በመጪዎቹ አስር ቀናት የበጋው ደረቅ ጸሃያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ሲዳማን ጨምሮ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ ታህሳስ 4/2006 በመጪዎቹ አስር ቀናት የበጋው ደረቅ ጸሃያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ። በአንዳንድ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደሚያይልና አልፎ አልፎ የቅዝቃዜው መጠን ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል፡፡ በአንዳንድ የደቡብና የደቡብ ምእራብ እንዲሁም የሰሜን ምስራቅ ስፍራዎች መጠነኛ የደመና ሽፋን መጨመር ስለሚጠበቅ የሌሊቱንና የማለዳውን ቅዝቃዜ ጋብ ሊያደርገው እንደሚችል ይጠበቃል። በዚህም ጊዜ ወቅቱ ለሰብል ስብሰባና ድህረ ሰብል ስብሰባ አመቺ ሁኔታን ቢፈጥርም ደረቅና ቀዝቃዛ አየር ወደ አገሪቱ የሚገባ በመሆኑ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ስለሚጠናከር በአንዳንድ ለውርጭ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በአዝርእትና በእንስሳት ጤናማ እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል ብሏል። በሌላም በኩል በአስሩ ቀናት መጨረሻ የደቡብ፣ የደቡብ ምእራብና የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች የደመና ሽፋን መጨመር ስለሚጠበቅ ሊፈጠር የሚችለውን ቅዝቃዜ እንደሚያረግበው ይጠበቃል፡፡ በዚህ መካከል የሚፈጠረው መጠነኛ ቅዝቃዜ ለአዝርእትና እንስሳት ጤናማ እድገት አመቺ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል ይጠበቃል ብሏል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር