ስለ ኢትዮጵያ ብሮድካስተር ምን ያህል ያውቃሉ? ኣንጋፋው ሬድዮ ሲዳማ በኣገሪቱ የማህበረሰብ ሬድዮ ዝርዝር ውስጥ ኣልተካተተም፤ ምስጥሩ ምን ይሁን?

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ባወጣው የኣገሪቱ የብሮድካስቲንግ ሚዲያ ዝርዝር ውስጥ 16 የማህበረሰብ ሬድዮዎች የተካተቱ ሲሆን፤ በኣገሪቱ የማህበረሰብ ሬድዮ ስርጭት በመጀመር በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነው ሬድዮ ሲዳማ በዝርዝሩ ውስጥ ኣልተካተተም።

ሬድዮ ሲዳማ፤ እኣኣ በ1990 ዎቹ ላይ በኣይሪሽ መንግስት ድጋፍ በይርጋኣለም ከተማ በቀድሞው ፉራ የልማት ምርምር ማዕከል ውስጥ በ954 ኪሎሄርዝ መካከለኛ ሞገድ ስርጭት መጀመሩ የሚታወስ ነው። ሬድዮ ጣቢያው ከስኞ እስከ ኣርብ በኣብዘኛው የትምህርት ፕሮግራሞችን የምያስተላልፍ ሲሆን፤ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ኣየር ላይ ያውላል።

ሬድዮ ሲዳማ የሲዳማን ባህል እና ቋንቋ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን፤ ከኣራት እስከ ስድስት ሚሊዮን ለሚቆጠረው የሲዳማ ህዝብ በቋንቋው ባህሉ የተተረከለት፤ የተዘፈነለት፤ በቋንቋው ድራማ የመሳሰሉ የሰነ ጥበብ ስራዎች የተሰሩለት ብሎም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮቹ ላይ በቋንቋው እንድወያይ እድል የተከፈተለት በሬድዮ ሲዳማ ነው።

ጣቢያውን በባለበትነት ያስተዳድር የነበረው የቀድሞው የሲዳማ ልማት ፕሮግራም በኃላ ላይ ደግሞ የሲዳማ ልማት ኮፔሬሽን በመንግስት ጠልቃ ገብነት በሲዳማ ያካህዳቸው የነበሩት የልማት ስራዎች ሲቋረጥ፤ ሬድዮ  ሲዳማ የባጄት ችግር ኣጋጥሞት ያስተላልፋቸው የነበሩትን ፕሮግራሞች በኣግባቡ ማስተላለፍ ኣለመቻሉ ይታወሳል። በወቅቱ ፕሮግራሞችን በመደጋገም ኣድማጮችን እስከ ማሰልቸት ደርሶ ነበር።

በኃላ ላይ ሬድዮ ጣቢያው በሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ ስር የሆነ  ሲሆን እስከ ኣሁን ድረስ የቀድሞ ዝናውን በሲዳማ ህዝብ ዘንድ መመለስ ኣልቻለም። 

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ወደፊት በሬድዮ ሲዳማ ላይ ዝርዝር ዘገባ እንደምያቀርብ ለኣንባብያን መግለጽ ይፈልጋል።

ምንጭ፦http://finndxer.wordpress.com/2009/03/23/radio-sidama-sidama-educational-radio-on-954-khz/
እና http://www.eba.gov.et/web/data/Broadcast/Broadcasters%20Details.pdf


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር