በቅርቡ ከሲዳማ ዞን ዋና ኣስተዳዳሪነት ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊነት የተዛወሩት ካላ ሚሊዮን ማቴዎስ በ19ኛው የአጠቃላይ ትምህርት ጉባኤ ላይ ሪፖርት በማቅረብ ስራ ጀምረዋል

በደቡብ ክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት ለትምህርት ቤቶች የተመደበው የድጎማ በጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል 


ሃዋሳ ጥቅምት 25/2006 ለትምህርት ቤቶች የተመደበው የድጎማ በጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመንግስትና በባለድርሻ አካላት ድጋፍ ለትምህርት ቤቶች ድጎማ የሚውል ከ564 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡ ተመልክቷል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ሰሞኑን በ19ኛው የአጠቃላይ ትምህርት ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት የትምህርት ስራ በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ በተለይም በትምህርት ተቋማት በተደራጁ የልማት ሰራዊት፣ በፖለቲካ አመራር፣ በትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም በመላው ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ንቅናቄና በፍጹም ባለቤትነት ለመምራት የበጀት ድጋፉ ያበረከተው አስተዋጽኦ ቁልፍ ነበር፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለድጎማ የዋለው በጀት መጠን 564 ሚሊዮን 861 ሺህ 714 ብር መሆኑንና ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን በመግለፅ ለአንድ ተማሪ የሚሰጠውን የድጎማ መጠን ከ20 እስከ 25 ብር የነበረው ከ80 በላይ እንዲያድግ እድርጎታል ብለዋል፡፡ በስራ ላይ እንዲውል በተደረገው በዚህ በጀት በየትምህርት ቤቶቹ አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ መርሀ ግብሮችን ለማሳለጥ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡ የድጎማ በጀቱ የየትምህርት ቤቱን የበጀት እጥረት ችግር ሙሉ በሙሉ እንደማይቀርፍ በመገንዘብ ትምህርት ቤቶችና ቀበሌዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለትምህረት ቤቶች መሻሻልና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እያደረጉ ያለው ድጋፍ እጅግ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ ከመንግስትና ከልማት አጋሮች የሚገኘውን የድጎማ በጀት በየደረጃው የሚገኘው የትምህርት አመራርና ሌሎች የባለድርሻ አካላት አሳታፊ በሆነና ግልፅነት በተሞላበት ሁኔታ ለታለመለት የትምህርት ጥራት መሻሻል ወሳኝ ጉዳዮች እንዲውል በማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡም አቶ ሚሊዮን አሳስበዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ርዕሳነ መምህራን መካከል ይሁን አበበ፣ ፈለቀ ዘሩ እና በሹ ታደሰ በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቤቶችን የግብአት አቅርቦት ችግርን በመቅረፍ ረገድ የድጎማ በጀት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰው የግብአት አቅርቦቱ እየተሻሻለ መምጣቱ ለአጠቃላይ ትምህረት ጥራት የማረጋገጥ ተግባሩን ላይ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=13195&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር