በደቡብ የአመራር አካላት ለስፖርት ትኩረት እንዲሰጡ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳሰቡ፤ በኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች ነጥብ ኣልባ ጉዞ ቀጥሏል


የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች የሆኑት ሃዋሳ ከነማ እና ሲዳማ ቡና በሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ጫዋታ በተገጣሚዎቻቸው በመሸነፋቸው በሊግ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻ ደረጃዎችን ይዘው ይገኛሉ። በሌላ በኩል፤የስፖርት ልማቱን በማጠናከር ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠሩ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ።
የደቡብ ክልል የስፖርት ምክር ቤት 17ኛው መደበኛ ጉባዔ ከትናንት በስቲያ በሃዋሳ ተካሂዷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ስፖርት ያለው ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ ዕድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡
«ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራት፣ በጥናትና ምርምር ሥራዎች የክልሉን የስፖርት ዕድገት የመደገፍና ለኅብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን የአመራሩ ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ጠንክሮ መሥራት ይገባል» ብለዋል።
በክልሉ የዘርፉን ዓላማ ለማስፈጸም በፋይናንስ፣ በአደረጃጀትና በአመራር የስፖርቱ ልማት ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የማድረግ፣ ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቆ ራሱን እንዲችል ማድረግ ይጠበቃል።
ኅብረተሰቡ በሚያመቸው ሁኔታ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻል፣ እንዲሁም የሴቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራዎች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ደሴ ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ የስፖርት ልማት በማፋጠን የኅብረ ተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ምርጥ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት የሚያግዙ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች፣ የልማት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።
በዘርፉ በየደረጃው የተፈጠረውን የሕዝብ ንቅናቄ የማሳደግና የተደራጀ የለውጥ ሠራዊት መገንባት የዘርፉ ውጤታማነት ዘላቂነት ባለው መልክ ለማረጋገጥ ቁልፍ ድርሻ ስላለው አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት ብለዋል፡፡
የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር መዘረዲን ሁሴን በበኩላቸው ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅነትና ለማኅበራዊ ግንኙነት ከሚያበረክተው ጉልህ አስተዋጽኦ በተጨማሪ ከፍተኛ ገቢ ከሚገኝባቸው የቱሪዝምና የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ በመሆኑ ዕድገቱን ለማፋጠን ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ባለፉት ሦስት የዕድገትና ትራንስፎ ርሜሽን ዕቅድ ዓመት ስፖርትን በማስፋ ፋትና በማጎልበት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ ከነጥብ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁስ ለክለቦች ድጋፍ ተደርገዋል፡፡
ከዚሁ በተጨማሪ ከሁለት ሺ በላይ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ግንባታ፣ በቤንች ማጂና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሁለት የሥልጠና ማዕከል ግንባታ ሌሎችም ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በሃዋሳ ከተማ በተደረገው የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት 17ኛው መደበኛ ጉባዔ የ2005 ዕቅድ አፈፃፀም፣ የ2006 የሴክተሩ ዕቅድና ትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም የስፖርት ሴክተር የሕዝብ ንቅናቄ ማቀጣጠያና የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ለ2006 የበጀት ዓመት በሴክተሩ ለሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች ከ115 ነጥብ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር