ሃዋሳ፦የመናፈሻ ፓርክ ብርቅ የሆነባት ከተማ


ሃዋሳ ከተማ የሲዳማ መናገሻ
በኣለማችን ላይ በርካታ ዘመናዊ ከተሞች በተለይ በኣሁኑ ጊዜ ከኣለም የኣየር ሙቀት ጋር ተያይዞ ብሎም ለከተሞቹ ውበት እና ለከተሞቹ ነዋሪዎች ምቾት ሲባል በርካታ የመናፈሻ ፓርኮችን እየገነቡ እና ለኣገልግሎት እያበቁ ይገኛሉ። መናፈሻ ፓርኮች በከተሞች መኖራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች በእረፊት ጊዚያቸው ንጽህ ኣየር እየተነፈሱ ኣልያም በለምለም ዞፎች መካከል እየተንሸራሸሩ ጊዚያቸውን እንድያሳልፉ ያስችላቸዋል።

ለኣብነት ያህል ኣብዛኛውቹ የደቡብ ኣሜሪካ ኣገራት ከተሞች ማለትም ከትናንሾቹ እንስቶ እስከ ሜክስኮ ሲቲ እና የብራዚሏን ሳኦፖሎን የመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች እያንዳንዱ የከተሞቹ መንደረ በፕላዛ ወይም በግሪንኤሪያ የተሞሉ ናቸው። እነዚህ ፓርኮች በከተሞቹ ነዋሪዎች ተሞልተው ይውላሉ። ፓርኮቹ የተለያዩ የስፖርት ማዘወተሪያ ማዕከላትን የያዙ በመሆናቸው በርካታ ወጣቶች ጊዚያቸውን ኣልባለ ቦታ ከማሳለፍ በተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች ላይ እንዲያሳልፉ ኣስችሏቸዋል።

በደቡብ ኣሜሪካ የከተሞች ውበት የምለካውም በያዙት ፓርኮች እና በፓርኮቹ ውበት ነው። በርግጥ የከተሞቹ ውበት እና ንጽህና የነዋሪዎቹን ስልጣነ ያሳያል። የሰሜን ኣሜሪካ ወይም የኣውሮፓ ከተሞችንም ሲንመለከት በውብ ፓርኮች የተሞሉ ናቸው። የየከተሞቹ ኣስተዳደር ለፖርኮች ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ስጥተው ይሰራል። ነዋሪዎችን ከየከተሞቹ ኣስተዳደር በላይ ለፓርኮቹ ውብ እና ንጽህ መሆን የበኩላቸውን ይወጣሉ።

ከኣውሮፓ እና ከደቡብ ኣሜሪካ ከተሞች ፊታችንን ወደእኛዋ ከተማ ስንመልስ ሌላ ታሪክ ነው የምናየው። የሲዳማዋ ዋና ከተማ ሃዋሳ ከሊባኖስ ተነስቶ እስከ ሞዛሚብክ ለምዘንቀው ታላቁ ስምጥ ሸለቆ እምብርት ላይ የምትገኝ ከመሆኗ የተነሳ ሞቃት ኣየር ኣመቱን ሙሉ የምታስተናግድ ከተማ ናት። ሞቃት ኣየር ያላት መሆኗ ደግሞ በርካታ የመናፈሻ ፓርኮች እንዲኖሯት የግድ ይላታል። ለዚህም ይመስላል በከተማዋ ውስጥ በግሪንኤሪያነት ታስበው በማስተር ፕላን የተከለሉ ቦታዎች በርካታ መሆናቸው።

በሃዋሳ ከተማ ማስተር ፕላን በርካታ ቦታዎች ለፓርክነት ታስበው የተከለሉ ቢሆንም በፓርክነት የለሙት ወይም የከተማዋ ኣስተዳደር ወደ ፓርክነት የለወጣቸው ቦታዎች በጣም ጥቂት ናቸው ለማለት ያስችላል። የከተማው ኣስተዳደር ሃዋሳን የውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቱ ለማድረግ ኣቅድ ኣንግቦ የተነሳ ቢሆንም በፓርኮች ልማት በኩል ብዙ ይቀረዋል።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ የላከልን መረጃ እንደምያመለክተው ከሆነ፤ የከተማው ኣስተዳደር በማስተር ፕላን ለመናፈሻ ፓርኪነት የያዛቸውን ቦታዋች ለሌላ ተግባራት ኣውሏቸዋል። ለምሳሌ ያህል በመናፈሻ ፓርኪነት በተያዙ ኣንዳንድ ቦታዎች ላይ የጋራ ቤቶች ግንባታ ማለትም ኮንዶሚኒዬም ተገንብቶባቸዋል እንዲሁም ለመገንባታ ታስቦባቸዋል። ሌሎቹ ደግሞ በህገ ወጥ መንገድ እና በሙሲና ለግለሰቦች ተሰጥተው ከመናፈሻ ፓርኪነት የወጡ በመሆናቸው ለታሰቡለት ኣላማ ሳይውሉ ቀርተዋል።

በርግጥ በዚህ ኣመት በኣንዳንድ ለመናፈሻነት ተብለው በተተው ቦታዎች ላይ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ስም ዛፎች የተተከሉ ቢሆንም ክፍት ቦታዎችን በዛፍ ከመሙላት ባለፈ ለኣከባቢው ነዋሪዎች በምመች መልኩ በፓርክነት ድይዛን ተሰርቶላቸው በመልማት ላይ ኣይደሉም።


ከተማይቱን እንደተባለው ውብ እና ንጽህ በማድረግ የምስራቅ ኣፍሪካ የቱርስት እና ኮንፈራንሲንግ ማዕከል ማድረግ ያለ መናፈሻ ፓርኮች ግንባታ የምታስብ ኣይሆንም። ስለዚህ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ለከተማዋ ውበት እና ለነዋሪዎቿ ምቾት ብሎም የኣለም ኣከባቢ ኣየር ሙቀትን ለመከላከ የከተማዋ ነዋሪዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ በመናፈሻ ፓርኮች ልማት ላይ ትኩረት በመስጣት ብሰራ መልካም ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር