በወቅታዊ የሲዳማ ዞን የፖለቲካ ኣጀንዳ፧ ሲዳማ ዞን መንግስት የሚያካህዳቸውን የልማት ስራዎች ምርጫ ተኮር ከመሆን ኣልፈው ለህዝቡ እድገት እና ብልጽግና መሆን ኣለባቸው

New
Photo from Internet
በሲዳማ ዞን የየወረዳ ካቢኔዎች በየወረዳው የሚገኙትን ቀበሌዎች በመከፋፈል ወቅታዊ የዞኑ መንግስት ኣጀንዳ በሆነው የግብርና ስራ ላይ ከየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ጋር በመምክር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በምክክሩ ላይ ኣርሶ ኣደሮቹ በ2006 ዓም ለማምረት እና ለመስራት በሚፈልጉትን ስራ እና ምርት በማቀድ እያንዳንዳቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ በመደረግ ላይ ነው ሲሆን፤ ከዚህም ባሻገር በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በኣርሶ ኣደሮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በካቢኔ ኣባላት ማብራርያ እየተሰጠባቸው ነው።

ካቢኔዎቹ ከኣርሶ ኣደሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፈው ዓመት ማለትም በ2005 ዓም የምርት ዘመን በታዩ ድክመቶችን እና ጥንካሬዎችን የመረመሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ድክመቶቹን በማረም ጥንካሬዎችን የበለጠ በማጠናከር በምቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተዋል ተብሏል።

በውይይቱ ላይ ካቢኔዎቹ እንዳሉት ከሆነ፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች በእጃቸው ያለው ሃብት መሬት፤ የሰው ኃይል እና ውሃ በመሆኑ እነዚህን በማቀናጄት የበለጠ ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል። በምቀጥሉት የበጋ ወራት የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ልደርሱ የምችሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ የምደረግ ሲሆን፤ ለዚህም ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ ያላቸው ኣርሶ ኣደሮች ከዚሁ የውሃ ሀብት እንዲጠቀሙ፧ ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ የሌላቸው ደግሞ የውሃ ጉርጓድ እንድቆፍሩ መክረዋል።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና በወቅታዊው የሲዳማ ፖለቲካ ላይ ያናገራቸው ስማቸውን እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኝ የካቢኔዎቹ የልማት ዘማቻ ድብቅ ኣጀንዳ ያጋለጡ ሲሆን፤ የሲዳማን ኣርሶ ኣደሮች ምርታማነትን ለማሳደግ ካቢኔዎቹ በማድረግ ላይ ካሉት እንቅስቃሴ በተጓዳኝ ኣርሶ ኣደሮቹን 1 5 የልማት ኣደራጃጀት ስም በማዳራጀት በ2007 ዓም የምደረገውን ብሄራዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ እንድያሸንፍ መሰረት የመጣል ስራ በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ኣክለውም ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎችም መሰል ኣደረጃጀት እና ቅስቀሳ ገዥው ፓርቲ በሲዳማ ዞን ኣሸናፊ እንድሆን ኣንዳደረገው ኣስታውሰዋል።

እንደፖለቲካ ተንታኙ፤የየወረዳዎቹ ካቢኔ ቀበሌዎችን ተካፋፍለው የግብርና ምርት በማሳደግ ስም ወደ ኣርሶ ኣደሮች ቅስቀሳ የገቡበት ዋናው ምክንያት የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች በገዥው የደኢህዴን ፓርቲ ላይ እምነት በማጣታቸው ለፓርቲው የምሰጡት ድጋፍ በመቀነሱ የተነሳ መሆኑን ኣመልክተዋል። በመደረግ ላይ ባሉት ውይይቶችም በመሳተፍ ላይ የምገኙት በኣብዛኛው የየቀበላቱ የፓርቲው ኣባላት እና ካድሬዎች መሆናቸው ተገልጸዋል።

በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ በሲዳማ ከተሞች ነዋሪዎች ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ እና በምቀጥለው ምርጫ ድምጽ እንዲሰጣቸው በከተሞች የልማት ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ መስራትን እንደቀዳሚ ኣማራጭ የተያዘ ሲሆን፤ በተለይ በሃዋሳ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በዶዘሮች በማስጠረግ እድሜ የሌለው የልማት ስራ በመሰራት ከመንገዶቹ በምነሳው ኣቧራ የከተማዋን ነዋሪ ለበሽታ በመዳረግ ላይ ብለዋል።


የሲዳማ ዞን መንግስት የሚያካህዳቸውን የልማት ስራዎች በኣንድ ድንጓይ ሁለት ወፍ እንደምባለው ምርጫን ለማሸነፍ ያለሙ ብቻ ሳይሆኑ ለሲዳማ ህዝብ እድገት እና ብልጽግና ለማምጣት ቢሆኑ ለፓርቲው ለህዝቡም ይበጃል ማለታቸውን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር