ደደቢትና ሀዋሳ ከነማ ተጋጣሚያቸውን አሸነፉ

በኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር እሁድ ህዳር 15/03/2005 ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከነማ ሲዳማ ቡናን እንዲሁም  ደደቢት አርባ ምንጭ ከነማን በተመሳሳይ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡
ደደቢት በብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች ምክንያት ከሶስት በላይ ተጨዋቾን በማሰመረጡ ከኢትዮጵያ ቡናና  ከሲዳማ ቡና የነበረውን ሁለት የፕሪሜየር ሊግ ጨዋታ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡
የመጀመሪያ የሊጉን ጨዋታ ከብሔራዊ ቡድኑ መልስ ከአርባ ምንጭ ጋር ያደረገው የባለፈው ዓመት ሻምፒዮና ደደቢት ፣በዳዊት ፍቃዱ በተገኘች ብቸኛ ጎል የመጀመሪያ የሊጉን ድል ማስመዝገብ ችሏል፡፡
ደደቢት በአጭር የኳስ ፍሰት ጨዋታውን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሎታል፡፡
በደቡብ ደረቢ በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ሀዋሳ ከነማ በበኩሉ በአንዷለም ንጉሴ ወሳኝ ጎል የመጀመሪያ የሊግ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
ሀዋሳ ከነማ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው መብራት ሀይልን ቢያሰተናግድም ሽንፍት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡ሲዳማ ቡና በአንጻሩ ሁለቱንም ጨዋታዎች በመሸነፍ ደካማ አጀማምር አሳይቷል፡፡
ሊጉን መከላከያ በሶስት ጨዋታ 7 ነጥብ ሰብስቦ መምራት ሲችል፣ ሙገር ሲሚንቶ በሁለት ጨዋታ 6 ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ እንዲሁም ወላይታ ዲቻ በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታ 4 ነጥብ በመያዝ ከ1 እስክ 3 በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር