የቀድሞ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) እህት የልማት ድርጅቶች የት ደረሱ?

ለሲዳማ ህዝብ ልማት እና ብልጽግና እንዲያመጡ ተብለው የተቋቋሙ የቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን(SDC) እህት የልማት ድርጅቶች በዞኑ መንግስት ትኩረት በመነፈጋቸው የተነሳ ፈርስዋል፤ በመፍረስም ላይ ናቸው
  • የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን(SDC)ሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎች ለመስራት ቀርቶ ድርጅቱ በራሱ በሁለት እግሩ መቆም ኣልቻለም
  • ፉራ ኮሌጅ፦ ከምመለከተው ኣካል ትኩረት በመነፈጉ የተነሳ ባጋጠመው የትምህርት ጥራት ጉድለት ኣብዛኛዎቹን የትምህርት ክፍሎች በመዝጋት ላይ ያለ ኮሌጅ ሆኗል
  • ሬድዮ ሲዳማ፦ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ለመንግስት የፖለቲካ ማካሄጃነት በመዋል ላይ ያለ
  • ጋራምባ ኮንስትራክሽ እና ኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ፦ተበትነው እና ፈርሰው ታሪክ የሆኑ
  • ሲዳማ ማክሮፋይናስ፦ በኦሞ ማክሮፋይናንስ የታፈነ
ክፍል ኣንድ
ኤስዲስ በኣይርሽ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ እና በሲዳማ ውስጥ በርካታ የልማት ተግባራትን ስያከናውን የቆየ ድርጅት ነው። ይሄው ድርጅት በወቅቱ በርካታ እህት ድርጅቶችን በስሩ ኣቋቁሞ ይስራ የነበረ ሲሆን ካቋቋማቸው ድርጅቶች መካከል በኣሁኑ ጊዜ ኣብዛኛዎቹ ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ በማገልግል ላይ ናቸው፤ የቀሩት ደግሞ ፍርስዋል።

እንደ ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘገባ ከሆነ፦ከሲዳማ ልማት ፕሮግራምነት ወደ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽነትን የተቀየረው SDC፤ በወቅቱ የሲዳማ ህዝብ ኩራት ሆኖ ለሲዳማ ህዝብ ልማት የምቆረቆሩ ግለሰቦች እንደንብ የምሯሯጡበት የነበረ ሲሆን፤ በኃላ ላይ በመንግስት ጠልቃ ገቢነት የተነሳ የስራ ኣቅሙ የተመታ እና የላሸቀ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በኣሁኑ ወቅት ስፋፊ የእርሻ መሬት በኮንትራት መልክ በመያዝ በተለይ በቆሎን በመዝራት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። ሆኖም ምርቱንም በመሸጥ የምያገኙውን ገቢ ለሰራተኞቹ ደሞዝ ከመክፈል ውጭ ሌላ ምንም የረባ እና የምታይ የልማት ስራ ሲስራ የማይታይ ድርጅቶ ሆኗል። በምያሳዝን ሁኔታ የተቋቋመበትን ዓላማ በማሳካት ለሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎች ለመስራት ቀርቶ ድርጅቱ በራሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያነስ በመሄድ ላይ ያለ ነው።

ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን ድርጅት የሆነው ፉራ ኮሌጅ ከSDC ጋር በቦርድ የምተዳደር ሲሆን ከዚህ በፊት ለበርካታ ለተቸገሩ የሲዳማ ልጆች የትምህር ድጋፍ ያደርግ የነበረ፤ ብዙ የሲዳማ ምሁራንን እስከ ውጭ ኣገራት በመላክ ሲያስተምር የነበረ ቢሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት በትምህርት ጥራት ላይ በመውስድ ላይ ባለው እርምጃ ተወዳዳር መሆን ያልቻለ እና በኮሌጁ ኣንዳንድ የትምህርት ክፍሎች በትምህርት ጥራት መጓደል የተነሳ ኣብዛኛዎቹ የትምህርት ክፍሎች ተዘግተው በኣሁኑ ጊዜ በሶስት የትምህርት ክፍሎች ብቻ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ነው። ኮሌጁ ከምመለከተው ኣካል ትኩረት በመነፈጉ ልክ እንደሌሎቹ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት ድርጅቶች በመክሰም ላይ ያለ ኮሌጅ ነው።

ሶስተኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሆነው ሬድዮ ሲዳማ በኣሁኑ ጊዜ በሲዳማ ትምህር መምሪያ ስር የምተዳደር ሲሆን፤ ባለቤት በማጣቱ የተነሳ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ መንግስት የራሱን ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ እና ፕሮግራሞች የምያስራጭበት ሬድዮ ጣቢያ ሆኗል።

ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሆነው ጋራምባ ኮንስትራክሽ በበኩሉ፤ በሲዳማ ውስጥ የምካሄዱትን የልማት ስራዎችን በጥራት እና በብቃት እንድሰራ ብሎም ለሲዳማ ልጆች የስራ እድል እና የስራ ልምድ ማካበቻ እንድሆን ተብሎ የተቋቋመ ቢሆንም፤ ሀላፊነት ወስዶ የምመራ ኣካል ባለመኖሩ ከዚህ በፊት ለስራ ተብለው የተገዙ ከባድ ማሽኖች ሳይቀር ተሽጠው ወይም ለሌላ ድርጅቶች ተሰጥተው ስላላቁ በመፍረስ ላይ ያለ ብቻ ሳይሆን የፈረሰ ድርጅት ነው።

ኣምስተኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት ኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ ከስሙ ውጭ ይሄን ስርቷል የምባል ነገር የለውም። ስራ ካለመስራቱ በላይ ለስራ ተብለው የተገዙ ከባድ ማሽኔሪዎች ተሽጠው ስላላቁ ከጋራምባ ኮንስትራክሽ የተለየ እድል ኣልገጠመውም። ለድርጅቱ መዘጋት ሃላፊነት ወስዶ የምመራው ኣካል ማጣቱ እንደምክንያት ይነሳል።ድርጅቱን በተመለከተ ሌላው ኣሳዛኙ ነገር ለኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ የተሰጠው በሃዋሳ ከተማ የምገኘው ቦታ በኣሁኑ ጊዜ Tony printing press ለተባለ ማተሚያ ድርጅት በክራይ ተሰጥቷል።

ስድስተኛውን እና ሌላኛው የሲዳማ ልማት ኮፐሬሽን እህት ድርጅት የሲዳማ ማክሮፋይናስን በተመለከተ በክፍል ሁለት እንመለስበታለን።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር