የቀድሞ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) እህት የልማት ድርጅቶች የት ደረሱ?



  • የሲዳማ ዞን መንግስት በቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት የልማት ድርጅቶች ላይ በያዘው የተሳሳተ ኣቋም ድርጅቶቹን ኣጠናክሮ ለታለሙለት ኣላማ እንድውሉ እና ስፊውን የሲዳማን ህዝብ እንድጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ ድርጅቶቹን እንደጠላት ንብረት በማየት የሚጠፉበትን እና የሚበተኑበትን ሁኔታዎችን ብቻ በማመቻቸት ላይ የተጠመዷል
  • የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የመንግስት ድጋፍ ያስፈልገዋል
ክፍል ሁለት
የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ተቋም (SMFI) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፋቃድ ኣግኝቶ በራሱ ቦርድ የሚተዳደር የገንዘብ ተቋም ነው።ተቋሙ በከተሞች ኣካባቢ ቤትን እና ሌሎች ንብረቶችን በመያዝ ብድር የመስጠት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን፤ እንደሌሎች መሰል የኣገሪቱ የብድር እና የቁጠባ ተቋማት ሁሉ ሰዎች በቡድን ተደራጅተው ገንዘብ የሚበደሩበትን መንገዶች በማመቻቸት ኣገልግሎት ይሰጣል።
በኣገልግሎቱም እስከ ሃምሳ ሺ ነው የሚያበድር ሲሆን በግለሰብ ደረጃ ግን ከሶስት ሺ ብር በላይ ኣያበድርም። ለነገሩ በኣሁኑ ወቅት በኣገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት ብድሩን የሚወስዱ ሰዎች በሶስት ሺ ብር ምን ኣይነት ኢንቨስትመንት ልያደርጉ እንደምችሉ ግልጽ ባይሆንም ብዙዎቹ በገንዘብ ኣያያዝ ላይ ትምህርት ሳይሰጣቸው የብድሩ ተጠቃሚ ስለምሆኑ የተበደሩትን ገንዘብ ላላለሙለት ጉዳይ ላይ በማዋል እዳ ውስጥ ስገቡ ታይተዋል። ሰዎች የተበረሩትን ገንዘብ በውቅቱ ኣለመመለሳቸው ከብድር እና ቁጠባ ተቋሙ ጋር እንድካሰሱ ምክንያት ሆኗል። ጉዳዮቻቸው በፍርድ ቤቶች እየታየ ያሉ እና ቤት ንብረቶቻቸውን ሽጠው ለመክፈል የተገደዱ ብዙዎች ናቸው። ለማንኛውን ተቋሙ በኣሁኑ ጊዜ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎትን በተዳከመ መልኩ በመስራት ላይ ይገኛል።
ለሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ተቋም መዳከም ምክንያቱ ምንድነው ብለን ስንል በዞኑ መንግስት ትኩረት መነፈጉ እና በሃላፊትን እና በብቃት የምመራውን ኣካል ማጣቱ ብሎም የሰለጠነ የሰው ኃይል እና የፋይናንስ ኣቅም ውስን መሆን እንደምክንያት ይነሳሉ።
የሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘገባ እንደምያመለክተው፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ከብድር እና ቁጠባ ተቋሙ ገንዘብ እንደፈለጉ እንዳይበደሩ በተበደሩት ገንዘብ ላይ ከፍተኛ የሆነና በየትኛውን ኣገር ተሰምቶ የማይታወቅ ኢንተረስት ወይም ወለድ ማለትም 18 ከመቶ እንድከፍሉ ይጠየቃሉ። ይህንን ከፍተኛ ወለድ ላልመክፈል ስሉም ሌላ ኣማራጨ የብድር ኣገልግሎቱ ሰጭ ተቋም እንድመርጡ ኣድርጓቸዋል። በዞኑ ውስጥ ያሉት ገንዝብ የመበደር ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ከሲዳማ ማክሮፋይናንስ ተቋም ከመበደር ይልቅ ከኦሞ ማክሮ ፋይናንስ መበደርን እንደምመርጡ ሆኗል ማለት ነው። ይህም ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ከመሆኑ በላይ በኣገሪቱ ገዥው ፓርቲ በተለይ ወጣቶችን ኣደራጅቶ የራሱን ፖለቲካ ማራመጃነት ለመጠቀም ሲል የሚያመቻቸውን የብድር ኣገልግሎት በኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በኩል እንድሰጥ ስለምደረገ የሲዳማ ማክሮፋይናንስ የገንዘብ ኣቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ መጥቷል። በተጨማሪም የሲዳማ ማክሮፋይናንስ ተቋም በራሱ ብድር ለመስጠት የምጠቀመውን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚበደር በመሆኑ እና ተቋሙ ያበደራቸው ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ በወቅቱ ካለመመለሳቸ ጋር የያይዞ ተቋሙ በራሱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የማግኘት እድል ጠቧል፤ ይህም ተቋሙ ለብድር ፈላጊ ደንበኞቹ ተገቢውን ኣገልግሎት እንዳይሰጥ ኣድርጎታል።
በተቃራኒው የኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በክልል ደረጃ የተቋቋመ ተቋም በመሆኑ በሲዳማ ውስጥ ብሎም በክልሉ ጠንካራ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል። በተለይ በሲዳማ ዞን ውስጥ cash crop ማለትም ቡና፤ ጫት እና እህል ባለባቸው ወረዳዎች በምገኙ በእያንዳንዳቸው ቀበሌያት ውስጥ LOAN OFFICER በመቅጠር የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ይህም የሲዳማ ማክሮፋይናንስ በዞኑ ውስጥ የነበረውን የብድር እና ቁጠባ ገበያ ለኦሞ ማክሮፋይናንስ እንድያጣ ሆኗል።
የክልሉ መንግስትም ብሆን የወጣቶች entrepreneurship ፕሮግራሙ የሚሆን ገንዘብ በኦሞ ማክሮ ፋይናንስ በኩል እንድገባ እና እንድወጣ ኣድርገዋል።በተጨማሪም ከኦሞ ማክሮፋይናንስ የሚበደሩ ስዎች 10 ከመቶ ብቻ ወለድ እንድከፍሉ ስለምጠየቁ በርካታ የኣገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ኦሞ ማክሮ ፋይናንስን እንድመርጡ ምክንያት ሆኗል። ከዚህም ባለፈ ኦሞ ማክሮፋይናንስ ያበደሩት ገንዘብ በወቅቱ እንድመለስላቸው ለተበዳሪዎች ተገቢ የሆነ የገንዘብ ኣያያዝ ትምህርት ስለምሰጡ ብሎም በየቀበሌያቱ ባሰማሯቸው ባለሙያዎች በኩል በተበዳርዎቹ ላይ ክትትል ስለምያደርጉ የሚያበድሩትን ገንዘብ በወቅቱ በተበዳሪዎች እንዲመለስላቸው ኣቅም ፈጥረዋል። የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እና ካቢኔዎችም ብሆኑ በምንቀሳቀሱባቸው የሲዳማ ቀበሌያት ህዝቡ የኦሞ ማክሮፋይናንስ ኣገልግሎት ተጠቃሚ እንድሆን የመቀስቀስ ስራ ይስራሉ ተብሏል።

ልክ ኣገሪቷም የውጭ የገንዘብ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ በማድረግ ለኣገር ውስጥ የገንዘብ ተቋማት ከሌላ እንደምሰጡት ሁሉ፤የሲዳማ ዞን መንግስት በዞኑ ውስጥ ከኦሞ ማክሮፋይናንስ በፊት ተቋቋሞ ኣገልግሎት ይሰጥ የነበረውን የሲዳማን ማክሮፋይናንስ ተቋም በማጠናከር በዞኑ ውስጥ ሌላ ማይክሮፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ የዞኑ ህዝብ ንብረት የሆነውን የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የብድር እና የቁጠባ ተቋም ከማጠናከር ይልቅ በማዳከሙ ላይ በመበረታቱ ለብዙ ሲዳማዎች መለያቸው እና ኩራታቸው የሆነው ተቋም ከስሮ ለመዘጋት እያመራ ነው።



የሲዳማ ዞን መንግስት በቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት የልማት ድርጅቶች ላይ በያዘው የተሳሳተ ኣቋም ድርጅቶቹን ኣጠናክሮ ለታለሙለት ኣላማ እንድውሉ እና ስፊውን የሲዳማን ህዝብ እንድጠቅሙ ከማድረግ ድርጅቶቹን እንደጠላት ንብረት በማየት የምጠፉበትን እና የምበተኑበትን ሁኔታዎችን ብቻ በማመቻቸት ላይ የተጠመደ ይመስላል። ነገር ግን ድርጅቶቹ የሰፊው የሲዳማ ህዝብ ንብረት መሆናቸውን በመገንዘብ በሰው ኃይል እና በገንዘብ የምጠከሩበትን መንገድ ቢያመቻች መልካም ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር