የሲዳማ ዞን መንግስት ለዞኑ ቡና ነጋዴዎች የገንዘብ ብድር ሊያመቻች ይገባል ተባለ

በሲዳማ ወቅቱ የቡና ነው፤ በርካታ የቡና ንግድ እንቅስቃሴ የምታይበት ጊዜ ነው። የሲዳማ ቡና ኣምራቾች በቡና ምርታቸው ገንዘብ የሚያገኙበት እና ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የምልኩበት፤ ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁሶች ጨምሮ ማንኛውንም ኣቅም የፈቀደውን ለማድረግ የገንዘብ ኣቅም የሚኖራቸውን ወቅት ነው።

ሆኖም ኣንድችግር ኣለ ይላል የጥቻ ወራና ዘገባ፤ ይሄውም የቡና ዋና ካለፈው ኣመት ኣንጻር ስነጻጸር በመውረዱ ነው። ለቡና ዋጋ መውረድ እንደምክንያት ከምነሱት ጉዳዮ ኣንደኛው የቡና ነጋደዎች በብዛት ወደ ቡና ንግዱ ኣለመግባታቸው ሲሆን፤ ለዚህም ቢሆን ምክንያቱ ባንኮች ብድር ባለመልቀቃቸው ነው ተብሏል።

እንደ ዘገባው ከሆነ፤ባንኮቹ ለሲዳማ ቡና ነጋዴዎች ብድር ለመገደባቸውም እንደምክንያት የሚያነሱት ባለፈው ኣመት ለነጋደዎቹ ያበደሯቸውን ገንዘብ በገቡት ውል መሰረት በወቅቱ ባለመመለሳቸው ነው።

በዚህ በሲዳማ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ልውውጥ በምካሄድበት በዚህ ወቅት ባንኮች ብድር መገደባቸው እና ማዘገየታቸው ብዙዎችን ነጋዴዎችን ያዛዘነ ጉዳይ ሲሆን፤ የዞኑ መንግስት በጉዳዩ ላይ ጠልቃ በመግባት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በዝምታ ማየቱ ኣነጋጋሪ ሆኗል።

ሆኖም ሰሞኑን ባንኮች ለኣንዳንድ የቡና ነጋደዎች ትንሽ ገንዘብ ማበደራቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ብድሩን ያገኙትም በመንግስት ልማታዊ ባለሃብት የምባሉት መሆናቸው ታውቋል።

ዘንድሮ ቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደሮችን ኣንድኪሎ ቡና በስድስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በመሸጥ ላይ ቢሆኑም በቡና ዋና ደስተኞች ኣለመሆናቸውን በመናገር ላይ ሲሆኑ እንደምክንያት የሚያነሱትም ባለፈው ኣመት በተመሳሳይ ወቅት ኣንድ ኪሎ ቡና ከስምንት ብር እስከ ኣስራ ሁለት ብር የሸጡ በመሆኑ እና ዘንድሮ የቡና ዋጋ በመውረዱ ነው።

እስከኣሁን ባለው መረጃ መሰረት በርካታ የቡና ነጋደዎች ቡና መግዣ ገንዘብ በማጣታቸው እየተጉላሉ ሲሆን፤ለቡና ዋጋ በውረድ ኣንደኛው ምክንያት ከዚህ በፊት እንደምደረገው በርካታ የቡና ነጋደዎች ወደ ቡና ገበያ በገንዘብ እጦት የተነሳ ባለመግባታቸውን በተብሏል።


በኣሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ ልማታዊ ነጋዴዎች ብቻ በቡና ገበያ ውስጥ እንደልባቸው በመነገድ ላይ መሆናቸውን ጥቻ ወራና ከኣለታወንዶ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር