ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች
​​
ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ፓሪስ-ፈረንሣይ የሚገኘው ዓለምአቀፍ ቡድን ኢትዮጵያ ያንን የርቀት መከታተያ ሶፍትዌር ግለሰቦችን ለመሰለል ጉዳይ እንደምትጠቀም እንደሚያውቅ ቢገልፅም አንድ የኢትዮጵያ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባለሥልጣን የሚባለውን ክስ አስተባብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
​​
ሲቲዘን ላብ የሚባለው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ማዕከል ባወጣው ዘገባ መሠረት የስለላ ማልዌሩን ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሃያ አምስት ሃገሮች የሸጠው ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድኑ - አርኤስኤፍ “የኢንተርኔት ጠላቶች” ሲል ከፈረጃቸው አምስት ሃገሮችና አምስት ድንበር ዘለል ድርጅቶች አንዱ የሆነው “ጋማ ኢንተርናሽናል” የሚባል ለንደን - እንግሊዝ የሚገኝ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራና ንግድ ላይ የተሠማራ ቡድን ነው፡፡
ጋማ ኢንተርናሽናል
​​
ጋማ ኢንተርናሽናል ማልዌሩን የሠራውና የሚሸጠው ሕፃናትን የሚያማግጡና ጥቃት የሚያደርሱባቸውን፣ ሽብርተኞችንና የተደራጁ ወንጀሎችን፣ ጠላፊዎችንና ሕገወጥ የሰዎች ሽግግርን ለመከታተል መሆኑን ተናግሯል፡፡ ደንበኞቹ እነማን እንደሆኑ ግን መግለፅ አልፈለገም፡፡
ዊልያም ማርዣክ እና ሞርጋን ማርኪስ-ቧር
​​
የኢትዮጵያ መንግሥት “ፊንስፓይ” የሚባለውን የጋማውን ማልዌር የሚጠቀመው የግንቦት ሰባት አባላትንና ግንኙነቶቻቸውን ለመከታተልና ለመሰለል ነው የሚለውን የሲቲዘን ላብን ጥቆማ አስመልክቶ የተጠየቀው ግንቦት ሰባት የተባለው ክትትል በአባላቱና በአመራሩ ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚካሄድ፣ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑንና ሁኔታውን ለመቆጣጠርና አደጋን ለመከላከል የሚያስችለው የተጠናከረ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን፣ ባለሙያና አሠራር ያለው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ግንቦት ሰባት
​​
በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥቱን ለመጣል ማንኛውንም የትግል ዘዴ የሚጠቀመው ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የኢንተርኔት ወይም ሳይበር ጦርነት እያካሄደ መሆኑን የግንቦት ሰባት ምክር ቤት ፀሐፊ አቶ አምሣሉ ፅጌ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ስሞታ ያቀርባሉ ።
አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የውጭ መንግሥታት የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ በተለያዩ ጊዜያት በሚያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እነዚህን ዘገባዎች አይቀበልም ። ይልቁንም በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች መብቶችን በሚጥሱ ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶችና የውጭ መንግሥታት እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስሞታ ያቀርባሉ ። እነዚህ ወቀሳዎች የሚቀርቡበት መንግሥት በቅርቡ «ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር » ያለውን ሠነድ አዘጋጅቷል ። በተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህ የድርጊት መርሃ ግብር ፋይዳ ና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩልን አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ አቶ እንዳልካቸው ሞላ በቀድሞው አጠራሩ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ተመራማሪን ጋብዘናል ። ሙሉውን ውይይቱን ያድምጡ ።የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ነው።
ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው ደኢህዴን ከረፋድ ጀምሮ የማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን ምርጫ እያካሄደ ይገኛል።
ለድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ 70 ዕጩዎች የተጠቆሙ ሲሆን ፥ ክአንዚህ ውስጥ 65ቱን በመምረጥ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ 9 ዕጩዎች ለኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲሁም 15 ዕጩዎች ደግሞ ለደኢህዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴነት ይመረጣሉ።
በጉባኤው እጩ ሆነው ከቀረቡት መካከል አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ ዶክተር ካሱ ኢላላ ፣ አቶ አለማየሁ አሰፋ ፣ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ አቶ ሳኒ ረዲ እና ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ይገኙበታል።
ምርጫው በአሁኑ ሰአት እየተካሄደ ሲሆን እንደተጠናቀቀም ውጤቱ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


Addis Ababa, March 20 (WIC) - Ethiopia, one of the world's most ancient countries, is broadening its cultural footprint in India, with the opening of the first Ethiopian Cultural Centre, complete with a traditional coffee shop, in the capital.
The centre -a sprawling facility with crafts display rooms, meeting space and an elegant coffee shop in the diplomatic enclave of Chanakyapuri - will serve the "purpose of introducing Ethiopian culture to India and to the international community", Genete Zewide, the ambassador of Ethiopia to India, said.
The centre was inaugurated Tuesday evening by the Ethiopian state minister of industry Tadesse Haile in the presence of the Ethiopian envoy, Indian businessmen, a host of dignitaries from African nations, here for the 9th India-Africa Conclave, and members of the diplomatic corps.
Addressing the inauguration, Ambassador Genete said the major attraction of the Ethiopian Cultural Centre was an Ethiopian Coffee Shop that will be open from 11 a.m. to 5 p.m. and promote the country's rich coffee tradition in India as a symbol of its cultural bonding.

The act of drinking coffee is a ceremonial women's bonding rite in Africa. Known as the 'Coffee Ceremony', the ritual has a "cultural, social and economic significance", Ambassador Genete said.
"The women of the community - who work for long hours - sit over coffee to relax and discuss their problems," she said. The envoy said she was also planning to add a library for students to study Ethiopian culture and popularize it".
"There should be more people to people cultural relationship. We are hoping that the centre will not be limited to showcasing Ethiopian culture alone. This should be the seat of other African cultures as well. My other colleagues (from African nations represented in India) will use it to demonstrate their culture," the envoy said.
Ethiopia, the second-most populous country in Africa with 91 million people, and India share a history of relationship that spans more than 2,000 years, industry state minister Tadesse Haile said.

"Both countries were trading various items along the Indian Ocean. Currently both Ethiopia and India enjoy political relations and a fast-growing mutually beneficial economic cooperation," the minister said.
In the cultural sector, the two nations engage with the exchange of a large number of students. "We will be able to play a significant role with the centre to introduce India to Ethiopian culture," the minister said putting it in context.
He said although India and Ethiopia were geographically apart, the centre would show how close the countries were.
Ethiopia has inked a new MoU with the Confederation of Indian Industry (CII) for greater cooperation in the industrial sector as well. The inauguration of the centre was marked by a bouquet of the country's colorful performance traditions. (IANS) Source :Waltainfo.com
Hawassa March 16/2013 Construction of a safe water project launched in Aleta Wondo Town, Sidama Zone of South Ethiopia Peoples' State with 16 million Birr is nearing completion, the town municipality said. The Municipality told ENA that the project includes digging of water wells, installation of water pipelines and construction of water reservoirs. It said the government allocated the budget for implementation of the project. So far digging of two water wells, installation of over 18km water pipe lines, construction of two water reservoirs and seven water distribution centers is undertaken. The project scheduled to be finalized at the end of the current Ethiopian budget year will give service to more than 30,000 residents for the coming twenty years, the Municipality said.

በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ሔክታር መሬት የሚሸፍን ቀርከሃ አለ ተብሎ ይታመናል፡፡ በየዓመቱም እስከ 12 ሚሊዮን ቶን የሚገመት የቀርከሃ መጠን ለተለያዩ ምርቶች ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በዘርፉ የተደረገ ጥናት ያመለክታል፡፡
ሀብቱ ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ቢውል ደግሞ ለ500 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ከ500 ሚሊዮን እስከ 700 ሚሊዮን ብር ገቢ ሊያስገኝ የሚችል ምርት በየዓመቱ ማምረት እንደሚቻል ሰሞኑን በአፍሪካ የቀርከሃ ሀብት ዙሪያ የተደረገ ዓውደ ጥናት ላይ ተጠቅሷል፡፡

ቀርከሃ በየዓመቱ በብዛት ሊበቅል የሚችል ተክል ሲሆን በአግባቡ ከተያዘና ከተጠበቀ ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በተጨማሪ ምርቱን ሳያቋርጡ ለዓመታት ማግኘት እንደሚቻል ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ቀርከሃን በመቀጠም በኢትዮጵያ የተሠሩ ሥራዎችን በተመለከተ መጋቢት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በተካሄደ ዓውደ ጥናት ላይ ማብራሪያ ቀርቦ ነበር፡፡

ዓውደ ጥናቱን አስመልክቶ በቀርከሃ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን ያቀረበው መረጃ በቀርከሃ የተሠሩ 200 ሺሕ ቤቶች ለገጠሩ ኅብረተሰብ በግልና በሰፈራ መሥራቱን ያስታውሳል፡፡ በገንዘብ ሲሰላ ሁለት ሚሊዮን ብር እንደሚጠጋም አስፍሯል፡፡ በቀርከሃ የተሠሩ 700 ሺሕ የቤት ቁሳቁስ መሣሪያዎች የተመረቱ ሲሆን፣ ከ20 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችም የሥራ ዕድል እንደተፈጠረ ያትታል፡፡ በዚሁ መረጃ መሰረት፣ 250 ሺሕ ቶን ቀርከሃ ለማገዶ መዋሉን፣ በገንዘብ ሲመዘንም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ 45 ቶን ቀርከሃ ለከብቶች መኖነት መዋሉ ከመገለጹም ባሻገር፣ በአዲስ አበባና አሶሳ የተከፈቱ ሁለት ፋብሪካዎች እስካሁን ድረስ ከ30 ሺሕ ቶን በላይ የቀርከሃ ምርትን ለተለያየ አገልግሎት ማዋላቸውም ተዘርዝሯል፡፡ የሚያመርቱት ውጤት በገንዘብ ሲሰላም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ተገምቷል፡፡

እንዲህ የተነገረለትን ቀርከሃ፣ ኢትዮጵያ በአግባቡ አልተጠቀመችበትም፡፡ የቀርከሃ ምርትን ግብዓት በማድረግ በዘመናዊ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ምርቶችን ለማምረት አልተቻለም፡፡ ቀርከሃን ጥሬ ዕቃ አድርገው የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች ቁጥር ሁለት ብቻ መሆኑ ጥሩ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ግን ይህንን ምርት በአግባቡ ለመጠቀም ብዙ ሥራዎች ተሠርቷል ይላል፡፡

በቀርከሃ ልማት፣ አጠቃቀምና ምርት ላይ እንዲሁም በቀርከሃ ምርት ሥራ ላይ ለ2,500 ሰዎች በተግባር የተደገፉ የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል፡፡

ለኢትዮጵያ ተስማሚ የሆኑ 15 ዓይነት የቀርከሃ ዝርያዎች ከቻይና፣ ከህንድና ከደቡብ አሜሪካና ከሌሎች አገሮች በማስገባት፣ በማላመድና በማባዛት እንዲተከሉ መደረጋቸውን፣ በግብርና ሚኒስቴር ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መላኩ ታደሰ ይገልጻሉ፡፡

ዘመናዊ የቀርከሃ ከሰል አመራረትና አጠቃቀም ቴክኖሎጂዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት የተለያዩ አነስተኛና ጥቃቅን ማኅበራትን በማደራጀትና በማሠልጠን የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀርከሃ ኢንዱስትሪን ለማቋቋም አንድ ሔክታር መሬት በቂ ነው የሚሉት የቀርከሃና ራታን መረብ ድርጅት፣የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ሁንዴ፤ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ የምትሆንበትን የተለያዩ ሥራዎች እየሠራች ሲሆን 10 ዘመናዊ ፋብሪካዎች ቢቋቋሙ እንኳ፣ ጥሬ ዕቃው ከበቂ በላይ ያገኛል ብለዋል፡፡ ብዙ ሊሠራበት ይችላል ይላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከቀርከሃ በቀላሉ የሚሠራው ጥርስ መጐርጐሪያ (ስቴኪኒ) እንኳ ከውጭ መግባት እንዳልነበረበት የሚገልጹት አቶ ተስፋዬ፣ በበቂ ሁኔታ እዚህ ሊመረት ይችል ነበር ይላሉ፡፡

በዓውደ ጥናቱ ላይ እንደተጠበቀሰውም የቀርከሃ ሥነ ሕይወት፣ አስተዳደግ፣ አመራረትና አጠቃቀም ላይ የተለያዩ ጥናቶች እንዲካሄዱ በማድረግ ከሰባት በላይ መርጃ መመሪያዎች በማሳተምና በማሠራጨት ሥራ ላይ መዋሉንም ዘርፉን ለማሳደግ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚጠቀስ ነው ተብሏል፡፡

ቀርከሃ አማራጭና ታዳሽ ኃይል በመሆን ለማገዶና ለከሰል አገልግሎት እንደሚውል በጥናት ተረጋግጦ በጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል፣ የቀርከሃ እንቡጥ (Bamboo Shoot) ለምግብነት የሚውል ሲሆን እስካሁን ድረስ ግን በአገራችን ጥቅም ላይ የዋለው ከ3 እስከ 5 ቶን ያለው ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ወደፊት ለምግብነት እንዲውል፣ መሥራት እንደሚገባም ተመክሮበታል፡፡

እንደዓውደ ጥናቱ አዘጋጆች ገለጻ፣ ዓውደ ጥናቱ በአጠቃላይ የዘርፉ ልማትና አጠቃቀም በአገር ብሎም በአኅጉር ደረጃ እንዲሻሻልና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲደረግበት የአገሮች ትብብር፣ ትስስርና ቅንጅት የጎላ ድርሻ እንዲኖረው ፈር የቀደደ ነው፡፡

በአፍሪካ ውስጥ ቀርከሃ በተፈጥሮው ሰው ሰራሽ ዘዴ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ያለውን የቀርከሃ -ብት ብዛትና ዓይነት በአፍሪካ አኅጉር ብሎም በዓለም እንዲታወቅ የሚደረግበትን ሁኔታ በማመቻቸቱ ረገድ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል፡፡ በአኅጉሩ ውስጥ ይህ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም በአሁኑ ጊዜ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ሌሎች የእስያ አገሮች የደረሱበትን የቀርከሃ ቴክኖሎጂ ምጥቀት ልምድ ለመቅሰምና ሽግግር ለማድረግ የሚቻልበትን ዘዴም ይመቻቻል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ከሰሐራ በታች ባሉ አገሮች ሦስት ሚሊዮን ሔክታር የሚሸፍን የቀርከሃ ደን እንደሚገኝ ሲታወቅ፣ ከአጠቃላይ የቀጣናው የደን ሽፋን የአራት በመቶ ድርሻን የያዘ ነው፡፡ በዓለም ላይ የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የገበያ ድርሻ ያለው የቀርከሃ ሀብት፣ በአግባቡ ቢሠራበት ለአፍሪካ የወጪ ንግድ አስተዋጽኦ ከማድረግ በላይ፣የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እንደሚረዳ ይታሰባል፡፡  

የቀርከሃ ውጤቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተቀባይነት እየጎላ መምጣቱን ለውጭ፣ ለአገር ውስጥ ንግድና ለብዙኀኑ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በአውደ ጥናቱ የቀረቡ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የቀርከሃና ራታን መረብ ድርጅት ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆና መመረጧን የገለጹት አቶ መላኩ፣ በአኅጉሩ ያላትን ከፍተኛ ኃላፊነት፣ ከመወጣት አኳያ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ተቀርፆላቸው ሊሠሩ የታቀዱ ዋና ዋና የተባሉ ተግባራት እንዳሉም አስታውቀዋል፡፡ እንደ አቶ መላኩ ገለጻ፣ በዚህ ዕቅድ መሠረት በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቻይና መንግሥት በተገኘ ድጋፍ አንድ ተቋም ይቋቋማል፡፡

ከዚህም ሌላ በአሁኑ ጊዜ የግብርና ሚኒስቴር ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትን ያካተተ አንድ ዓብይ ኮሚቴ በማቋቋምና በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሊሠሩ ከታቀዱ ሥራዎች መካከል የቦታኒካል ጋርደን ማቋቋም፣ የቀርከሃ ቦታ መከለልና በተሻሻለና ሳይንሳዊ በሆነ አያያዝ መጠበቅ የዕቅዱ አካል ነው፡፡

ቀርከሃ ላይ እሴት የመጨመር ሥራዎች፣ የአቅም ግንባታ መመሪያዎችንና የሕግ ማዕቀፎችን መከለስና ማዘጋጀት፣ ምርምርና ልማት ማካሄድ፣ ችግኝ ጣቢያ ማቋቋም፣ ነባር የቀርከሃ ደኖችን መልሶ ማልማትና አዲስ ተከላ ማካሄድ፣ በቀጣይነት ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ የልማት የትብብር መስኮችን በመለየት በፕሮግራመችና ፕሮጀክቶች የተደገፉ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ማሳደግ የሚቻል መሆኑንም ባለሙያዎቹ አመልክተዋል፡፡

የግል የቀርከሃ አምራች ፋብሪካዎች ቁጥርም እየጨመረ ለመምጣቱ፣ አገር በቀልና የውጭ ባለሀብቶች በቀርከሃ ኢንዱስትሪው ለመሰማራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት ሒደት ላይ መገኘታቸው ዋቢ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቀርከሃ ኢንዱስትሪ ከተሰማሩ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የአደል ኢንዱስትሪስ ሥራ አስኪያጅ አቶ አዳነ በርሔ፣ ከቀርከሃ የማይመረት ነገር እንደሌለ፣ ከሚመረቱት ውስጥ  የቤት ቁሳቁሶች፣ ጣውላዎች፣ ከሰል፣ ስቴኪኒ፣ ምንጣፍና ሰንደል የመሳሰሉት ምርቶች ሰፊ ገበያ እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡

የምርት አቅርቦቱን በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሠራሮች በመደገፍ በዓለም ገበያ ሊሸጡ የሚችሉ ምርቶች ማቅረብ ከተቻለ፣ ለዘርፉ ምቹ የሆነ ሥነ ምኅዳር በኢትዮጵያ በመኖሩ የቀርከሃ ተፈላጊነት እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ይታሰባል፡፡

በኢትዮጵያ የተስተናገደውና የአፍሪካ የቀርከሃ ምርትን በተመለከተው ዓውደ ጥናት ላይ የቀረቡ ጥናቶች፣ በግብርና ሚኒስቴርና ዓለም አቀፍ የቀርከሃና ራታን ኔተዎርክ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት፣ ከጀርመን ተራድኦ ድርጅትና ከካናዳ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ እንደሆነም ተገልጿል፡፡