የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ2005 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል፤


የወባ በሽታና የመከላከል ጥረቶች
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ2005 .ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል፤


ከሁለት ሺ ሜትር በታች በሆኑ የወይና ደጋና ቆላማ አካባቢዎች ሁሉ ይተላለፋል የወባ በሽታ። በአብዛኛው ከክረምት ወራት በኋላ ከመስከረም እስከ ህዳር ባለው ወቅት ስርጭቱ የሚጨምር ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች ከበልግ ዝናብ ተከተሎ ባሉ ወራትም ይከሰታል።
ስለ ወባ በሽታ አጠቃላይ ግንዛቤ ለማስረጽ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም በሽታውን በመከላከል በኩል ስለሚደረጉት ጥረቶች መረጃ ለማግኘት ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጎራ ብለን ነበር። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሪት ህይወት ሰለሞን ስለወባ በሽታና የመከላከል ጥረቱን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተውናል።
«የወባ በሽታ ፕላስሞድየም የሚባል በአይን የማይታይ ረቂቅ ጥገኛ ተህዋስ በደም ውስጥ መኖር፣ ማደግና መራባት ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው። ይህ በሽታ በአለም ላይ በብዙ ቦታዎች ይከሰታል። በአገራችንም ሰባ አምስት በመቶ በሚሆነው የቆዳ ስፋት የወባ በሽታ ይታያል። ስልሳ ስምንት በመቶ የሚሆነው ህዝብም ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ይገኛል» ይላሉ ወይዘሪት ሕይወት።
የወባ በሽታ አኖፊለሰ በመባል በምት ታወቀው እንስት የወባ ትንኝ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋስ ነው። ትንኟ የምታስተላልፈው የበሽታው መንስኤ የሆነውን ተህዋስ ነው፡፡ በሃገራችን ሁለት ዋና ዋና የወባ ተህዋስ ዝርያዎች አሉ የሚሉት ቡድን መሪዋ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ በመባል እንደሚ ታወቁ ይናገራሉ።
በሽታው አኖፊለስ በመባል በምትታወቀው እንስቷ የወባ ትንኝ ንክሻ ምክንያት ከህመም ተኛ ሰው ወደ ጤነኛ ይተላለፋል። አኖፊለስ የም ትባለው ትንኝ በተፈጥሮዋ የመትመገበው ደም ነው፡፡ ደም መመገቧ ደግሞ እንቁላሏን ለማሳደግ ይጠቅማታል፡፡እግረ መንገዷንም የበሽተኛውን ሰው ደም ከተህዋስያኑ ጋር አብራ ትመገባላች። ተህዋስያኑ በትንኝዋ ውስጥ በማደግ በሌላ ወቅት ከጤነኛ ሰው ደም በምትመገብበት ጊዜ ይተላለፋሉ፡፡
የወባ በሽታ በሰውነት ውስጥ መሰራጨት እንደ ጀመረ ዋና ዋና ምልክቶች መታየት ይጀም ራሉ የሚሉት ወይዘሪት ሕይወት ምልክቶቹም ብርድ ብርድ ማለትና የማንቀ ጥቀጥ ሰሜት፣ ትኩሳትና ማላብ፣ የጀርባና የሰውነት መጋጠ ሚያዎች ቁርጥማት ፣ከፍተኛ ራስ ምታት ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸው። እነዚህ የበሽታው ምልክቶች የታዩበት ህመምተኛ በአቅራቢያው በሚገኝ የጤና ደርጅት በመሄድ መመርመር ይኖርበታል ሲሉ ይመክራሉ።
በቅድሚያ የጤና ባለሙያው የበሽታውን ምልክቶች በማየት ሊገምት ይችላል የሚሉት ወይዘሪት ሕይወት በመገመት ብቻ ሰይሆን የደም ምርመራ በማድረግ በሽታው ሰውነት ውስጥ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ፈውስ የሚሰጥና ከስቃይ የሚገላግል መድሃኒት ይታዘዛል። ህመምተኛው የታዘዘለትን መድሃኒት እንደ ጀመረ ለውጥ ስለሚታይበት ተሽሎኛል ብሎ ምድኀኒት ማቋረጥ የለበትም። ተገቢውን ህክምና በአግባቡ ወስዶ መዳን ካልቻለ ወይም በሽታው እየተጠናከረ ከሄደ በአስቸኳይ ወደ ጤና ባለሞያ በመቅረብ እራስን ከሞት መታደግ ይገባል የሚለውን አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ።
በወባ በሽታ ላለመያዝ የቅድመ መከላከል ስራው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ይላሉ ወይዘሪት ሕይወት። በቅድሚያ የወባ ትንኝ እንዳይፈጠር ማድረግ ከመከላከያዎቹ አንዱ ነው። የወባ ትንኝ እንቁላል የምትጥለው በሰዎች መኖሪያ አካባቢ የሚገኙ የተጠራቀሙ ውሃዎች፣ ኩሬ ፣ረግራማ ስፍራ ፣የመስኖ ቦይ ፣ውሃ ለማቆር የሚችሉ ቁሳቁሶችና ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ጉድጓዶች ውስጥ ነው፡፡
እንቁላሎቹ በውሃ አካል ውስጥ እንደ ተጣሉ ከእስከሳምንት በሚሆን ጊዜ ውስጥ የተለያዩ የእድገት ደረጃዎችን በማለፍ በራሪ ትንኞች ይሆናሉ።ይህ ስራ ደግሞ ህብረተሰቡን በማስተማር ያቆሩ ቦታዎችን ማፅዳት፣ ለሰውና ለአንስሳት አገልግሎት የማይውሉና የማይንቀ ሳቀሱ የውሃ አካሎችን በማስወገድ እጮች እንዳይራቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
በሽታውን ለምታስተላልፈው ትንኝ ንክሻ ላለመጋለጥ በምሽትና በሌሊት መላ አካልን የሚሸፍኑ ልብሶችን መልበስ፣ በመኝታ ጊዜ በፀረ ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበር መጠቀም ፣አንድ አጎበር የሚያገለግለው ለአመታት ስለሆነ የአገልግሎት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት መቀየር፣ የቤት መስኮቶችና ክፍተቶችን ትንኝ ማስገባት በማይችሉ ወንፊት ሽቦዎች በመጋረድ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆ ኑንም ይመክራሉ።
ህብረተሰቡን በማስተባበርና በማስተማር ረገድ በመላው ሃገሪቱ የሚገኙ ከ38 ሺ በላይ የሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና 16ሺ ጤና ኬላዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው የሚሉት ወይዘሪት ሕይወት ባለሙያዎቹ ከህብረተሰቡ ጋር ባላቸው ቅርበት ትምህርት በመስጠት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የተቻለ ሲሆን በዚህም በፍጥነት ወደ ጤና ኬላ በመሄድ አፋጣኝ ህክምና ስለሚደረግ የሞት መጠን ቀንሷል። በወረርሽኝ መልክ እየተከሰተ የበርካታ ሰዎችን ህይዎት ማጥፋቱ ቀርቷል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
የወባ በሽታን ለመቆጣጠር በ1996 .ም የተሰራጩ 47 ሚሊዮን በላይ አጎበሮች ያሉ ሲሆን የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የመተካት ስራና ከዚህ በፊት አጎበር ላልነ በራቸው ሙሉ በሙሉ የማሰራጨት ተግባር ተከናውኗል። የቤት ለቤት የመድሃኒት ርጭት ከመደረጉም በላይ የተረጨው መድኃኒት ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል ግድግዳው እንዳይለሰንና በወረቀት እንዳይሸፈን ማድረግ የቅድመ መከላከል ስራ አካል በማድረግ መተግበሩን የቡድን መሪዋ ገልጸዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር