በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት 8 ከተሞች ሲዳማን ወክለው ይወዳደራሉ


ከህዳር 7 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በባህርዳር ከተማ በሚካሄደው የከተሞች ሳምንት ላይ ዞኑን በመወከል የሚሳተፉት የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች ለኩ ዳዬ ያዬ አለታ ጩኮ ወንዶ ኬላና መጪሾ ከተሞች ሲሆኑ የሲዳማ ዞን መንግስት በከተሞቹ  የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማሟላት ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግበራት ህብረተሰቡ ተሳታፊ በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ማበርከት ኣለበት ማለቱ ተሰምቷል። ዝርዝር ዜናው የኢዜኣ ነው።

ሐዋሳ ህዳር 4/2006 በከተሞች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማሟላት ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግበራት ህብረተሰቡ ተሳታፊ በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ አስታወቀ። አምስተኛውራ የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት በማስመልከት መምሪያው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሻሸመኔ 103 ነጥብ 4 ጋር በመተባበር በይርጋለም ከተማ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸው ባለፉት ዓመታት በከተሞች የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማስፋፋት ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ለገሰ ማሬሮ እንዳሉት ከ1989 ዓ.ም በፊት በዞኑ የነበሩት 14 ከተሞች ምንም ዓይነት የመሰረተ ልማት ተቋማት ያልተሟላላቸውና ለኑሮ ምቹ ያልነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ በተፈጥሮ ያላቸውን ሀብት አልምተው ለመጠቀም በርካታ ችግሮች እንደነበሩባቸው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በዞኑ በፕላን የሚመሩና የመብራት፣ የስልክ፣ የመንገድና ሌሎች አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ተቋማት የተገነቡላቸው 52 ከተሞች እንደሚገኙ በከተሞቹ በሆቴል፣ በቡና ኢንዱስትሪ የተለያዩ አነስተኛና መካከለኛ ፋብሪካዎች ተከፍተው ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል። በዞኑ ይርጋለምና አለታወንዶ ከተሞች በከንቲባ የሚመሩ መሆኑንና በከተሞቹ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ለኑሮ ተስማሚና ምቹ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን እንደቻለ አቶ ለገሰ አስታውቀዋል። በዞኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነዋሪውን በማሳተፍ ባከናወኗቸው ተግባራት በፈጣን ደረጃ በማደግ ላይ ካሉ ከተሞች ውስጥ ይርጋለም አለታ ወንዶ በንሳ ዳዬ አለታ ጩኮ ወንዶ ኬላ ማጪሾና ተፈሪ ኬላ ከተሞች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተለይ የዳዬ ከተማ ከራሳቸው ወጪ ላይ በጀት በመመደብና ህብረተሰቡን በማስተባበር በኮብል ስቶን የመንገድ ስራ ከፍተኛ ተግባር ከማከናወናቸው በተጨማሪ ለበርካታ የከተማዋ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ያከናወኑት ተግባር ለሌሎች ምሳሌ መሆን እንደሚችል ገልጸዋል። የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 4 ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ገመዳ በበኩላቸው እንዳሉት በከተሞች እየተከናወኑ ያሉ ተግበራትን ለህዝብ በማውጣት መገናኛ ብዙሃን እያበረከቱ ያለው ተግባር ከፍተኛ መሆኑንና ይህን ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል የሚጠበቅባቸውን ግዴታ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ በዞኑ ከሚገኙ ከተሞች ከህዳር 7 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በባህርዳር ከተማ በሚካሄደው የከተሞች ሳምንት ላይ ዞኑን በመወከል የሚሳተፉት የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች ለኩ ዳዬ ያዬ አለታ ጩኮ ወንዶ ኬላና መጪሾ ከተሞች መሆናቸው ተገልጿል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=13477&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር